አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅ!

እንደ ዋላ ውሀ እደጠማት እንደራባት ጥም እንደያዛት የሚያሳብቀው ገላዋ ጎስቋላ ነው ስጋዋ ይህቺ እማማ….. አዲስ አቁማዳ ተሸክማ አየኋት ማህሌት ቆማ አዳዲስ ዜማ ስታዜም ስትደረድር ስትገጥም አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅልኝ የወይን አረግ ጥመቅልኝ

More

ፀሀይ ውጪ ውጪ! – ገለታው ዘለቀ

ጎህ ሳይቀድ ማለዳ የአማሮች መርዶ ጎህ ሳይቀድ ማለዳ የትግራዋይ መርዶ ደግሞ ማልዶ ማልዶ የኦሮሞ መርዶ ደግሞ ማልዶ ማልዶ የኮንሶዎች መርዶ ደግሞ ማልዶ ማልዶ ያገሬ ልጅ መርዶ አዘን ደረበባት ኢትዮጵያ አይኗ ጠፋ ልቧ

More

ቪቫ ሲሪ ላንካ!  (ከአሁንገና ዓለማየሁ) 

እንዲህ ሹክ ይለኛል የምኞት ፋብሪካ አቢይ አህመድ አሊ ሳይሞት ሳይነካ ቪቫ ሲሪ ላንካ! የካድሬን ኩይሳ የተቦረቦረን ያለቀን ተበልቶ ሕዝቡ እንደ ንብ ተምሞ ይደርምሰው ገብቶ ከውቅያኖስ ማዶ ላሰማችው ፊሽካ ቪቫ ሲሪ ላንካ አቢይ

More

ነፃነትህ በእጅህ! (በላይነህ አባተ)

አሻጋሪ ድልድይ ስትል የነበረው፣ መቀመቅ አስምጦ እየጨረሰህ ነው፡፡ ኩላሊትና ልብ ሳንባዬ ነው ያልከው፣ ምች ነቀርሳ ሆኖ ተምድር ሊያጠፋህ ነው፡፡ መብት ነፃነትህን ተእጅህ አዘርፈህ፣ ተእግር ብትደፋ እንዲመልስልህ፣ እንኳንስ ጭራቁ እግዜርም አይሰማህ፡፡ እርዳኝ እረዳለሁ

More

ስማኝ የሸገር ልጅ (ከአሁንገና ዓለማየሁ) 

ጠኔውም ቢገልህ ስጋም አንቆህ ብትሞት መዝግቦት ተጓዘ ታሪክ ያንተን ሐሞት ስትሳለቅ ነበር ትናንት በእስክንድር በአቋራጭ ቀዳድሞህ ቆሞልሃል ብድር። ስማኝ የሸገር ልጅ ኳስ ዳንኪራ ብርቁ ጊምቢ ቶሌ አይደለም እልቂቱ ፍጅቱ ያንተኑ ነገ ነው ያሳዩህ በሩቁ ንብረትህን ዘርፈው ቤትህን ሲያነዱ እትና እናትህን ልጅና ሚስትህን እንዴት እንደሚያርዱ ምን እንደሚመስል ያንተኑ ነገ ነው ያሳዩህ በሽንቁር ወለጋ ሩቅ መስሎህ የዋሁ ሸገሬ እንዳትደነቁር ከነግብራበሩ ነገ ብልጽግና ባንተ ደም ይዋኛል ግንፍሌ፣

More
/

እግዜር ይጠይቃል! ትውልድ ይታዘባል! ታሪክ ይዘግባል! – በላይነህ አባተ

በዘር በቋንቋቸው በባትሪ በመብራት እየተፈለጉ፣ እንደ በግ እንደ ከበት ሰዎች ሲታረዱ፣ እግዜር ይጠይቃል ማን እንደነበሩ ስለቱን የያዙ፣ ትውልድ ያፋጥጣል እነማን አሳስረው ሕዝብ እንዳስጨረሱ፣ ታሪክ ይታዘባል ስንቶች ሆድ ለመምረግ አፍን እንደ ዘጉ፡፡ ግብር

More

ዜጎች ሲታረዱ ዘንችረው ያድራሉ! – በላይነህ አባተ

የይህ አድግ መቅሰፍት ወርዶ ባገሪቱ፣ ለፍቶ አዳሪ ዜጎች በጭራቅ ሲፈጁ፣ ጉልቻ እንደራሴ ሚኒስቴር የሆኑ፣ የሟቾችን ግብር ደመወዝ እያሉ፣ ተአራጅ ተአሳራጅ እጅ እየተቀበሉ፣ በሰፊው ከርሳቸው ሲዝቁ ያድራሉ፣ ሕዝብና ትውልድን ታሪክን ሳይፈሩ! በታቦት በመስጊድ

More

“አንተነህ” – ብዙአየሁ ደስታ

አግኝተህ ያልኮራህ ጥቅም ያልቀየረህ፣ ለአገርህ ለህዝብህ ንፁህ ፍቅር ያለህ፣ አንተነህ ጀግናችን ፅኑ አላማ ያለህ። ከፓርላማው መሀል ጎልተህ የምትወጣ፣ ጥያቄህ እውነታ አንጀት የሚያጠጣ፣ ብዙ አመት ኑርልን እኛ አንተን አንጣ። አንተ የጎጃም ነህ አንተ

More

አልወለድም – አቤ ጉበኛ (የመፃሕፍት ማዕድ)

እውነት በሌለበት በዚህ ውሸት አለም፣ እኔ አልወለድም ይቅርብኝ ግዴለም፣ ሠው በሰውነቱ እኩል ካልተዳኘ፣ ወፍራም በውፍረቱ ዳኝነት ካገኘ፣ ድህነት እርሀብን ችግርና ስቃይን ፣ ለማየት አልሻም ቅጡ ያጣ ፍርድን፣ አልወለድም፣ እቢ አልወለድም እኔ በዚህ

More

“ ቀጠለ…ወደ እሳቱ” – ጌታቸው አበራ

እንደ እሳት እራቷ – እንደ ቢራቢሮ፣ ብር… ትር… እያለ – ክንፎቹን ሰትሮ፣ ሙቀቱን ሳይለካ – ትርፍና ኪሳራ፣ ብርሃኑ መስሎት – መንገድ እሚመራ፣ እሚቋቋም መስሎት – በሰላ አንደበቱ፣ የመቅለጡን ጉዞ – ቀጠለ ወደ

More

የተካደ ትውልድ (በእውቀቱ ስዩም)

የተካደ ትውልድ አይዞህ ባይ የሌለው ታዳጊ የሌለው ወይ ጠባቂ መላክ፥ ወይ አበጀ በለው ደርሶ ከቀንበሩ ፥የማይገላግለው፤ የተካደ ትውልድ አብዝቶ የጾመ፥ ተግቶ የጸለየ ጥቂት መና ሳይሆን፥ ጥይት ሲዘንብ ያየ እድሜ ይፍታህ ተብሎ፥ የተወለደ

More
1 2 3 12