የወለጋው ጭፍጨፋ ከ700 ተሻግሯል

በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ዞን ጊምቢ ወረዳ በአማራ ተወላጆች የተፈፀመውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ የዞን እና የወረዳው አስተዳዳሪዎች እና አመራሮች “የሟቾቹን አስከሬን ወደ መቃብር ስፍራ አታሰባስቡ ፣ በሞቱበት ስፍራ በጅምላ ይቀበሩ” በሚል ሁሉንም አስከሬን በየቤቱ ጓሮ አፈር እያለበሱ መዋላቸውን ከጭፍጨፋው የተረፉ የቀበሌዋ ነዋሪዎች ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።
የዞኑና የወረዳው አመራሮች ይህንን ትዕዛዝ ያስተላለፉት ጭፍጨፋውን አለም አቀፍ ሚዲያዎች እያራገቡት በመሆኑ የሟቾች ቁጥር በትክክል መታዎቅ የለበትም በሚል መሆኑን ከስፍራው በስልክ ያነጋገርናቸው የሟች ቤተሰቦች ገልፀውልናል።
289524160 10227478809466643 5729393116830544003 n
ዛሬ በቀበሌዋ በሚገኙ ሦስት ጎጦች ውስጥ ከሰባት መቶ በላይ አስከሬን መገኘቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ከሟቾቹ ውስጥም የአምስት ቀን ጨቅላ ህፃን ትገኝበታለች ብለዋል ነዋሪዎቹ።
286905826 151684844100166 7067570455980644270 n
ጎበዜ ሲሳይ
ተጨማሪ ያንብቡ:  የቶሮንቶ ኢትዮጵያዊያን የዜጎችን መፈናቀል አወገዙ፤

Leave a Reply

Your email address will not be published.