ፋኖ ላይ የዘመተው መንግስት ደባ…!

287585454 2351556845000793 1809736838433372475 nይህ ሙትቻ አገዛዝ የዜጎችን ደህንነት የማያስጠብቅ ነውረኛ ስርዓት ነው፤ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለይም በኦሮሚያ ምእራብ ወለጋ መንግስት ተብየው በፈለፈላቸው አሸባሪዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ባለማቻሉ ንጹሃን ዜጎች በግፍ እየተገደሉ ነው….።
ዛሬ ሰላማዊውን ፋኖ የሚያሳድድ ደመኛ አገዛዝ ልብ ካለው ለምን አራጁን ሸኔ ማስታገስ አቃተው፤ ካቃተውስ የንጹሃን መታረጃ የሆነው ወለጋ ለምን በዐማራ ኮማንድ ፖስት አይመራም??!
እናንተ በንጹሃን ደም የተጨማለቃችሁ እርኩሳን ይዋል ይደር እንጅ ከተጠያቂነት አታመልጡም…።
——————–

ኦነግ መንግስት ውስጥ እያለ እንዴት ፣መንግስት ኦነግን ማሸነፍ ይችላል ? # ግርማካሳ

ሳማንታ ፓወርስ፣ ሊንዳ ግሪንፊልድ ፣ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ በኦሮሞ ክልል በአማራዎች ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ሰቅጣጭ (horrific ) ሲሉ አውግዘዉታል፡፡ ለሞቱትም ሃዘናቸውን ገልፀዋል::
በአንጻሩ አብይ አህመድ ፣ “ኢመደበኛ በሆኑ ኃይሎች ጥቃት ተፈጽሟል።ንጹህና ተጨፍጭፈዋል፣ ህግ የማስከበር ስራችንን ተከትሎ የተሸነፉ ሕይሎች የፈጸሙት ድርጉት ነው” ውጭ ከማለት ባለፈ፣ እስከ አሁን ሃዘኑን አልገለጸም፡፡ ለሞቱት ነፍስ ይማር አለለም፡፡ መዝሙር አልተዘመረም: ኦሮሞ ይጠላል እያለ ሲያብድ እንዳልነበረ በወለጋ ያለቁትና የተገደሉት ተመርጠውአማራዎች መሆናውን እንኳን ለመጥቀስ አልፈለገም::
አንድ የኦሮሞ አርቲስት ሲሞት ሃዘን ለማወጅ፣ ባንዲራ ዝቅ ለማድረግ የተፋጠነው የአብይ አህመድ ኦህዴድ መንግስት ፣ በይፋ የታወቀው ወደ 500 መቶ፣ ግን ቁጥሩ ከአንድ ሺህ በላይ ይሆናል በሚባለው ጭፍጨፋ ሕይወታቸው ላጡ ዜጎች ግን፣ በአገር ደረጃ የሃዘን ቀን እንዲታወጅ፣ ባንዲራ ዝግ እንዲደረግ አላደረገም፡፡ በዚህም የኢትዮጵያዉያንን ሕይወት እንደ ትንኝ የሚቆጥር ጨካኝና አረመኔ፣ hearltess አገዛዝ መሆኑን ነው ያሳየው፡፡
በፓርላማ ከሞቱት የሕሊና ጸሎት ይደረግ ሲባል እንኳን ፣ የህሊና ጸሎት ይደረግ ያሉትን እስከ ማስጠንቀቅ፣ እንዳይናገሩ ማይክሮፎናቸው እስከ መዝጋትም ተደርሷል፡፡ የኢትዮጵያ ፓርላማ የግራዚያኒ ጊዜ የነበረ ስብስብ እስኪመስል ድረስ የኢትዮጵያዉያንን ስቃይ ማንሳት እንደ ወንጀልና ህገ ወጥ ሲቆጠር እንደማየት ልብን የሚያደማ ነገር የለም፡፡
የአብይ መንግስት ጭፍጨፋዉን የፈጸመው ኦነግ ነው ይላል፡፡ ጥፋቱን ሌሎች ላይ ለማላከክ ይሞክራል፡፡ ላለፉት አራት አመት የለመደውን አሳፋሪ ድራማ ያሰማል፡፡ “እርምጃ እየወሰድን ነው፣ ይሄን ያህል ሸኔ ደመሰስን” እያለ፡፡
ኦነግ አደርገውም፣ አላደረገውም ፣ መታወቅ ያለበት ግን: የአብይ መንግስት ለጭፍጨፋው ቀዳሚና ዋናው ተጠያቂ መሆኑን ነው፡፡ ሌላው ቢቀር ፣ ኦነግ ነው የጨፈጨፈው ከታበለም፣ ይህ ጭፍጫፊ በስፋት እንዲንቀሳቀስ ያደረገው የአብይ መንግስት አይደለም እንዴ ? ለአራት አመት ኦነግ ሲደራጅ፣ ወጣቶች እየሰበሰበ ሲያሰለጥን ዝም ብሎ የተመለከተው የአብይ መንግስት አይደለም እንዴ ? ለኦነግ ስንቅና ትጥቅ፣ መረጃዎች ሲሰጡ የነበሩት፣ አሁንም የሚሰጡት በአብይ አህመድ አገዛዝ ውስጥ ያሉ የመከላከያ፣ የደህንነት ፣ የኦሮሞና የፌዴራል መንግስት ኦነጋዊ አመራርና ሃላፊዎች አይደለሉም እንዴ ? የኦነግ ታጣቂዎች ብዙዎች የአብይ መንግስት ያሰለጠናቸውና ከባባድ መሳሪያ ያስታጠቃቸው የኦሮሞ ልዩ ኃይል አባላት የነበሩ አይደሉም እንዴ ?
በኔ እምነት
1ኛ ኦህዴዶች የፌዴራል መንግስትን እስከተቆጣጠሩ ድረስ፣ ጭፍጨፋው ይቀጥላል፡፡ በመሆኑም አብይ አህመድ ከሃላፊነቱ መነሳት አለበት፡፡ ኦህዴድ ያልሆነ፣ ለኦሮሞ ጽንፈኞች ስስ ልብ የሌለው፣ ወይም ቀን ብልጽግና ማታ ኦነግ ያልሆነ፣ የሁሉም ኢትዮጵያዉያንን ደህንነት ለማስጠበቅ ቁርጠኝነት ያለው ጠቅላይ ሚኒስተርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ያስፈልጋል፡፡ የግድ ነው፡፡ ኦህዴዶች ስልጣን ላይ ሆነው ፣ በኦሮሞ ክልል ሰላም የሚያገኝ አማራ አይኖርም፡፡
2ኛ በሂደት የኦሮሞ ክልል መበተን አለበት፡፡ ኦሮሚያ የሚሉት ክልል እስካለ ድረስ በክልሉ ያሉ ሌሎች ማህበረሰባት ስንጥር ታክል ሰላምና ደህንነት አያገኙም፡፡ እስከዚያው ግን በቶሎ መደረግ ያለበት ጉዳይ አለ፡፡ በወለጋ ያሉ የዞንና የወረዳ አስተዳዳሪዎች በሙሉ መነሳት አለባቸው ። ወለጋ በፌዴራል ስር ሆና ፣ በአካባቢው ባሉ የተከበሩ ሽማግሌዎች እንድትተዳደር በማድረግ፣ ሰላምና ደህነንት የማስጠበቁን ስራ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ በመከላከያ ስር እንዲሆን መደረግ አለበት፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን ማድረግ ካልተቻለ፣ ሁለት አማራጭ ነው ያለው።
ጭፍጨፋን ለማስቆም፡፡ በወለጋ የሚኖሩ አማራዎች ሙሉ ለሙሉ ወለጋን ጥለው መውጣት አለባችው፡፡
ወይንም የአማራው ማሀረሰብ አራት ኪሎ ያለው አረመኔ አገዛዝ በኃይል ለማስወገድ በመንቀሳቀስ ፣ የወለጋን ችግር በዘላቂነት የሚፈታ ጠንካራ ማ እከላዊ መንግስት እንዲኖር ማስደረግ አለበት፡፡
ወገኖች አንሳሳት ኦነግ ሆነ ሌሎች የሚፈነጩት፣ መንግስት ውስጥ የነርሱ እዎች ስላሉ፣ በኪሳቸው ያስገቧቸው የኦህዴድ። የመከላከያና የደህንነት መስሪያ ቤቶች ሰዎች ስላሉ ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ከኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫና የቀረበ ጥሪ

Leave a Reply

Your email address will not be published.