” አቡነ” ሳዊሮስ ማናቸው ?

★ ከሁለት ሴቶች ዲቃላ(ከሕጋዊ ጋብቻ ውጪ) የወለዱ ምንኩስናቸውን በዝሙት ያፈረሱ ሴሰኛ ሰው ናቸው።★
★ ቅዱስ ሲኖዶስ በአስቸኳይ ከዲቁና እስከ ጵጵስና ያለው ሥልጣነ ክህነታቸውን ያንሳ!! ቤተክርስቲያን የዘማዊ መጫወቻ አይደለችም።★
“አባ” ሳዊሮስ በምዕራብ ሸዋ ዞን አዳበርጋ አዳዳ ባለወልድ የተወለዱ የሸዋ አማራ ሲሆኑ ቋንቋውን ስለሚችሉ ግን ኦሮሞ ነኝ ብለው ለኦሮሚያ ክልል ኮታ ማሙያ ጵጵስና የተሾሙ ሰው ናቸው፡፡
የቀድሞ ስማቸው አካለ ወልድ ሞገስ ነው፡፡ በምስካየ ኅዙናን ገዳም ሲያገለግሉ በምንኩስና እያሉ ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጪ ልጅ የወለዱ ሲሆን እዚያው ወንድማቸው ዲያቆን ግርማ ሞገስ የተባለ የሚያሳድገው ከእሳቸው የተወለደ ልጅ አላቸው ስሙም ግርማ አካለወልድ ይባላል፡፡ እዚያው ምስካየ ሕዙናን ት/ቤት ተማሪ ነበር። አባ ሳዊሮስ 6 ሺ ብር ይከፍሉለታል፤ ምግብ ከገዳሙ ድርጎ ያገኛል፡፡ሰውን ለማታለል የእህቴ ልጅ ነው እያሉ ያስወራሉ እንጂ ልጃቸው ነው። ይህን ምስጢር በፊት የወሊሶ በኋላ ደግሞ የሆረጉድሩ ወለጋ ሥራ አስኪያጅ መጋቤ አዕላፍ ተስፋዬ ዋቅጅራ በደንብ ያውቃሉ፡፡ብዙ ጊዜ ከአባ ሳዊሮስ ጋር ሲጣሉ የሚናገሩት ይህንኑ ነበር፡፡ በሠበታ ጌቴ ሰማኒ የሴቶች ገዳም የምትኖር አገር ቤት በሚኖረው አበበ ሞገስ በሚባለው ወንድማቸው ስም የምትጠራ “የትናዬት” የምትባል ከሌላ ሴት የወለዷት ልጅም አላቸው፡፡ የዚህች ልጅ እናት አሁን አቃቂ የምትኖር ሲሆን ግሮሠሪ አላት፡፡
“አባ” ሳዊሮስ ቦረና በነበሩ ጊዜ የቤት አስቤዛ በገፍ እንደሚያመጡላት የዓይን እማኞች ይመሠክራሉ፡፡ከተጣሉት ማህበር ጋር ለመታረቅ መንስኤ የሆነችው ይህች ሴት ናት፡፡ ምክንያቱም የማህበሩ አባላት ከፍተኛ ብር በመመደብ እናትየውን ያሳመኑ ሲሆኑ እስዋም ልጅህን አጋልጣለሁ በማለትዋ አባ ሳዊሮስ ከማህበሩ ጋር እንደ ታረቁ የታመኑ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ይህ እንግዲህ ሰው ገድሎአል ከሚለው በተጨማሪ ሌላኛው መረጃ ነው። ሐራ ተዋሕዶ ይህን ዘገባ ዘግቦአል፡፡ ይህችን አባ ሳዊሮስ የወለዱላትን ሴት ያደራደሩትና ጉዳዩንም ከጫፍ ያደረሱት
1. ወሊሶ ከተማ የሚኖር የመንግሥት ሠራተኛ መምህር የሆነ ጌታሁን አማረ፣
2. ወጣት ሣሙኤል ደረሰ የተባለ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ የማህበሩ ማዕከል ሰብሳቢ በዋነኛነት ይጠቀሳሉ። አሁን አባ ሳዊሮስን በቅምጥነት የምታገለግል በሰበታ ወረዳ ቤተ
ክህነት ሥር የሚገኘው የዑራኤል ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ምክትል ሊቀመንበር የሆነች ሜዘር የምትባል ባልዋ የሞተባት ሴት ስትሆን አባ ሳዊሮስ ቤቷን ሀገረ ስብከታቸው እንዳደረጉት ይነገራል፡፡ ይህን ምስጢር ያውቃሉ የሚባሉትን ሰባክያነ ወንጌል ተሃድሶ የሚል ታፔላ ተለጥፎባቸው ተባረዋል፡፡ ለምሳሌ፡- የሰበታ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ሰባኬ ወንጌልን፣ የሰበታ ወረዳ ቤተክህነት ስብከተወንጌል፣ የተጂ መድኃኔዓለም ሰባኬ ወንጌል ይጠቀሳሉ፡፡
አባ ሳዊሮስን በሞኝነት እየዘወረ ያለው የመንገድ ትራንስፖርት ዳይሬክተር የሆነውን ካሣሁን ኃ/ማርያም ሲሆን ቅዳሜና እሁድ ውሎው ወሊሶ እንደነበረ ሳዊሮስ ገንዘብ በመመደብ እስከ እኩለ ሌሊት አቶ በላይ ሆቴል በማምሸት ከአንድ ጳጳስና የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊ የማይጠበቅ ተግባር ፈፅመው ያመሹ እንደነበር ምንጮች ይናገራሉ፡፡ አባ ሳዊሮስን በቅርብ የሚያውቁ ደብረ ፅሞና ገዳም እያሉ ከገዳሙ እስከ እንጪኒ ከተማ አረቄ በመጠጣትና በመዝፈን የወጣትነት ጊዜያቸውን እንዳሳለፉ ይገልፃሉ፡፡ አባ ሳዊሮስ የተሾሙበት ሀገረ ስብከት የዛሬውን አያድርገውና ሀብተ ፈውስ የተሰጣቸው የታላቁ አባት የወንጌል ገበሬ የሆኑት አቡነ ዲዮስቆሮስ የኖሩበት ሀገረ ስብከት ሲሆን ሰውን በወንጌል አገልግሎት አሳርፈዋል፣ በኋላም ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ደክመው አልምተውታል፡፡ አባ ሳዊሮስ የተጠመዱት ግን በነውራቸው አሸማቀው የያዙዋቸው ቡድኖች በሰጧቸው ስም ዝርዝር መሰረት አገልጋዮቹ ላይ ተሃድሶ የሚል ታፔላ እየለጠፉ በማገድና ሴት ወይዘሮዎችን በመቀያየር ነው፡፡ ከወሊሶ እስከ ሠበታ ባሉት የደብር አለቆች እና የቢሮ ሠራተኞች ዓበይት በዓላትን፣ የጾም ፍቺዎችን እየጠበቁ ከ1ዐ-4ዐ ሺ ካላመጡ ያግዳሉ፣ ይቀይራሉ በተሃድሶነት ይፈርጃሉ፡፡ ለምሳሌ ዓለምገና ሚካኤል አባ ወ/ጊዮርጊስ አስተዳዳሪ የሆኑበት ደብር ሙዳየ ምፅዋት ሲቆጠር በየወሩ 15ሺ ብር ስለሚሰጡ ስንቱ አለቃ ሲዘዋወር እኚህ አለቃ ግን ይታለፋሉ፡፡ ከሀገረ ስብከታቸው ውጪም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ የአባ ሳዊሮስን የቤተ ክህነቱን መኖሪያ ቤት ሽምገል ያሉት ጳጳሳት ሁለተኛው የሲኖዶስ ጽ/ቤት ይሉታል፡፡ አድማ፣ ረብሻ፣ ተንኮል የሚጠነስሰው በዚሁ ቤት ነው፡፡ሲኖዶስ በመጣ ቁጥር አስቀድመው በዚህ ቤት መሰብሰብን የሚያዘወትሩ
1. አባ ማቴዎስ
2.አባ ዲዮስቆሮስ
3. አባ ሉቃስ
4. አባ ቀሌምንጦስ
5. አባ ሔኖክ ናቸው።
የሲኖዶስ ስብሰባ ተጀምሮ እስከሚያልቅ አባ ሳዊሮስ ቤት የመዋጮ ተራ በመግባት ሲበሉ ሲጠጡ ከውስኪ ጋር ነገር ሲያወራርዱ ያመሻሉ፡፡ ይህም ተራ የሚገቡት ሙክት ፍየል ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህን ምግብ በተለይ የፈረንጁን አሣምሮ የሚሠራላቸው የመልከጸየዴቅ ገዳም አስተባባሪ የሆነ ለይኩን የተባለ ሰው ነው፡፡ ልብ በሉ በመንበረ ፓትርያርኩ በጀት ማዕደ አበው የተባለ ለብፁዓን አባቶች የተመደበውን አይነኩትም፡፡ ብዙዎች አባቶች አባ ሳዊሮስን በጣም “ጅል” ናቸው ይላሉ፣ ምክንያቱም እንዲህ ዓይነት ስብሰባ ሌሎች አባቶች ቤት እንዲደረግ ፈቃደኛ ስለማይሆኑ የእርሳቸውን ቤት ለአድማ ይጠቀሙበታል፡፡ “በሞኝ ክንድ የዘንዶ ጉድጓድ ይለኩበታል” ይባላል፡፡ ሊበሉ ሊጠጡ ሊዘፍኑም ተነሱ እንደ ተባለው ከዚህ በኋላ ነው የቀድሞውንም የአሁኑንም ፓትርያርክ መከራ የሚያሳዩት፡፡ በአባ ሳዊሮስ ቤት ውስጥ እልፍነሽ የምትባል ሴት ትኖራለች፡፡ ምናቸው እንደሆነች ባይታወቅም የዚችን ሴት እህቶች በተለያየ ቦታ እንደቀጠሩ ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ ለምሳሌ 1) በሰበታ ገብርኤል ገንዘብ ያዥ፣ 2) የዚያው የወረዳው ቤተ ክህነት ሂሳብ ሹም አዳነች ትባላለች፣ 3) ሌላ ወለቴ ሥላሴ ዕቃ ክፍል ነች፡፡ ስለዚህ እርሷ ያለአንዳች ምክንያት ከአንድ ቤተሰብ እነዚህን መቅጠራቸው ለምን ይሆን ሲሉ ብዙዎች ይጠይቃሉ፡፡
ስለዚህም የኦሮሞ ክርስቲያኒኖች እባካችሁን ንቁ!! እነዚህ ለሆዳቸው ያደሩ፣በሥልጣን ጥማትና በፍቅረ ንዋይ በታወሩ ጳጳሳት ተብዬዎች አትታለሉ እነርሱ ከቤተክርስቲያን ክብር በላይ በፓለቲከኞች ሽንገላ የተደለሉ ከዳተኞች ናቸው። ምዕመናን ሆይ እናንተ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን ብቻ እያያችሁ ከቅድሥት ቤተክርስቲያን አንድነት ጋር ጽኑ።ዋጋችሁ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ብዙ ነው።
ሌሎችም ጳጳሳት ተጠንቀቁ!! ብዙ ጉድ ችለን ዝም ያልነው ለምዕመናን አዕምሮ በመጠንቀቅ ነው።እምቢ ብላችሁ የምታምጹ ከሆነ ግን ከእናት ቤተክርስቲያን ክብርና ህልውና በላይ የእናንተ ክብር ስለማይበልጥ ተጨባጭ መረጃዎችን ለሕዝብ ማጋለጣችንን እንቀጥላለን።ክርስቶስ በደሙ የዋጃት ቅድሥት ቤተክርስቲያን ጸንታ ትቀጥላለች እናንተ ግን ትውልድ እየተጸየፋቹ ዘመናችሁ በከንቱ ያልቃል።ፍርድንም ከመለኮት ትቀበላላችሁ።
እባካችሁ ለሌሎችም ሼር በማድረግ ከቤተክርስቲያን ጎን እንቁም!!
መ/ር ታሪኩ አበራ
ተጨማሪ ያንብቡ:  30 ዓመት ችግር ያመጣ አደገኛ አካሄድን በተረኝነት ማስቀጠል ያዋጣል!? | Hiber Radio with Ato Kidane Alemayehu

2 Comments

  1. ጎበዝ!
    ጌታቸው ረዳ የተባለ የአክሱም ኢትዮጵያዊ ላለፉት 30 አመት ያለመታከት ባንዳን( የኦሮሞን፤የትግሬን) ሲፋለም እስከ ዛሬ የኖረ ወንድማችን ነው፡፡ የህወአትን ታላቁን ሴራ ቀድሞ የሚያሳውቀን ይኸው ወንድም ነው ነገር ግን ስራው በብዙ ኢትዮጵያውያን የሚታወቅ አይደለም ብዙ ደክሞ የሚያዘጋጀው ” ethiopian semay” የሚል የድር ገጸ ስላለው ጥልቅ የሆነ ጽሁፉን ለማንበብና ለስራው እውቅና ለመስጠት እየገባን ብናነበው ለሌሎች ብናስተላልፈው እኛም አገርም ተጠቃሚ እንሆናለን የሚል እምነት አለኝ፡፡አመሰግናለሁ

  2. የታተተውን ሪፖርት ካነበብንና ቀኖናው የሚፈቅደውን ካገናዘብን በኋላ በማንኛውም ጊዜ አቶ አካለ ወልድ ብለን ብንጠራ ቅስፈት ይሆንብን ይሆን? እሳቸውስ ይህን ሁሉ ካደረጉ በኋላ ይህን በማለታችን ቅሬታ ይገባቸው ይሆን? ወይስ እንደተባለው እናንተ ከጀመራችሁት ብለው ደስታ በደስታ ይሆኑ ይሆን? ቀሲስ በላይ ከዚህ በፊት ክርስቲያኖች በሚንጫ ይፈጁ ብሎ ያዘዘውን ያልተቀበለ ኦርቶዶክስ አላውቅም እንዳሉት ጸንተው ይሆን?

Leave a Reply

Your email address will not be published.