Comments on: “በሠይፍ የሚጥሉ በሠይፍ ይወድቃሉ” አምባቸው ዓለሙ (ከደሴ) https://amharic-zehabesha.com/archives/121836 ዘ-ሐበሻ | Ethiopian News | የዕለቱ ዜና | ሰበር ዜና, ትኩስ የዕለቱ ዜና በአማርኛ, የኢትዮጵያ ዜና | ዜና ፖለቲካ ፣ አይቲ ዘ-ሐበሻ ሰበር ዜና ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ ሌሎች ብዙ አዳዲስ ዜናዎች| Fri, 17 Sep 2021 14:28:53 +0000 hourly 1 https://wordpress.org/?v=6.0.3 By: Tesfa https://amharic-zehabesha.com/archives/121836#comment-199509 Fri, 17 Sep 2021 14:28:53 +0000 https://amharic.zehabesha.com/?p=121836#comment-199509 ስማ/ሚ ወገኔ በአለም ላይ ለሚነሱ ግጭቶች መንስኤ ናቸው ከሚባሉት ቀዳሚው ሃይማኖትን ተገን ያደረገ ነው። ከዚያ ቀጥሎ ዘረኛነትና የሃብት ምንጭ ማግኛ ለምሳሌ የነዳጅ ዘይት ምንጭ እንዳይደርቅ በሃገሮች ላይ የሚደረግ የቀጥታና የእጅ አዙር ሽኩቻን ይጨመራሉ። በመሰረቱ አንድ ሃይማኖት ከአንድ ሃይማኖት አይበልጥም። ግን አንድ የሚያደርገንን ነገር አጎልቶ ከማሳየት ይልቅ ትንሿን ልዪነት ጣራ ላይ እየሰቀሉና ጸጉር እየሰነጠቁ ለራሳቸው ጥቅም የሚያላትሙን ሆዳሞችና ከፋፋዪች ናቸው። ለዚህም ነው ወያኔ ሃርነት ትግራይ በይፋ አማራንና የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ቀብረናቸዋል ብሎ የፎከረው። አሁን ላይ ለቆመ ማን የተቀበረው ማን እንደሆነ ማየት ይችላል። ጉራና ት እቢት ስለሆነም የፕሮቴስታንት አማኝ ጥርቅም ይህን አለ ያን አለ፤ አመራሩ ይህን አጠፋ፤ እከሌን ልከሰው ነው ምን የማይባል ነገር አለ እያሉ የህዝባችን የሰቆቃ ጊዜ ከማራዘም ብልህ የሚታለፈውን አልፎ የልብን በልብ ይዞ ለሃገር አንድነትና ልዕልና ይሰራል።
ባጭሩ ማንም መንግስት ቢሆን ሙሉዕ አይደለም። በዲሞክራሲ ስም ምላ የምትገዘተው አሜሪካ እንኳን ዲሞክራሲያዊነቷ የውሸት ነው። ለዛ ነው በድንጋይ የተባረረው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሃገርን ለማፍረስ ከአሜሪካና ከሌሎች ሃገር አፍራሽ ሃይሎች ጋር የተጎዳኘው። የተላላኪዎች መንግስት መፍጠር የአሜሪካ የውጭ ፓሊሲ ዋንኛ ተግባር ነውና። ግን እኛ ትንኝን ልናጠራ ስንላፋ እነርሱ በለመድት ተንኮል ዛሬም ትላንት ያለቀሱ አይኖችን እያስለቀሱ ይገኛሉ። በመሆኑም ይህን ያን እያለን የቆመን ለማፍረስ ከመከጀል ይልቅ እኔ ምን ላርግ የቱ ላይ ልሰለፍ በማለት የምንችለውን በጎ ነገር ዘር፤ ቋንቋ፤ ሃይማኖትን ተገን ሳናረግ አስተዋጾ ማድረጉ ከሁሉ የሚሻል ይመስለኛል። ለአሁኑ ሰይፍ ወጣ ሰይፍ ገባ ፍሬ የለውም። ሰው ሲጠቃ መከላከሉ ያለና የሚኖር ነው። አንድም ይሮጣል ያለዛም ቆሞ ይፋለማል። የምናየው ይህኑ ነው። በቃኝ!

]]>
By: Ahoon https://amharic-zehabesha.com/archives/121836#comment-199507 Thu, 16 Sep 2021 19:39:02 +0000 https://amharic.zehabesha.com/?p=121836#comment-199507 Amen. Qale hiwot yassemalin. That is all I could say.

]]>