ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ማነዉ? ክፍል አንድ (በንጉሤ ዶሌቦ)

ጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ከአባቱ ከአቶ ጴጥሮስ ሎዳሞ እና ከእናቱ ከወይዘሮ ሸዋዬ አብርሃም በአሁኑ ደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን ምስራቅ ባዳዋቾ ወረዳ አንደኛ አምቡርሴ ቀበሌ ሐምሌ 13 ቀን 1943 ዓ.ም ተወለደ፡፡(ፎጊ) በሚል የበረራ ኮድ ስሙ የሚታወቀዉ የሰማዩ ጀግና ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ከቤቱ ሶስተኛ ልጅ ነዉ፡፡

ከልጅነቱ ጀምሮ በመልካም ፀባዩ የሚታወቅ፣ደፋር፣ቁጡ ግን ደግሞ ይቅር ባይና ተግባቢ ባህሪይ ያለዉ ሲሆን በትምህርት አቀባበሉ ንቁና ጎበዝ እንዲሁም ወታደር የመሆን ዝንባሌም ነበረዉ፡፡ ዕድሜዉ ለትምህርት ሲደርስ ት/ቤት ገብቶ የተከታተለ ሲሆን እስከ አስራ አንደኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ድረስ ትምህርቱን በሆሳዕና ከተማ በቀድሞ ራስ አባተ ቦያለዉ በአሁኑ የካቲት 25/67 ትምህርት ቤት ተከታትሏል፡፡የአስራ ሁለተኛ ክፍል ትምህርቱን በዚሁ ት/ቤት እየተከታተለ እያለ በወቅቱ የኢትጵያ አየር ኃይል ባወጣዉ ማስታወቂያ ተወዳድሮ የተሰጠዉን ምዘና በብቃት በመወጣት ጥር 26 ቀን 1961 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር ኃይልን ተቀላቅሏል፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይልን ከተቀላቀለ በኋላ በተቋሙ የሚሰጡ ሥልጠናዎችን በብቃት ተከታትሏል።ከተከታተላቸው የሥልጠና ዘርፎች ውስጥ፦ የስድስት ወር መሠረታዊ የዉትድርና ኮርስ፣የሰባት ወር መሠረታዊ የበረራ ኮርስ፣የስድስት ወር የመጀመሪያ ደረጃ የበረራ ሥልጠና ኮርስ፣የአዉሮፕላን አብራሪነት ዲፕሎማ እንዲሁም ከፍተኛ የተዋጊ አዉሮፕላን ሥልጠና ኮርስ በሀገር ውስጥ ሰልጥኗል።ከሀገር ዉጭ በሀገረ አሜሪካ እና በቀድሞ ሶቭየት ህብረት የሚሰጠውን የበረራ ትምህርት ስልጠና ተከታትሎ በብቃት አጠናቋል፡፡በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት በወሰዳቸው የሥልጠና ኮርሶች ባገኘዉ ዕዉቀት እና ክህሎት እንዲሁም ባዳበረው ልምድ በአየር ኃይል ዉስጥ በተለያዩ ቦታዎች ለረዥም ጊዜ ተዛዋዉሮ አገልግሏል፡፡

ኮሎኔል በዛብህ አገልግሎት ከሰጠባቸው የተለያዩ ቦታዎች ውስጥ በተዋጊ አዉሮፕላን አብራሪነት፣በበረራ አስተማሪነት፣በስኳድሮን ምክትል አዛዥነት፣በተዋጊ ስኳድሮን የበረራ አስተማሪነት፣በበረራ ትምህርት ቤት የትምህርት መኮንን በመሆን (በተደራብነት)፣በበረራ ትምህርት ቤት አዛዥነት በተደራቢ፣በሰሜን አየር ምድብ ጥገና አዛዥነት፣በኤል-39 አዉሮፕላን በረራ አስተማሪነት፣ በበረራ ትምህርት ቤት ምክትል አዛዥነት፣በበረራ ማሰልጠኛ ት/ቤት የሥርዓተ ትምህርት ደረጃ እና ምዘና ኃላፊነት፣በበረራ ት/ቤት የዕቅድና ስርዓተ ትምህርት ኃላፊነት፣በኤል-39 አዉሮፕላን ስኳድሮን አዛዥነት እንዲሁም በምስራቅ አየር ምድብ አዛዥ ተደራቢ በመሆን የሰራባቸው ቦታዎች በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዓለማየሁ ገላጋይ

ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሠራዊት አባል ሆኖ በተሰማራባቸው አውዳ ውጊያ ግንባሮች ከፍተኛ ጀብድ እየፈፀመ የኖረ የሀገር ኩራት የሆነ ጀግና ነው።ጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ከወይዘሮ ወይንሼት ኃይሌ ጋር ትዳር መሥርተው ሶስት ወንድና ሁለት ሴት በድምሩ አምስት ልጆችን አፍርተዋል፡፡

1 Comment

  1. Ke Bezabeh timhirt mewsed ygebachewal lela ager metgat min titebikalachihu 1987 temeto aweredut be 1993
    leqequt lemin huletegha gize 1998 temelese ?

Leave a Reply

Your email address will not be published.