የአርባምንጩን የእነ እስክንድር ነጋ’ን እስር ባሰብኩ ጊዜ! ወደየት እያመራን ነን? ብለን ደግመን ደጋግሜን መጠየቅ አለብን – ዳንኤል ሽበሽ

eskinderሰሞኑን በዕድሜ የገፉ ወላጅ እናቴንና አባቴን ጨምሮ ሌሎች ቤተሰቦቼን ለመጎበኘት፣ በእርግዝና ምክንያት በጽኑ ታማ በሆስፒታል የሚትገኘውን እህቴን ለማስታመም እና የቆዩ ወዳጅ ዘመድ ለቅሶ ለመድረስ ባጠቃላይ ለማህበራዊ ጉዳዮች ወደ ትውልድ አከባቢዬ ቁጫ (ሰላምበር) ተጉዤ ነበር ። አከባቢው የትውልድ አከባቢ ከመሆኑም ባሻገር ከአንድም ሁለተ ለሕ/ተ/ም/ቤት የተወዳደርኩበት እና በብዙ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ የሚታወቅበት አከባቢ መሆኑን ልብ እያላችሁ ተከተሉኝ ።

ምን ገጠመኝ?

በ4ኛው ቀኔ ሆስፒታል የሰነበተችው እህቴን በሀኪሞች ውሳኔ ከሆስፒታል ይዘን ወደ ከላይኛው እህቴ ቤት (ሁለቱም የሕክምና ባለሙያ ናቸው) አምጥተን አከባቢው ሞቃታማ በመሆኑ በረንዳ ላይ እያስታመምናት እያለን ግቢው ተወረረ ። ፖሊሶች፣ የሚሊሺያ አባላት እና ሲቪል የለበሱ ግለሰቦች የአጥሩን በር በርግደው ገቡና ከበቡን ።

ማነህ? ከየት መጣህ? ለምን መጣህ? ስምህ ማነው? መታወቂያ አምጣ! ፀጉረ_ለውጥ ነህ! ወዘተ እያሉ ማዋከብ ማስፈራራት ጀመሩ ። ቀጠሉና በአጠገቤ ያለውን የህክምናና ሌሎች ሰነዶችን ፈተሹና መለሱልኝ ። የፍተሻና የመያዣ ከፍ/ቤት መያዛቸውን ጠየኳቸው ። እኛ ፖሊሶች ስለሆነን የፍ/ቤት ትዕዛዝ አያስፈልገንም የሚል ምላሽ ሰጡን ። ብቻ ድራማው ብዙ በመሆኑ አንባቢያንን ላለማሰላቸት ልተውው ።

ዕሁድ ሚያዝያ 2ቀን 2014 ዓም ። ከሰላምበር 50 ኪሜ ያህል ራቅ ብላ ወዳለችው  በለስ ተብላ ወደሚትጠራው ከተሜ ቀመስ መንደር የሚገኙ ወላጆቼን ላገኛቸው ጉዞ ጀመርኩ ። ወደ 35 ኪሜ ያህል ተጉዤ በአልፋ ወረዳ ልዩ ስሙ  ማጥኔ የሚትባል መንደር እንደደረስኩ በታጠቁና ሲቪል በለበሱ አካላት እንዳላልፍ ተደርጌ ወደ ኋላ (ወደ ሰላምበር) ለመመለስ ተገደድኩ ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአስተሳሰብ ነፃነትን በመገደብ ማንነትን መግደል አይቻልም !! (አሥራደው ከፈረንሳይ)

ድርጊቱ እጅግ የሚያበሳጭና መልመድ ያቃተን የአገዛዝ ባሕርይ ነው ። ይህኑን ያጋጠመኝን ነገር ለወላጆቼ በስልክ ነገርኳቸው። በተጨማሪ ለሕይወቴም ጭምር ሥጋት ውስጥ እንደገባሁ ለወረዳው ፀጥታ ቢሮ፣ ለፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮች፣ ለቅርብ ጓደኞቼ እና በግል ለማውቃቸው ከዞን እስከ ፌዴራል ላሉ ባለሥልጣናት አሳወቅሁ። በእርጅና፣ በህመምና በኑሮ ውድነት የተጎሳቆሉ ደካማ ወላጆቼን እንዳላይ ተከልክዬ ዕሮብ ሚያዝያ 5ቀን፡2014 ዓም ወደ አዲስ አበባ ተመለስኩ ። ከዚህ በፊት በኮቪድ-19 አስታከው በጨለማ ክፍል ከእባብ፣ ከጉንዳንና ከመሰል ተሳቢና በራሪ ነፍሳት ጋር አስረውኝና አሰቃይተውኝ መልቀቃቸው ይታወቃል ።

እንዲህ አይነት ማን አለብኝነትን የምለምድ ስብዕና የሌለኝ ቢሆንም ለጊዜው እንደተለመደ ቆጥሬ ዝም ብዬ ያሳለፍኩት በእሳቱ ላይ ቬንዝን ላለመሆን አስቤ ነበር ። ይሁን እንጂ ነገሮቹ እኛ በምናስበው መንገድ እየሄደልን ላለመሆኑ ከኢትዮጵያ ም/ቦርድ የተሰጣቸው ሕጋዊ ደብዳቤ ይዘው የተቀሳቀሱና ሰላማዊ ትግል እያደረጉ ያሉ የባልዴራስ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በአርባምንጭ መታሰራቸው አንዱና ትንሹ ማሳያ ነው ።

ለእንደነዚህ አይነት ነውር ምክንያት ከሆኑ ነገሮች አንዱ የቀድሞ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት የነበሩ በወረዳ፣ በዞን፣ በክልልና በፌዴራል የተሳሰረ ሰንሰለት ፈጥረው ወደ ሥልጣን ዳግም መመለሳቸውና በቀድሞ መንገድ ለመጓዝ መወሰናቸው ነው ። በደቡብ ክልል ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ክልሉ ባለው መዋቅር በቀዳማዊ ኢህአዴግ ዘመን በራሱ በኢህአዴግ መሥፈርት በሙስናና በሌሎች ብልግና ተገምግመው የተባረሩትን ጨምሮ ከ2010 ወዲህ ሕዝብ ነፃነት ያገኘ መስሎት ያወገዛቸው በሙሉ በሚያስብል ደረጃ ወደ ቀድሞ ሥልጣናቸው መመለሳቸው ሲሆን እኚህ ካድሬዎች በአሸናፊነት ሥሜት ሕዝቡንም ሆነ ተቀዋሚዎችን እየተበቀሉ ይገኛሉ ።

ሌላው ምክንያት አንዳንድ ነገሮች የፌዴራሉ ይሁንታም ጭምር የተቸረው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የፌዴራሉ መንግሥት በሰሜኑ ጦርነት፣ በዓለም አቀፉ ጫናና በመሳሰሉ ጉዳዮች የተወጠረ መሆኑን እንደ መልካም አጋጣሚ መውሰዳቸውን መገመት ይቻላል ። ይህንን በሚመለከትና ለውጡን በሁለት እግር ማቆም የምር ፍላጎት ካላችሁ ምን እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ለብልጽግና ባለቤቶች በተከታታይ ምክር ለግሼ ነበር ። እንዲህ በማለት፦

ተጨማሪ ያንብቡ:  ልጆቿን እዬበላች የማትጠግብ ሀገር - አገሬ አዲስ

«ቀዳማዊ ኢህአዴግ ከወደ አናቱ፤ ዳግማዊ ኢህአዴግ ከወደ እግሩ ነው መበስበስ የጀመሩት» ስለሆነ ብልጽግና የራሱንም ሆነ የሀገራችን ሚዛን ጠብቀው እንዲቆሙ በሁለት እግራቸው እንዲቆሙ ከፈለገ እግሮቹን ያክም፤ በጋንግሪን ላይ ሪፎርም አይሰራም የሚል ምክር መለገሰን አስተውሳለሁ ። የአካል ጋንግሪን እንዳለ ሁሉ የሀሳብ፣ የአስተሳሰብና የአመለካከት ጋንግሪንም አለና። ጋንግሪን ጋንግሪንን አያክምም ካልተባለ በስተቀር ።

በመጨረሻም ሁለት ምክረ ሀሳቦችን ላንሳና እንሰነባበት ።  የመጀመሪያው ለቀዳማዊ ኢህአዴግም ሆነ በእግሩ ለተተካው ብልጽግናም ተቀዋሚዎች የሚናገሩትን የሚሰማ ጆሮ ባትታደሉም አሁንም ጊዜ አላላችሁምና ቆም ብላችሁ አስቡ ። ሁለተኛው እነ አቶ እስክንድር ነጋ’ን በማፈን ወይም የፖለቲካ ምህዳሩን በማጥበብ የሚፈታ የሀገር ችግር የለም!!!

የነገው ጌታ የነገ ሰው ይበለንና እናያለን !!!

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.