በእስር የሚንገላታው ባልደራስ የአደረጃጀት ሥራውን በአዲስ መልክ አጠናክሯል!

rrrr6የኦህዴድ የእስር ዘመቻ ቀዳሚ ሰለባ የሆነው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) እጅግ በተጠናከረ ሁኔታ በአዲስ አበባ የአደረጃጀት እንቅስቃሴውን ቀጥሏል። የፓርቲው የአደረጃጀት ክፍል በሁሉም ክፍለ ከተሞች በአዲስ መልክ አባላትን ማደራጀቱን ቀጥሏል። እስካለፈው ምርጫ 2013 ዓ.ም. ተደራሽ ባልሆነባቸው ሰፈሮች ለመድረስም እየተንቀሳቀሰ ነው።

በከፊል ክፍለ ከተሞች የአመራር ሽግሽጎች የተደረጉ ሲሆን፣ በገሚሶቹ ደግሞ በቅርቡ ይደረጋል። የአዲስ አበባ ኗሪዎች ወደ ባልደራስ በመምጣት የድርጅቱ አባል እንዲሆኑና የከተማቸውን ህልውና እንዲያስጠብቁም የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ጥሪ አቅርበዋል። ባልደራስ ወደ ሀገር አቀፍ ፓርቲነት በማደግ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች አደረጃጀቱን ለማስፋት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

የፊርማ ማሰባሰቡ እንቅስቃሴ በተጀመረባቸው አካባቢዎች ጥሩ ህዝባዊ ምላሽ የተገኘ ሲሆን፣ ከኢትዮጰያ ውጭ ያለውን እንቅስቃሴም በአዲስ መልክ ለማዋቀር ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

(ምንሊክ ሳልሳዊ)

ተጨማሪ ያንብቡ:  በባሌ 2 ሙስሊሞች በመንግስት ቅጥር ነብሰ ገዳዮች ሕይወታቸው መጥፋቱ ተዘገበ

Leave a Reply

Your email address will not be published.