ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታ በ81 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

Fisha destaቤተሰቦቻቸው እንደገለፁት ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ የልብ ሕመም የነበረባቸው ሲሆን ለዚህም በአገር ውስጥና በውጪ ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዋል። ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት የነበሩት ፍሰሐ ሕይወታቸው ያለፈው አርብ ሚያዚያ 28/2014 ዓ. ም. እኩለ ሌሊት አካባቢ ሲሆን የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው እሁድ ሚያዚያ 30/2014 ዓ. ም. በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገልጿል።

ከእስር ከወጡ በኋላ በሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ስላለፉባቸው ሁኔታዎች የሚተርክ “አብዮቱና ትዝታዬ” የሚል መጽሐፍ ያበረከቱ ሲሆን፣ በዚህም “ደርግ በወሰዳቸው በጎ ዕርምጃዎች እንደምደሰት ሁሉ በማወቅ፣ በድፍረት፣ ባለማወቅና በስህተት ለተፈጸሙት ደግሞ ሙሉ ኃላፊነት በመውሰድ በበኩሌ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ” ብለው ነበር።

ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ከመጀመሪያው መጽሐፋቸው በተጨማሪ ሁለተኛ መጽሐፍ በማዘጋጀት ላይ ነበሩ።

ትግራይ አድዋ ውስጥ የተወለዱት ሌፍተናንት ኮሎኔል ፍሰሐ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአደዋ ንግሥተ ሳባ እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃን አዲግራት ውስጥ በሚገኘው አግአዚ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል።

bookበተጨማሪም አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ኮተቤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሩ ሲሆን፣ ከዚያም በኋላ ወደ ሐረር ጦር ትምህርት ቤት ገብተው ከሰለጠኑ በኋላ በክብር ዘበኛ ውስጥ ገብተው በንጉሡ ቤተ መንግሥት ውስጥ ተመድበው አገልግለዋል።

ወደ አሜሪካ በመሄድ ከፍተኛ ወታደራዊ ሥልጠና ወስደዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርት ተከታትለዋል።

ንጉሡን ከሥልጣን ያስወገደው ሕዝባዊ አብዮት ሲፈነዳና በደርግ አማካይነት ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ሲመሠረት ከጦር ኃይሉ ተወጣጥተው የአመራርነት ቦታውን ከያዙት የወቅቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል አንዱ ነበሩ።

ከዓመታት ቆይታ በኋላ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) ሲመሠረት የቀድሞው ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማሪም ምክትል በመሆን የአገሪቱ ሁለተኛ ሰው ለመሆን በቅተው ነበር።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኬንያታ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከአማፂያን ጋር ለ17 ዓመታት የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የቆየው አስተዳደራቸው እየተዳከመ መጥቶ ፕሬዝዳንቱ አገር ለቀው ከተሰደዱ በሳምንታት ውስጥ የአማጺያኑ ስብስብ ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር የኢሕዲሪ መንግሥት ፍጻሜ ሆነ።

ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐን ጨምሮ በአገር ውስጥ የተገኙት የቀድሞው መንግሥት ባለሥልጣናት በአገሪቱ ውስጥ በተፈጸሙ ጭፍጨፋዎችና በሰብአዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ተከሰው ለዓመታት በተካሄደ የፍርድ ሂደት እስር ተፈርዶባቸዋል።

ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታም ለ20 ዓመታት በእስር ካሳለፉ በኋላ ከ10 ዓመት በፊት በይቅርታ መለቀቃቸው ይታወሳል።

2 Comments

  1. Great respect for Fisseha Desta for being the only Derg high official to even hint at the role of foreign intelligence in weakening the Government of Ethiopia in particular, and Ethiopia in general. His book was also the first one to expose that the great munitions depot in Addis was struck by a US cruise missile attack launched from the Indian Ocean.
    Even though the Derg has been involved in great crime against the Ethiopian nation and people in the name of the revolution, Fisseha Desta has been tried in court and paid his dues. Compared to the corrupt-to-the-bone and utterly unpatriotic authorities of TPLF and OPDO that succeeded him, Fisseha could be considered a saint.
    May he rest in peace.

  2. በዘርና በጎሳ ወይም በሃይማኖት ሳይከፋፈሉ ላመኑበት ጉዳይ እስከ ፍጻሜ ድረስ የተዋደቁ ቁጥራቸው እልፍ ነው። እንዲህ ነበር ብሎ ታሪካቸውን የሚዘክርላቸው ጠፋ እንጂ ያኔም ነበሩ ዛሬም ጥቂቶች አሉ፤ ወደፊትም ይኖራለሁ። ኮ/ል ፍስሃ ደስታ በለውጡ ማእበል ገብተው ዋኝተውና አስዋኝተው እስከ መጨረሻው ድረስ ዘላባጅ ፓለቲከኞችን ተፋልመው አልፈዋል። በደርግ ጊዜ ለሆነው ሁሉ ደርግን ብቻ ተጠያቂ የሚያደርገው የዛሬው የከፋ አሰላለፍ ትሻልን ትቼ ትብስን ህዝባችን እንዲል አድርጎታል። እርግጥ ነው የደርግ ዘመን የጨለማ ዘመን ነበር። ግን በሃገር ፍቅርና በህዝቦች ጥምረት ደርግ አያመነታም። በሻቢያና በወያኔ ሴራ በምዕራባዊያን ድጋፍና በአሜሪካ መሪነት በመጨረሻው ሰአት አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ደርግ አንድ ጥይትና አንድ ሰው እስኪቀር እያለ አፋክሮ እንዲያ መፍረክረኩ የሃገራችን የበፊትና የአሁን የፓለቲካ ቱልቱላነት ያሳያል። ሲጀመር አንድ ሰውና እንድ ጥይት ብሎ ነገር የለም። ግን የራስን ባህሪ ሳይገቱ ተፈጥሮን እንቆጣጠራለን እያሉ ክንዳቸውን አንስተው በየመድረኩ የጮኹት እነዚያ ወታደራዊ ገዥዎች በህልማቸውም ቢሆን ወያኔ በአዲስ አበባ ሻቢያ በአስመራ የሃገር መሪዎች ይሆናሉ ብለው አስበው አያውቁም ነበር። የሆነው ሆነና ለዛሬ በቅተናል። የዛሬው የምድሪቱ የፓለቲካ ሽኩቻ ደግሞ ጊዜውን ተገን አርጎ አንድን እያቆራቆሰ፤ በውብ ቃሎች ሰውን እያታለለ ይነጉዳል። ፍጻሜው ምን ይሆን?
    በመሰረቱ ኮ/ሌ ፍስሃ ደስታ 17 ዓመት በስልጣን፤ 20 ዓመት በወያኔ እስር ታስቦ ከ 81 ላይ 37 ሲቀነስ ተራፊው ጊዜአቸውና የእፎይታና የሰላም ጊዜአቸው ጥቂት ናት። ግን ምን ይደረግ አንድ ጊዜ ኢትዮጵያዊ ሆነን ተወልደናልና መከራውም ደስታውም፤ መራብና መጠማቱም የጊዜው ታፔላችን ሆኗል። ሞቱ ከሚለው ይልቅ አረፉ የሚለው ቃል ይመቸኛል። ለክፉም ለደጉም እናመሰግናለን። ለቤተሰብና ለወዳጆች ሁሉ መጽናናት ይሁንላችሁ። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.