እናት

Happy Mothers dayእናት  ልክ እንደ ለም  መሬት 
መሐፀኗ ፤ አብቃይ ነው ሰውነት ፡፡
ይኽ የዓለም ህዝብ  ወንድ  ሴት
ከእናት መሐፀን የወጣ ነው በራቁትነት ፡፡
እናት …
ወድና ሴትን አፈራች  …
በማሃፀን በደም ስሯ እያጠባች ፡፡
ዘጠኝ ወር በመሐፀኗ ተሸክማ
በጭንቅ ዓምጣ  የወለደች …
ጡቷን አጥብታም ያሳደገች ፡፡
እናት …
ፍቅር ናት ፡፡
 
ብሽቅ ፖለቲካ ፤ የማይነካካት …
የዓለም ዜጋነት ።
ዓለምን አቃፊነት
ድንበር የማይገድባት
ፍቅር ብቻ የሚገዛት
እንዲህ  ናትእናት 
አባታዊ አምባገነንት
ሲያልፍም አይነካት ፡፡
 ሚያዚያ 30 ቀን /2014 ዓ/ም ( ለእናቶች ቀን መታሰቢያ ይሁንልኝ )
 

ተጨማሪ ያንብቡ:  “አማራጩ መንገድ በሰላማዊና ወንድማማችነት መኖር ነው” - አንዷለም አራጌ ደራሲና ፖለቲከኛ

Leave a Reply

Your email address will not be published.