የስብዓዊ ማዕበል የጦርነት ስልት ከሽፎል፣ እልፍ አእላፍ ወጣቶች ረግፈዋል!!! ዳግማዊው “ህዝባዊ ሠራዊት፣ለህዝባዊ ጦርነት!” እልቂትም ተደግሏል!!!

r544rrr/ ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)

‹‹የማምነው እንደዛ ነው:: እነዚህ በማፕ ላይ ያሉ መስመሮች በእውኑ ዓለም፣ በምድር ላይ የሉም፣ መሬት ላይ አናያቸውም፡፡ በእኔ ህልም አንድ ቀን መስመሮቹ ከካርታው ላይ ይጠፋሉ፡፡ በመጨረሻውም ሁላችንም አንድ ህዘብ ሆነን መሬት በሚባለው ፕላኔት ላይ እኖራለን፡፡›› ያኒ ‹‹በድንበር የለሽ ዓለም›› “It’s what I believe. These lines that are in the maps, they really don’t exist. They’re not on the ground. I don’t see them. My dream is that some day, they will fade away. And finally we will realize that we are all one people living in this one magical place called Earth.” Yanni On “World Without Borders” tour

 • ‹‹ኦሮሞ ነኝ አማራም ነኝ፣ ሁሉም ነኝ ›› መሃመድ አል አሩሲ
 • ‹‹አምነስቲበኢትዮጵያ ላይ የሚያወጣው መግለጫ አሜሪካ ኢራቅን በወረረችበት ሰአት የሚሰጠውን መግለጫ ነው። ስንትሺ ህዝብ በማንነቱ ተጨፍጭፎ ያንን ጨፍጫፊ ሀይል ከማውገዝ ይልቅ ተጨፍጫፊውን ከአካባቢው ይልቀቅ ይላል።›› ሱሊማን አብደላ
 • ‹‹ህወሃ ት የሚሰራውን ወንጀል በፍጥነት እና ጥራት የሚሰራ ኦህዴድ ነው የመጣው›› ታምራት ነገራ
 • ‹‹ጦርነቱ ኢትዮጵያን የመታደግ ሳይሆን የአብይ አህመድን ስልጣን ለመታደግ ነው፡፡ የማዝነው የአብይ አህመድን ስልጣን ለማስጠበቅ ለሚያልቀው አማራ ነው፤ የአማራ ኢሊቶች ማስብ የምትጀምሩት ስንት አማራ ሲያልቅ ይሆን!›› ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድ
 • በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉድሩ ወለጋ አሙሩ ወረዳ ውስጥ የሚኖሩ አንድ አርሶ አደር ሲነግሩኝ፡- የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በዚህ መጡ በዚህ ገቡ ብለን ለኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል ፖሊስ ስንጠቁም‹‹ እነሱ እኮ አገራቸው ነው፡፡ ከፈለጋችሁ እናንተ ወደ አገራችሁ ሂዱ አሉን፡፡›› ……‹‹የመሳሪያ መደብር ተከፍቶ እየተሸጠ ነው!!!›› ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፡፡  አንባገነኑ ጁንታው የአብይ መንግሥት፣ ጎበዜ ሲሳይ በአስቸኳይ ይፈታ!!!
 • ‹‹ትልቁ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግር የኦሮሞ ፖለቲካ ነው!!!››….‹‹ጠቅላይ ሚንስትሩ ሰበካው ላይ ብቻ ሳይሆን ተግባሩ ላይም ቢበረቱ ›› ጋዜጠኛ አበበ በለው
 • ‹‹የአብይ ቡድን የትግራይን  ማጥፍት ቀዳሚ ዓላማ ነበረው፣ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ ያወጁትን  ጀኖሳይድ ጦርነት ለማሳካት ቀዳሚ ተግባራቸው ወጣቱን ማጥፋት እንደሆነ የትግራይ ወጣቶች ማህበር አስታወቀ በጃኖሳይድ ጦርነቱ ምክንያት ከሶስት መቶ ሺ በላይ የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶች እድራሻቸው እንደማይታወቅ የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ሓላፊ ማሓሪ አዳነ ገልፆል፡፡ ›› …….‹‹ትግራይ ቴሌቪዥን አማርኛ››

· ‹‹ የእነዚህ የእናቶች ድምዕ በትግራይና በኢትዮጵያ ያስተጋባል፣ እስከዛሬ ድምፃቸው አይሰማም ነበር፡፡በአሸባሪው ህወሓት በተጀመረው ጦርነት፣ የጦርነቱ ሠለባዎች ናቸው፡፡ ›› “These are the voices of mothers in Tigray, Ethiopia. Until now, they have been rendered voiceless. They are victims of the war started by the terrorist organization, the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) in Nov 2020.” ሔርሜላ አረጋዊ፣……………………(1)

· ‹‹የዛሬ የትግራይ ወጣቶች በተሳሳተው የህወሓት የታሪክ ትርክት፣ የውሽት ባህል እና በአፍሪካ አዲስ በተፈበረከው የማንነት ጥያቄ መሳሪያ በማድረግ የተስፋፋው የህወሓት ጠባብ ብሔርተኛነት የውሸት መንገድ መቀጠል የለባቸውም ››Early ex-TPLF recruit Kidane Afeworki is speaking out so the youth today aren’t misled like he was. Afeworki says, Tigray  ኪዳኔ አፈወርቂ

ሔርሜላ አረጋዊ፣ ከቀድሞው የህወሓት አባል ኪዳኔ አፈወርቂ ጋር ያደረገቸው ቃለ-መጠይቅ የትግራይ ወጣቶች በህወሓት የውሸት የታሪክ ትርክት ተሳስተው በጦርነት እንዳይማገዱ የወያኔን ትልቅ ውሸት እንደሱ እንዳይታለሉ ወጣቶችን የሚያስገነዝብ ትምህርታዊ ውይይት ስለሆነ መደመጥ ይኖርበታል እንላለን፡፡ “We Were Lied To”: How Story, Culture & Manufactured Identities are Weaponized in Africa  ( May 1, 2022 • I speak with former TPLF member Kidane Afeworki about…) Early ex-TPLF recruit: I am speaking out so young people from Tigray don’t continue to be misled by the fraudulent Tigray People’s Liberation Front, like I was፡ TPLF & the Big Tigray Lie: A Cautionary Tale ………(2)

ተጨማሪ ያንብቡ:  ታምራት ላይኔና አማረ (ክፍል-2) - (ከኢየሩሳሌም አ.)

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሃገሪቱን  ሉዓላዊነት ለመታደግ ሳይሆን የአብይንና የደብረፂዮን ስልጣን ለመታደግ ሲሆን በህዝባዊ መዕበል እየተመመ ወደ ጦርነቱ እሳት የሚገባ የአማራ ወጣቶች፣ የአፋር ወጣቶች፣ ትግራይ ወጣቶች፣ ወዘተ    በመጀመሪያው ጦርነት ግማሽ ሚሊዮን ወጣቶች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በ2014 ዓ/ም የክረምት ወራት ለመጀመር በዝግጅት ላይ የሚገኙት የህወሓትና የብልፅግና ‹‹ህዝባዊ ሠራዊት›› ሚሊዮን የአማራ፣አፋር፣ የትግራይ ወዘተ  ወጣቶችን በማሰልጠንና በማደራጀት ‹‹ህዝባዊ ጦርነት›› ለማካሄድ በከሸፈ ‹‹የስብዓዊ ማዕበል የጦርነት ስልት››፣ የእግረኛ ሠራዊት እልቂት ለመድገም በሰኔ ወር ድግስ ተደግሏል!!!  ጥንት ጠመንጃዎቹ አንድ ጎርሰው የሚተኮሱ፣ ቆመህ ጠብቀኝ፣ የሚባሉ  ዲሞትፎር፣ ቤልጂግ፣ ሰነኔ፣ ነጭ ቃታ ቤልጂግ፣ሞውዤር ወዘተ አነስተኛ የተኩስ አቅም ያላቸው ዘመን ነበር የሰው ማዕበል በመላክ ከጠላት ምሽግ ገብቶ በእጅ መተናነቅ የጦርነት ስልት የነበረው፡፡

‹‹ “The human wave attack, also known as the human sea attack,[1] is an offensive infantry tactic in which an attacker conducts an unprotected frontal assault with densely oncentrated infantry formations against the enemy line, intended to overrun and overwhelm the defenders by engaging in melee combat. The name refers to the concept of a coordinated mass of soldiers falling upon an enemy force and sweeping them away with sheer weight and momentum, like an ocean wave breaking on a beach.” (From Wikipedia, the free encyclopedia)››

አብይና ደብረፂዮን ወጣቶችን የሚማግዱበት የጣረ-ሞት የጦርነት ዘመቻ ደግሰዋል፡፡ ጦርነትን በወታደር ብዛት፣ በሰዎች ጎርፋና ማዕበል ጦርነትን ማሸነፍ፣ የጦር መሳሪያው የመተኮስ አቅም ዝቅተኛ የነበረበት ዘመን ሲሆን በዚህ  ዘመን ጊዜ ያለፈበት ‹‹ህዝባዊ ሠራዊት፣ ለህዝባዊ ጦርነት›› የከሸፈ የጦርነት ስልት ነው፡፡ በህወሓትና ብልፅግና የእግረኛ ሠራዊት እንደቅጠል እንዲረግፍ የሚያደርግ እልቂት በሰኔ ወር ደግም ተደግሏል !!! ዘመናዊው የጦርነት ስልት በጦር መሳሪያው ዓይነትና ብዛት የማውድም ኃይል የሚለካ ሲሆን ለምሳሌ ዘ ሄክለር እና ኮች ጂ አስራአንድ  ጠመንጃ   (The Heckler and Koch G11 Assault Rifle Can Fire 2,100 Rounds Per Minute) በደቂቃ 2100 በአንድ ዙር ጥይቶች  የመተኮስ አቅም ሲኖረው፣ በሰዓት መቶ ሃያ ስድስት ሽህ፣በቀን ሦስት ሚሊዮን ሃያ አራት ሽህ ጥይቶች የመተኮስ አቅም ስላለው፣ ምንያህል ወታደሮች እንደሚፈጂ በዚህ ቀላል ምሳሌ መረዳት ይቻላል፡፡ አንድ እናት አንድ ህፃን ለማሳደግ አስራ ስምንት አመታት ሲፈጅባት፣ ዘ ሄክለር እና ኮች ጂ አስራአንድ በደቂቃዎች የጠመንጃ ቃታ በመሳብ ሚሊዮኖች እንዴት እንደሚያልቁ ያስረዳል፡፡ ፋየር ፓወር፡- የመተኮስ አቅምና የማውደም አቅም መለኪያ ሲሆን ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎች ጠመንጃዎች፣ ሚሳኤሎች፣ወታደራዊ ኃይል (የሰው ኃይል ቁጥርና የመሳሪያ ዓይነትና ብዛት ያገናዘበ መለኪያ ነው፡፡) fire-power፤-the destructive capacity of guns, missiles, or a military force (used with reference to the number and size of guns available).

በአፄ ሚኒሊክ የአድዋ ጦርነት በአስራስምንተኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ‹‹ህዝባዊ ሠራዊት፣ ለህዝባዊ ጦርነት›› ሰልትን በመጠቀም የጦልያን ጦርን አሸንፈዋል፡፡ እግረኛ ሠራዊት እንደ አንበጣ ወረራ በእልፍ ወታደሮች የጠላት ምሽግን፣ ታንክን፣ ከባድ መሣሪያዎችን በድንገት በማጥቃት በሰው ኃይል የማሸነፍ የውጊያ ስልት ነበር፡፡ አብይና ደብረፂዮን በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን  ይህን ስልት በመተግበር ሚሊዮን ወጣቶችን በጦርነት በመማገድ ላይ ይገኛሉ፡፡  በእልፍ ጦር በድንገት የማጥቃት እምነትና ህግ መሠረት ‹‹ትክክለኛ የጦር መሣሪያ ከመጠን በላይ አድርጎ መገመት፣ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው በጣም ጥሩ ዘመናይ የጦር መሣሪያ የድል መንገድ ጠራጊ ነው ፡፡›› “Mass assault doctrine: “Perfect” weapons are overrated a large number of “good enough” weapons is the path to victory” የወታደር ብዛት የስብዕዊ ማዕበል ዘመን አከተመ፡፡ ዛሬ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ ዓይነትና ብዛት በአነስተኛ የሰው ኃይል የጦርነት ስልት ዘመን ተተክቶል የእስራኤልና የአረቦች ጦርነትን ልብ ይበሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኦሮሞ ጠባብ ብሔርተኞች ለኦሮሞ ሕዝብ ያላቸው ጥያቄ ምንድ ነው? - በፈቃዱ ኃይሉ

 

ስብዓዊ ማዕበል፣(human waves) የቻይናዎች የጦርነት ስልት ነው፣ ብዙ እግረኛ ጦር ሠራዊቶች፣ ጠላታቸውን ለማጥቃት ወደፊት በመገስገስ በጦርነት ዘመቻ የሚተሙበት ታክቲክና ስትራቴጅ ሲሆን ዓላማውም በሁለቱም  ጎራ በሠራዊት ጎርፍ፣ በእግረኛ ወታደር ማዕበል በማሰለፍ በሙታን ላይ እየተረማመዱ ወደፊት የሚተሙበት አሰቃቂ ሰው ሰው ያልሸተተ የጦር ስልት ነው፡፡ ዘመናዊ የጦርነት ስልት ለአንድ ወታደር ህይወት የሚጨነቅ ሲሆን አመራሩም  የዘመኑን የወታደራዊ ሳይንስ የተማሩና ስብዓዊነትን የተላበሱ መሪዎች መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ‹‹The Chinese tactic meaning human waves was a charge of too many soldiers, too many soldiers rushing forward in attacks against their opponents.›› (Dec 13, 2021) የብልፅግና ህወሓት የጦር አበጋዞች በሰሜኑ ጦርነት ዘመን ባለፈበት ታክቲክና ስትራቴጅ፣ በሁለቱም ወገን ህዝባዊ እግረኛ ሠራዊት እንደ መንጋ በማሰለፍ በግንባር በማሰማራት ወጣቶቹን ቦንብ ጠራጊ፣ ጥይት አብራጅ፣  ምሽግ ደርማሽ፣ የታንክ አጋች፣ የጠብመንጃ አፈሙዝ ያዥ፣ በማድረግ የምስኪኖቹን እልፍ አእላፍ ወጣቶችን ህይወት አስገበሩ፡፡  የብልፅግና ህወሓት የጦርአበጋዞች የሥልጣን መንበራቸውን ለማስጠበቅ በውሽት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት አንደኛው ሌላኛውን በሃገር ክህደት፣ በአገር በመሸጥ፣ በሃገር ላይ በማሴር  ወንጀል ወዘተ በመካሰስ የእርስ በእርስ ፀባቸውን  በህዝብ ስም በሃገር ስም በማድረግ አንድን ህዝብ ለሁለት ከፍለው ወንድም ወንድሙን እንዲወጋ፣ ጦር እንዲሰብቅ፣ ጋሻ እንዲነቀንቅ፣ እንዲፎክር እንዲያቅራራ በማድረግ  የወጣቶችን ህሊና በማጠብ ውድ ህይወታቸውን በከንቱ እንዲያጡ አደረጉ፡፡  ለአብይና ደብረፂዮንና ኢሳያስ ጂኒ ህይወትታቸውን እንዲገብሩ ‹‹ወጣት የነብር ጣት!!!››…‹‹ማን ይፈራል ሞት!…ማን ይፈራል!›› በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ወጣቶቹን ‹‹በእናት ሃገር ስም›› ‹‹በእምዬ ኢትዮጵያ ስም›› ‹‹በትግራዋይ ስም›› ወጣቶችን ለመስዋትነት ያቀረቡበት ለሃገራችን ህዝብ ጨለማው ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ነው፡፡

“Who does not shudder to hear of the “human wave” tactics reportedly being used by Iran in its invasion of Iraq? The phrase summons up the image of thousands, perhaps tens of thousands of soldiers, many still young boys, marching “fanatically” to certain death for a cause rendered dubious fecisely by the extreme means employed to serve it. Often the term, human wave, comes with a definition of it as a “Chinese tactic,” from the Korean War. The implication is that Western or white soldiers would never lend themselves to any such mass display of mindlessness and barbarism.”…………..(3)

ተጨማሪ ያንብቡ:  ያልተቀደሰው ጋብቻ (ኢህአዴግ፣ ፋና፣ ኢብኮ፣ ምርጫ ቦርድ) -ጌታቸው ሺፈራው

ሰብዓዊ ማዕበል “human wave” የጦርነት ስልት ኢራንና ኢራቅ በወረረች ጊዜ  ተጠቅማበት ነበር፡፡ በጦርነት በሽዎችና በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች  ወደ ጦርነት ዘመቻ ተመሙ በጭፉን እምነትና በከንቱ የሃገር ፍቅር ስሜት ወደሚጠበቀው ሞት አመሩ፡፡ የሰው ማዕበል ‹‹የቻይናዎች ስልት›› ሲሆን በሰሜን ኮርያ ጦርነት ጊዜ የተገበሩት የጦርነት ስልት ነበር፡፡ እንድምታውም ምዕራባዊያን ወይንም  የነጭ ወታደሮች በፍፁም እራሳቸውን በጅምላ ማቅረብ፣ እራሳቸውን በመንጋ ማሳየት በድንቁርና ያለመሠልጠንና አረመኔያዊነትና  ኃላቀርነት ነው፡፡ ሰው ሰው ያልሸተተውን የጦርነት ስልትን በመሆኑ የጦርነት ስልቱን አይቀበሉም ፡፡ የአንበጣ ወረራ ፀሓይን ይጋርዳል፣ የምድር እፅዋትንና ሠብልን ዶጋ አመድ አድርጎ ወደፊት ይገሠግሳል፡፡ ስብዓዊ ማዕበል የጦርነት ዘመቻ የረገፈው ረግፎ፣ በደመነፍሳቸው በሙታኖች ሬሳ ላይ እየተረማመዱ የመዋጋት ስልት ሲሆን፣ እንደ አንበጣ ወረራ ምግብ ፍለጋ ወደፊት ብቻ የመገስገስ ዓይነት ነው፡፡

በመጨረሻም በዓለማችን ከ2013 እኤአ ጀምሮ ሰው ሠራሽ ክህሎት (Artificial Intelligence (AI) ሮቦቶች ወይም ማሽኖች ከሰው ልጆች የተሸለ ይሠራሉ፣ አይሠሩም በዓለም አቀፍ የጦፈ ክርክር ያስነሳ ውይይት ነበር፡፡  ሮቦቶች (ሰው ዓልባ ድሮኖች፣መኪኖች ወዘተ) አስተማማኝና እንከን የለሽ የጦር መሳሪያ ዘመናዊ ስርዓት ሆነዋልን? በዓለም አቀፍ ስብዓዊ መብቶቸ ህግጋትም ሮቦቶች ሴቶቸን አይደፍሩም፣ወይም የጦር ወንጀል አይፈፅሙምን? ሮቦቶችና የሥነ-ዜጋን የሞራልና ስብአዊነትን የተላበሰ ተግባር በመፈፀም ከስብዓዊ ወታደሮች ጋር ሲነፃፀር  የተሸሉ መሆናቸው ይታመናል፡፡ “When the international debate over fully autonomous weapons began in 2013, a common question was whether robots or machines would perform better than humans. Could providing more autonomy in weapons systems result in greater accuracy and precision? Could such weapons increase compliance with international humanitarian laws because they would not rape or commit other war crimes? Would they “perform more ethically than human soldiers,” as one roboticist claimed?”………..(4)

በምድረ እንግሊዝ በሰው ሰራሽ ክህሎት የተሠሩ ሮቦቶች በወህኒ ቤቶች ያሉ እስረኞችን አጥርና ከተንበሬ መዕልት ወ ለሊት  እስረኞች እንዳያመልጡ ይጠብቃሉ፡፡ እንደ ጢያራዋ ሰው አልባ ድሮውን ወደፊት እግረኛ ሰው ሰራሽ ወታደራዊ ሮቦቶች ከህያው ወታደሮች ጋር የሚዋጉበት የዲጅታል ቴክኖሎጅ ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ በጦርነት ጥርሳችንን ነቅለናል ለሚሉት የዘመናችን ሲሊቨስትሪ ስታሊየኖች አብይና ደብረፂዮንና ኢሳያስ፣ የጦር አበጋዞች ወጣቶችን በእሳት መማገድ በእግዚያብሄር ያስጠይቃል እንላለን፡፡ ለዓለም አቀፍ የጦር ፍርድ ቤት መቅረባችሁ ግን በፍፁም አይቀርም፡፡ መንግሥት ያልፋሉ ህዝብ ግን አያልፍም፡፡የኤርትራ፣ የትግራይ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ጥንት እንደ ጠዋቱ በፍቅር፣ በሠላምና በአንድነት ይኖራል፡፡

 

ወጣቶች እራሳችሁን ከጦርነት አግልሉ!!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅ!!!

ምንጭ

(1) https://youtu.be/7cbwBgnYU5Q

(2) (653) “We Were Lied To”: How Story, Culture & Manufactured Identities are Weaponized in Africa – YouTube)

(3) ‘Human Waves’ – The Washington Post/By Stephen S. Rosenfeld/March 9, 1984

(4) Robots aren’t better soldiers than humans/ The Boston globe/ mary wareham/ Oct. 26, 2020

2 Comments

 1. የሃገሮች ወሰን፤ ስም፤ ማንነት ጦር ባሰለፉና ጉልበተኛ በሆኑ መንግስታት በዘመናት መካከል በዚህም በዚያም እያሳበቡ ሲያሰፉት፤ ሲያጠቡት፤ ከአንድ ነጥቀው ለራሳቸው ሲያረጉት ወይንም ለታዘዘላቸው ሲሸልሙት ኖረዋል። በመሰረቱ ሃገር ማለት ሰው የተወለደበት ሥፍራ ማለት አይደለም። የሰው ልጅ መብቱ ተከብሮ በሰላም ሰርቶ ወልዶ ከብዶ የሚኖርበት ሥፍራ እንጂ። በነጻነት ስም በየዋሻው ገብተው እልፍ ደም ካፈሰሱ በህዋላ የከተማ አለቆች ሲሆኑ ድርጊታቸው ከተፋለሙት ገዥ ሃይል ሲከፋ ምኑ ላይ ነው ነጻነቱ? ደግሞስ የአንዲት ሃገር ባንዲራ (ሰንደቅ) በከፍታ ስፍራ ላይ መውለብለቡ ብቻውን የህዝቦች ነጻነት ምልክት ሊሆን ይችላል? በጭራሽ። የማምለክ፤ የመሰብሰብ፤ የመናገር፤ ከላይ እንደተባለው በሰላም ገብቶ የማድርና ለህግ ተገዥ ሆኖ ገፊዎችንና ዘራፊዎችን ለፍርድ የማያቀርብ ሃገር ለስሙ ሃገር ይባል እንጂ የተኩላዎች መናህሪያ ነው። የትግራይ ወጣቶች በምንም ሂሳብ ቢሆን በወያኔ የፈጠራ ታሪክ ተጠልፈው ዛሬም ትላንትናም ሊሞቱ አይገባም ነበር። ግን ይህ ሁሉ መግደልና መገዳደል የሚፈጸመው አንድ አንድን በመፍራት በጅምላ አስተሳሰብ ስለሚራመድ ነው። በጦርነት መካከል ከህዋላ ሆኖ ከሚመታህ ወገንህ እንዴት ስብዕናን ትጠይቃለህ? ወያኔዎች አብደው ምድሪቱን ካሳበድ ቆዪ። የጠፋው የእብደታቸው ማርከሻ ነው። የትግራይን ወጣቶች አስጨርሰው ትርፋቸው ምን ሊሆን ነው? ስንቱን አስረህ ገድለህ ትጨርሰዋለህ? በሃበሻዋ ምድር የአስተሳሰብ ለውጥ እስካልመጣ ድረስ መገዳደላችን ይቀጥላል። ያው ወያኔ ቀዳሚው ደም አፍሳሽ ይሁን ሌሎችም ከገጠር እስከ ከተማ ሃገር አፍራሽና ሰላም አደፍራሽ ተግባር በመፈጸም ላይ ይገኛሉ። የኢትዪጵያ ችግር ድርብርብ ነው። እንደ ሽንኩርት ልጣጭ አንድን ሲቀርፉት ሌላው ይተካል። ዛሬ የምናየው የድርቡሽ ሥራ ክፋቱ ሰማይ ደረሰ እንጂ ድሮውንም ቢሆን እርስ በእርስ ከመሸራገድ ተቆጥበን አናውቅም። ሞት በሃበሻው ምድር ሳይታሰብ ሳይሆን አስቦ አሰላስሎ ነው የየሰውን በር የሚያንኳኳው። ለምን ቢሉ ተላላኪና ሥራ አስፈጻሚው ብዙ ነውና! መሬት ሰላም ከሌለበት ለሰው ልጅ ምኑ ነው። ሃገር አብረው ካልኖሩበት አጥርና ክልል እያበጅ አትለፍብኝ ካልን ስልጣኔውና አብሮ የመኖር እሳቤው ለእኔ ብቻ ለሚለውም ድኩማን አይጠቅመውም።
  ሃበሻው ራሱን ፈትሾ፤ ዓለምና ዙሪያዋን ገምግሞ የፓለቲካና የሶሻል እይታውን እስካልሞረደ ድረስ ሁሌ ሲያሳድድና ሲሳደድ መኖር ከመኖር አይቆጠርም። በዚህ ላይ እኔን እጅግ የሚያበሳጨኝ በየስፍራው የፈጣሪን ስም እያነሱ ቱልቱላ የሚነፉ ፓለቲከኞችና ለሰማይ አድረናል የሚሉ አወናባጆች ናቸው። ሥራህና ተግባርህ የድርቡሽ ሆኖ እንዴት ባለ ሂሳብ ነው ስለ ሰማይ አምላክና ስለ ቸርነቱ የምታስተምረው? ፍርድ ለተዛባባቸው፤ በግፍ በእስር ላሉ፤ ዘርና ወገን፤ ክልልና ቋንቋን ተገን በማድረግ ግፍ የሚደርስባቸውን ሰዎች መደገፍ፤ ስለ እነርሱ ድምጽ መሆን የማይፈልግ የእስልምናም ሆነ የክርስትና እምነት ተከታይ ቃና የለሽ ቃጭል ነው። ሰው ማደንቆር ብቻ። በከንቱ የፈጣሪን ስም በዚህም በዚያም እያነሱ የመኖሪያ ብልሃት እንደሚፈልጉት የውሸት ፓስተሮች፤ ነብያቶች፤ ሃዋሪያትና ቀሳውስት ዝም ብሎ የማይኖሩበትን ነገር በሌላው ላይ መጫን ራስን ከእውነት ጋር ማላተም ነው። በዚህ ዙሪያ ላይ እውቁ አቶ ከበደ ሚካኤል ከጻፉት ግጥም የተወሰኑ ስንኞችን ተውሼ ሃሳቤን ልቋጭ።
  ዓይን የለውም አሉ የሰነፍ ልመና
  ወደ አምላክ ሲጸልይ ማታ በልቦና
  መንገድ ሳይመታኝ ባቧራ በጭቃ
  አድርገኝ ይለዋል ላገሬ እንድበቃ
  እንጦጦ ተኝቼ ሃረር እንድነቃ።
  በቃኝ!

 2. The TPLF also used human waves during the 1998-2000 wars with Eritrea. According to the eye witness accounts of the survivors,the TPLF offensive with human waves were mainly composed of Oromo and Amhara recruits who had to clear mines too. The Tigray forces were stationed behind all the human waves to kill those who might retreat. They killed many o f those who retreated. The TPLF reportedly used the same tactics with its Tigray forces when it invaded the Afar and Amhara regions.

Leave a Reply

Your email address will not be published.