“የተፈፀሙ ወንጀሎች ነጥረው ስለወጡ፣ እውነታ ስለታወቀና ተፃራሪ ቡድኖች እጅ ለእጅ ስለተጨባበጡ ብቻ እርቅና ሰላም አይመጣም። “

ኢትዮጵያ የሃገራዊ የውይይት መድረክ ግምገማ

መግቢያ

ሃገራዊ የውይይት /National Dialogue/ መድረክ በተለያዩ ሃገራት ተከናውኗል ነገር ግን ውጤታማ የሆነው  እፍኝ በማይሞሉ አገራት ነው።

ለምሳሌ ያህል በሩዋንዳ “በሁቱና ቱትሲ” የዘር ጭፍጨፋ ፣ በሳውዝ አፍሪካ” አፓርታይድ አገዛዝንና ኤንሲ/ANC/” ፣ ላይቤሪያ ፣ በኬኒያው የምርጫ ወቅት የተነሳው ግጭት ወ.ዘ.ተ. የተከወኑ አገራዊ ምክክሮች /Public Dialogues/ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው።

ከላይ ከጠቀስኳቸው የምክክር መድረኮች የተዋጣለትና በስኬት የተጠናቀቀው የሩዋንዳው “ቱትሲና ኡቱ” ድርድር ነበር።

የተቀሩት ግን የሚጠበቅባቸውን የድርድር ስርአትና አካኤድ ስላልተከተሉ ውጤታማ አልሆኑም።

በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ ከዚህ በፊት እንደገለፅኩት በተለያየ መንግስታት ብዙ አገራው የምክክር መድረኮች ተሰይመዋል አብዛኞቹ አንዱ አንዱን እንዲያሳድድና እንዲበላሉ ከማድረግ በስተቀር ያለ ውጤት ከስመዋል።

የዚህ ክስተት ምክንያት ደግሞ በኢትዮጵያ የተቋቋሙት ኮሚሽኖች ሆነ የመማክርት ጉባኤዎች በመንግስት ሽረባ ስለሚመሰረቱ፣ የመንግስት ጣልቃ ገብነትና ተፅህኖ ስለሚያጋጥማቸውና ህጋዊ አካሄድን ተከትለው ስለማይሰየሙ ለጥቂት ቀናት ወንበር አሙቀው ይፈረካከሳሉ።

ከነዚህም ውስጥ ለመጥቀስ የደንበርና ወሰን ኮሚሽን፣ የኢንቨስትመንት /Privatization commission/ ፣ የሰላም ኮሚሽን፣ ቪዥን ኢትዮጵያ ወ.ዘ.ተ. ናቸው። አንዳንዶቹ አሁንም ያሉ ቢመስልም ፣ አሉ ለማለት አያስደፍርም።

የተፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀሎች፣ ማፈናቀሎች ወ.ዘ.ተ. እውነታዎች ነጥረው ስለ ወጡ ፣ በሁለት ጎራ በተቃዋሚነት የሚናረቱት/የሚዋጉት/ ቡድኖች እጅ ለእጅ ስለተጨባበጡ ዕርቅና ስምምነት ይመጣል ለማለት በታሪክ እንዳየነው ያስቸግራል።

ወደ ኢትዮጵያ ሃገራዊ ድርድር/Nation Dialogue/ና ዕርቅ /National reconciliation/ ዝግጅት ስንመጣ ወደ ሃገራዊ ምክክር መድረክ ከመገባቱ በፊት መሟላት ያለባቸው የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታወች ሊጠበቁ የግድ ይላል። እነሱም፣

  • ትክክለኛሃገርና ህዝብ የተግባባቸውና ስምምነት የተደረሰባቸውን ታሪኮች አንጥሮ ማውጣትና ህዝብን ማስተማር የመጀመሪያውና ዋናው ወደ ሃገራዊ ምክክር መንደርደሪያ  ስልት ነው ፣

በየመድረኩ የሚደሰኮሩ ሰው ሰራሽ /Fabricated/ ታሪኮች ሊገመገሙ፣ሊተቹና ታርመው ትክክለኛው የኢትዮጵያ ታሪክ ሊዘገብና ትውልዱ ሊማረውና ሊያውቀው የግድ ይላል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በወቅታዊ ሀገራዊና ድርጅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን አሳለፈ

የተመዘገቡና ያልተመዘገቡ የኢትዮጵያ ታሪኮች በታሪክ ሙሁራን፣ በአረጋዊያንና በተመራማሪዎች ለክርክር ቀርበው ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ታሪክ ማህበረሰቡ ሊያውቀው የግድ ይላል።

ፈረንጆች እኛን እርስ በርስ አፋጅተው እነሱ ሃገረ ኢትዮጵያን እንደ ልባቸው ሊንቀባረሩባትና የተፋጥሮ ሃብታችን ሊመዘብሩ ያስቀመጡልን ታሪኮች ወደ ጎን ልንላቸው ይገባል።

  • ሕዝብየጨፈጨፉ፣ እንዲጨፈጨፍ መመሪያ የሰጡ ፣ ያፈናቀሉ፣ ያንኮላሹ ፣ የደፈሩ ወ.ዘ.ተ. ማን ይሆን ማን ወንጀል ፈፅመዋል የሚባሉ ሁሉ ህግ ፊት ቀርበው አግባብነት ያለውን ቅጣት ሊያገኙ የግድ ይላል፣

 

  • ያለአግባብ የተበደሉ ቡድኖችና ግለሰቦች የደረሰባቸውን ወንጀል፣ በደል፣ መፈናቀል፣ የአካል ጉዳት ፣ የአዕምሮ መጎዳት ለመጠገንና ለማስረሳት የካሳ /Reparations/ ክፍያ ሊመቻችላቸው ይገባል፣

 

4)በጉልበት ፣ በብልጠት፣ በግለኝነት፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማግኘት፣ ከሌላው ህብረተሰብ በተለየ መልኩ ለማደግና የግል ዕድገትን የመጨቆኛ መሳሪያ ለማድረግ ታስቦባት (Intentionally) ተቆርሰው የተወሰድ መሬቶች ለነባርና በታሪክ ባለቤት ለሆኑ ህዝቦች ሊመለሱ ይገባል፣

 

  • ሕዝብንእንደ ህዝብ የሚያቃቅሩ፣ ለሃገር አንድነት ሰንክና ሰላም የሚነሱ የሕገ መንግስት አንቀፆች ፣ ሕጎች ፣ ደንቦች ፣ መመሪያወች ወ.ዘ.ተ. በህግ ሊሻሩና ማሻሻል ያለባቸው ሊሻሻሉ ይገባል፣

 

  • ሕዝብን በጋራአግባብተው ሊያቆሙ የሚያስችሉ ምልክቶች ለምሳሌ:
    • ባንዴራ ፣ ሃውልቶች ወ.ዘ.ተ. በህዝብ ተግባቦት ሊቆሙና ሊሰየሙ የግድ የሚል ሲሆን እንደ “አኖሌ ሃውልት” ያሉ ያለተፈጠረ ታሪክ እየዘከሩ በህዝብ መካከል ቂም እየጫሩ ለግጭት የሚገፉና ምክንያት የሚሆኑ መሰል ምልክቶች ሊወገዱ ይገባል፣

 

  • ዋናከተማወች ለምሳሌ እንደ አዲስ አበባና ድሬደዋ ያሉ /Metropolitan cities/ የመላ ሃገር ህዝቦች መናህሪያ ፣ የተለያዩ ሃገራት ኢምባሲዎች መቀመጫ፣ የውጭ ሃገር ድርጅቶች መናህሪያ ፣ የለጋሽ ሃገራት ቢሮዎች  በመሆናቸው ለአንድ የሕዝብ አካል /ብሄር/ ለመስጠት ወይም ጥቅም ማስጠበቂያ ለማድረግ መሞከር ለሕዝብ እልቂት / Jonocide/ና ግጭት ምክንያት ስለሚሆኑ እነዚህ ዋና ዋና ከተሞች የመላው ህብረተሰብ መኖሪያ መሆናቸውን በሕግ ማወጅ የግድ ይላል፣
ተጨማሪ ያንብቡ:  የምርጫ ህጉን፣ የምርጫ ዘመቻ መመሪያን የሚተላለፉ ንግግሮችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

 

6.3.) በዋና ከተሞች ደንብና ስርአት የሚያስጠብቁ ፓሊሶች ፣ ትራፊኮች ፣ ደንብ አስከባሪዎች በመንግስት የስራ ሃላፊነት የሚሰሩ የስራ ሃላፊዎች ወ.ዘ.ተ. የተለያዮ የሃገሪቱን ህዝቦች /ብሄሮች/ የሚወክሉና አማረኛ ተናጋሪ ቢሆኑ ይመረጣል፣

7) መንግስት ለችግሮች መባባስ ያሳየው ዳተኝነትና ግጭቶችን ለመፍታት ያለው አቅመ ደካማነት ሊፈተሽ የግድ ይላል፣

8) ተቃዋሚ ከሆኑ ቡድኖች ከሕወሃት ፣ ኦነግና ኦነግ ሸኔ ጋር ለመማከር መሞከሩ ባይከፋም የሚያቀርቡት ቅድመ ሁኔታዎች ለሃገር  ደህንነት ፣ ሉአላዊነት፣ ሰላምና አብሮነት ፀር ስለሆኑና መሪዎቹም በሰሩት ወንጀል በሕግ የሚፈልጉ በመሆኑ በማን ተወክለው እንደሚደራደሩ መግባባት ላይ መፍረስና በአንፃራዊነት የሰላምና የአንድነት መንፈስ ካላቸው ተከታዮቻቸው ጋር በገደምዳሜው የኢትዮጵያንና የሕዝቦቿ የጋራ ጥቅም አሳልፎ ባለ መስጠት ሊከወን የሚቻልበትን አካሄድ መቀየስ የተሻለ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል።

ማጠቃለያ

አገራዉ የምክክር መድረክ ከላይ የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታወችን አሟልቶ ከተከናወነ እውነተኛ እርቅ /Reconciliation/ ዕውን ይሆናልተብሎ ይታሰባል።

መንግስት ይህ የህዝብ መመካከሪያ መድረክ /National Dialogue/ ጉባኤ ሲቋቋም እጁ መግባት የለለትም ፣

የመማክርት ጉባሄ መማክርታን / Public Covneres/ ሲመረጡ በግለልተኛ ወገን መሆን ይገባዋል።

መንግስት ለድርድር የቀረቡትን ቡድኖችና ግለሰቦችን ለማባበልና የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም ሲል ለተቃራኒ ቡድኖች ስልጣን በማካፈል ችግሩን ለማብረድ ከሞከረ “ ከድጡ ወደ ማጡ” እንደሚሆንበት ከሌሎች ሃገሮች ልምድ አንፃር የታየ በመሆኑ ይህ ዓይነቱ አካሄድ መታሰብም ሆነ መሞከር የለበትም።

በመጨረሻም መድረኩ አሳታፊ /Inclusive/ , ግልፅ / Transparence/ የተሞላበት፣ ግልፅ አጀንዳ ያለው ፣ ስርዓት ያለው አካሄድ የተላበሰ / ከጣልቃ ገብነት የራቀ፣ የተመረጡት የመማክርት ጉባኤ አባላቱ ትፅህኖ በሌለበት መልኩ ያለ መንግስት ተፅህኖ ሊሰየሙ ይገባል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ከቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በጋምቤላ እና በምእራብ ወለጋ ለተከሰተው የንጹሐን ወገኖች ግድያ አስመልክቶ ያስተላለፈችው መልዕክት

 

ተዘራ አሰጉ- ከምድረ እንግሊዝ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.