“ከንቲባዋ የአዲስ አበባ ባህል ማዕከልን ዳግም እስካልከፈቱ ድረስ ከኪነጥበቡ ዓለም ተለያይቻለሁ” አርቲስት ደበበ እሸቱ

280619116 10159924816026411 2416697909385309776 nከከንቲባዋ ጋር ለመገናኘትና ለመነጋገር በተደጋጋሚ ብሞክርም ላገኛቸው አልቻልኩም። የአዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት የባህል ማዕከል ተዘግቶ ባለሙያዎቹ ተበትነው በማየቴ በሕይወቴ ትልቁ ያዘንኩበት ነገር ነው። ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ይህን ቴአትር ቤት ቢከፍቱት ምን ይጎዳሉ? ቴአትር አይሰሩበት ለስብሰባ እኮ በማንኛውም አዳራሽ መሰብሰብ ይቻላል።

ነገር ግን ይህ አልሆነም! ኅምሳ ዓመት ያገለገልኩበት ሙያዬ እንዲህ በደል ደርሶበት፣ የሙያ አጋሮቼ ተበትነው ሲንከራተቱ በማየቴ ከእንግዲህ ይህ ቤት ተመልሶ አገልግሎት መስጠት ካልጀመረ በስተቀር ከዚህ ሙያዬ ራሴን እንደሞትኩ ቆጥሬ ተለይቻለሁ። በየትኛውም የኪነ ጥበብ ዝግጅቶችና ፕሮግራሞች ላይ አልገኝም። እኔና ጥበብ ለዘለዓለም ተለያይተናል።

( አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ በመዘጋጃ ቤት ውስጥ የሚገኘው የአዲስ አበባ ቴአትር ማዕከል ተዘግቶ ባለሙያዎቹ መበተናቸውን በማስመልከት በታዲያስ አዲስ ያሰማው ቅሬታ )

በቃ!

ክብርት ሚንስትር፣ የጥበብ አጋሮቼ የአክብሮት ሰላምታዬን ተቀበሉኝ።

እንደምታውቁት እምነት አለኝ፣ ለጥበብ ከሃምሳ ዓመት በላይ እራሴን አስገዝቼ፣ እያከበርኳት አስከብራኝ እዚህ ደርሰናል። ለዚህም ክብርና ምስጋና ለፈጣሪ ይሁን።

ባለፈው ሥርዓት ላመንኩበት መቆሜ ወንጀል ሆኖብኝ ታስሬ ፍርድ ቤት የቆምኩት በፍርድ አደባባይ ሳይሆን አቃቂ በሚገኘው የሃገር ፍቅር ቅርንጫፍ ቴአትር ቤት ስለነበር፣ ቅሬታዬን ያሰማሁት በመታሰሬ ሳይሆን ያለቦታቸው መድረኩ ላይ ተሰይመው በሃሰት ክስ የሃሰት ፍርድ ለመስጠት በመዘጋጀታቸው ነበርና፣ እግዚአብሔርን የዚህን ፍርድ አንተ ስጥ ብዬው ነበርና በለውጡ ማግስት ፍርዱን ሲሰጥ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሥራ ሲጀምሩ በተዘጋጀው ምሽት ላይ ውጉዝ ከመአርዮስ በተባልኩበት ግቢ መድረክ ላይ ዕድሜ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አቢይ አህመድ ፕሮግራሙን እንድመራ ሲደረግ እግዚአብሔር ፍርድ ሰጠ አልኩ። ዛሬ ግን እግዚአብሔርን ፍርድ ስጥ አልለውም ዛሬ የሚለው ሌላ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አስገደ ገ/ስላሴ በባለስልጣናቱ ምክንያት ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰባቸው ገለጹ

ሁላችንም እንደምናውቀው የአዲስ አበባ መስተዳደድር ዕድሜ ለከንቲባ አዳነች አቤቤ አምሮና አሸብርቆ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ተውቦ ተመርቋል ሲሉ ሰምቼ ደስ አለኝ፣ በቴሌቪዥንም የባህል አዳራሹን ሳይ ከልብ ተደሰትኩ።

ቆየሁ፣ ጠበቅሁ፣ አቤቱታ ሲደረግም እኔም አማረርኩ። ያ የተዋበ የጥበብ አዳራሽ ለባለቤቶቹ የጥበብ ሰዎች አልተሰጠም፣ እነሱም የሚጠበቡበት ቦታ የላቸውምና ከዛሬ ከነገ በሚል ተስፋ እስካሁን አሉ።

ስለዚህም እነዚህ የጥበብ እጋሮቼ አዳራሹን በክብርት ከንቲባችን መልካም ፈቃድ እንዲጠበቡበትና የሙያ ቤታችን ማለት እስኪችሉ ድረስ ከዛሬ ጀምሮ እራሴን ከጥበቡ መንደር ማግለሌንና በዚህም ፕሮግራም ላይ እንደማልሳተፍ አክብረው የጠሩኝን ክብርት ዶር ሂሩትን ስለጥሪው እያመሰገንክና እናንተንም የጥበብ አጋሮቼን ይቅርታችሁን እንዳትነፍጉኝ በጥበብ አድባር ስም እጠይቃለሁ።

ጨርሻለሁ።

አመሰግናለሁ።

አርቲስት ደበበ እሸቱ ረታ

Leave a Reply

Your email address will not be published.