አሸባሪው የህወሓት ቡድን አሁንም በአማራ እና አፋር ክልሎች በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች አለመውጣቱን መንግስት አስታወቀ

280937199 582033263278295 6705546996604071696 nየመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማደናገር በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች እንደወጣ ቢያወራም አሁንም በአማራ ክልል በወረራ ከያዛቸው አዲአርቃይ፣ ጸለምት፣ አበርገሌ እና ሌሎች አካባቢዎች እንዲሁም ከአፋር ክልል ደግሞ በራህሌ፣ ኮኖቫ፣ አብአላ፣ መጋሌ ወረዳዎች አልወጣም ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ የሰብዓዊ እርዳታ እና ሰሜኑን የኢትዮጵያን ሁኔታ በተመለከተ በሰጡት መግለጫ÷ መንግስት በትግራይ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ የክልሉን ነዋሪዎች ለመታደግ ሲባል የግጭት ማቆም ውሳኔን ተከትሎ በየብስ እና በአየር ትራንስፖርት የሚጓጓዘው የሰብዓዊ እርዳት ተጠናክሮ መቀጠሉን አንስተዋል፡፡

የእርዳታ ፍሰቱንም የተሳለጠ ለማድረግ መንግስት ከእረጅ ድርጅቶች የሚነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችን መፍታቱንም ገልጸዋል፡፡

ባለፈው ሳምንትም የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 165 ያህል ተሸከርካሪዎች መቀሌ መግባታቸው በመግለጫው ተነስቷል፡፡

መንግስት አቅም በፈቀደ መጠን የእርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ማቅረብ የሚችሉትን እርዳታ እንዲያቀርቡ ያላሰለሰ ጥረት ቢያደርግም÷ በአንጻሩ የትግራይ ወራሪ ኃይል የእርዳታ ማጓጓዝ ስራው እንዳይሳለጥ እንቅፋት እየሆነ ነው ብለዋል ዶክተር ለገሰ በመግለጫቸው፡፡

የእርዳታ እህል ለማሳለጥ ሲባል ከትግራይ ወጥተናል በሚል የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማደናገር የሚረጩት ወሬም መሰረተ ቢስ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሽብርተኛው ህወሓት፥ መንግስት ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ እንዳይቀርብ እያስተጓጎለ ነው፤ “በከበባ ውስጥ በማስገባት ትግራይን በርሃብ እየቀጣ ነው” በሚል የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት መንግስትን ሲከሱ ይደመጣል ብለዋል ዶክተር ለገሰ፡፡

ይሁን እንጂ፥ የአማራ እና የአፋር ክልል ወረዳዎችን በጉልበት ወርሮ እና ተቆጣጥሮ የአካባቢውን ነዋሪዎች በማፈናቀል ለስቃይና እንግልት እየዳረጉ ተከበብኩ፣ ተራብኩ ወዘተ የሚለው የተለመደ ድራማ እና መዝሙር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ዶክተር ለገሰ ቱሉ አስገንዝበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ለኢትዮጵያ የ130 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ሰጠ

ይህ ድርጊታቸው ሕዝብን በማዋረድ ሰግብግብ ፍላጎታቸውን በሕዝብ ሞት እና ስቃይ ለማሟላት የሚያደርጉት እኩይ ሴራ ነው ብለዋል፡፡

“ከበባውን ለማስከፈት ሲባል የግድ ወደ ጦርነት ለመግባት እገደዳለሁ” በሚል የሚገለጸው የጦርነት ጉሰማ እና ፉከራም ዳግም የትግራይን ወጣቶች ለማስጨረስ እንደሆነም በመግለጫው ተነስቷል፡፡

የአሸባሪው ቡድን ዳግም በትግራይ ወጣቶች ደም እኩይ ፍላጎቱን ለማሳካት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የትግራይ ሕዝብ እንዲታገል መንግስት ጠይቋል፡፡ ኤፍ ቢሲ

1 Comment

  1. ዳግም የትግራይን ወጣቶች ለማስጨረስ ?
    How about the other youth that will be dying, don’t they count?

    This is empty propagandistic talk by leaders that are preparing the way for additional destruction of the Amhara, Afar and Tigray people. Why are you disarming the Amhara farmers? Why is the OPDO swarming over the Amhara region dismantling the Fanno and other local defense structures that saved the Amhara from total annihilation last year? Why were the Afar left without any support to face the wrath of the government-armed TPLF?
    And who was it that left the TPLF in control of the areas that your are lamenting as occupied.
    Until when will you continue to fool yourself thinking that your are fooling others?

Leave a Reply

Your email address will not be published.