የጭራቅ አሕመድ ጭራቃዊ ስሌት፤ እውን ኦሮሞ ብዙሃን ነው? – መስፍን አረጋ

Untitled design 33የዚህ ጦማር ዓላማ የአማራ ሕዝብ ቁጥር የኦሮሞን ይቅርና የኦሮሞንና የትግሬን ድምር ቁጥር በሚሊዮኖች እንደሚበልጥ በግርድፍ ስሌት (back of the envelope calculation) ማሳየት ነው፡፡  በኦሮምኛ ስለተሰየመ ብቻ ኦሮሞ ሳይሆን ኦሮሞ ነው የሚባለውን ሰፊ አልኦሮሞ (non-Oromo) ሕዝብ ከስሌት ውስጥ ካስገባነው ደግሞ አውነተኛው ኦሮሞ ቁጥሩ እጅግ አነስተኛ የሆነ ህዳጣን (minority) መሆኑን በማሳየት የጭራቅ አሕመድን ዓይን ያወጣ ውሸት ማጋለጥ ነው፡፡  እግረ መንገዱን ደግሞ ጭራቅ አሕመድ ሆን ብሎ በሚፈጥራቸው የጦርነት፣ የመፈናቀልና የርሐብ ቀውሶች የአማራን ሕዘብ እንደ ቅጠል በማርገፍ ኦሮሞን ብዙሃን ለማድረግ ተግቶ እየሠራ መሆኑንና፣ ጭራቁ በፍጥነት ጨርቅ ካልተደረገ ጭራቃዊ ዓላማውን ማሳካቱ አይቀሬ መሆኑን ለማስገንዘብ ነው፡፡

 
መንደርደርያ
የሉባው ሠራዊት የገዳው ኦሮሞ
ሐበሻን ሲያገኘው በግራኝ ተዳክሞ
ጨለማ ተላብሶ እያረደ አጋድሞ፣
ባበሻ ምድር ላይ በያቅጣጫው ተሞ
የተንሰራፋ ነው እንደ አረማሞ፡፡
በጦቢያ ምድር ላይ ከጣና እስከ ጫሞ
በኦሮምኛ ቃል ያለ ተሰይሞ
ከመስፋፋት በፊት ሁሉም አስቀድሞ
አይደለም ኦሮሞ ወይም የኦሮሞ፡፡ 
 

በስሙ ቢባልም ኤጀርሳ፣ ኤለሞ
በደሙ ያልሆነ ሐበሻና ጋሞ
እንዲሁም ወላይታ፣ ሐድያ ሲዳሞ
እስኪ ተናገሩ የቱ ነው ኦሮሞ?
 
የጭራቅ አሕመድ ጭራቃዊ ስሌት

ዓይኑን በጨው አጥቦ መዋሸት የማይታክተው፣ አፉና ምግባሩ ሐራምባና ቆቦ የሆነው፣ የኦነጉ ኦቦ ጭራቅ አሕመድ፣ ብዙሃን ያልሆነውን ኦሮሞ ብዙሃን ለማስባል በተለያዩ ጊዜወች የተለያዩ ቅጥፈቶችን ቀጥፏል፡፡  ከነዚህ ቅጥፈቶች ውስጥ ደግሞ አሮሞ በቁጥር ካፍሪቃ አንደኛ ነው ሲል በድምጽና በምስል የተቀረጸውና፣ ከቅርብ ቀናት በፊት ደግሞ ሸንጎ ላይ ቀርቦ ምንም መረጃ ሳያቀርብ ኦሮሞ 35% ነው በማለት በይፋ የተናገረው ይገኙበታል፡፡

ጭራቅ አሕመድ ኦሮሞ 35% ነው ሲል በትክክል ለማለት የፈለገው እኛ ኦሮሞወች በከፍተኛ ደረጃ ብዙሃን ስንሆን፣ የቀራችሁት ሁላችሁም ንዑሳን ናችሁ፣ ስለዚህም ወደዳችሁም ጠላችሁም በኛ በብዙሃን ሥር ትተዳደራላችሁ ነው፡፡  ጭራቅ አሕመድ ‹ኦሮሞ አላግባብ ስልጣን ይዞ ከሆነ ከኔ ጀምሮ እንጠየቅ›› ሲል፣ በትክክል ለማለት የፈለገው በጉምሩክ፣ በፋይናንስ፣ በአስተዳደር፣ በደህንነትና በመከላከያ ሁሉንም ቁልፍ ቦታወች እኞ ኦሮሞወች መያዛችን አይግረማችሁ ቢያንስብን እንጅ አይበዛብንም ነው፡፡

ጭራቅ አሕመድ ይህን ሁሉ ቅጥፈት የሚቀጥፈው የጦቢያ ብዙሃን ኦሮሞ ሳይሆን አማራ እንደሆነ እያወቀና በተለያዩ ዘዴወች የአማራን ቁጥር ቀንሶ ኦሮሞን ቁጥር በመጨመር ኦሮሞን ብዙሃን ለማድረግ የቻለውን ሁሉ እያደረገ ባለበት ጊዜ ነው፡፡  ጭራቅ አሕመድ ስልጣን ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ የአልኦሮሞ ጦቢያውያንን (የአማራን፣ የትግሬን፣ የሱማሌን፣ የጌድኦን፣ የወላይታን ወዘተ) ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንሱ ቀውሶችን (መፈናቀሎችን፣ ጭፍጨፋወችን፣ ርስበርስ ጦርነቶችን፣ ርሐብን ወዘተ.) ሆን ብሎ ፈጥሯል፡፡  በተለይም ደግሞ የሐበሻን (የአማራና የትግሬን) ቁጥር በተመለከተ አንዴ ካማራ ጋር ሌላ ጊዜ ደግሞ ከትግሬ ጋር የወገነ እየመሰለ ርስበርሳቸው ተጨፋጭፈው እንዲጨራረሱና በሽናሻ ደረጃ ንዑሳኖች እንዲሆኑ የቻለውን ሁሉ አድርጓል እያደረገም ይገኛል፡፡

“የኦሮሞን” ቁጥር ባፋጣኝ ለመጨመር ደግሞ መታወቂያ የሌላቸውን አልኦሮሞወች (በተለይም ደግሞ ወጣት ችግረኞችን) በኦሮሞ ስም መታወቂያ በመስጠት፣ መታወቂያቸውን ለመሳደስ የሚሄዱትን ደግሞ ስማችሁን ወደ ኦሮሞ ካልለወጣችሁ አላድስላችሁም በማለት “ኦሮሞወችን” በሁሉም ዋና ዋና ከተሞች (በተለይም ደግሞ ባዲሳባ) ላይ ብዙሃን ለማድረግ በከፍተኛ ትጋት እየሰራ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ክብር እንክርዳድ ተዘርቶበት ስንዴ ሆኖ ለበቀለ ትውልድ!!! – ተስፋየ ኤልያስ

በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ላይ የሚፈናቀሉት፣ የሚራቡት፣ የሚጨፈጨፉት እንዲሁም በርስበርስ ጦርነት የሚያልቁት አልኦሮሞወች በተለይም ደግሞ ሐበሾች (አማሮችና ትግሬወች) ብቻ ናቸው፡፡  ጭራቅ አሕመድ ቀውሶችን ሥራየ ብሎ የሚያቅናበራቸው ኦሮሞወች ናቸው የሚባሉት ሰወች የቀውሶቹ ሰለባ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረገ በጭራቃዊ ስሌት ነው፡፡   በዚህም ምክኒያት በጭራቅ አሕመድ የስልጣን ዘመን የሐበሻ (በተለይም ደግሞ የአማራ) ቁጥር በሚሊዮኖች ሲቀንስ፣  ኦሮሞ ነው የሚባለው ሕዝብ ቁጥር ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ እንደጨመረ ግልጽ ነው፡፡

ይህ ኦነጋዊ ጭራቅ ባፋጣኝ ካልተወገደ ደግሞ፣ በተለያዩ ጊዜወች ሥራየ ብሎ በሚፈጥራቸው የተለያዩ ቀውሶች አማካኝነት የአልኦሮሞወች ቁጥር እየቀነሰ፣ የኦሮሞ ተብየወች ቁጥር እየጨመረ ይሄድና፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እንደ ጭራቁ ምኞት ኦሮሞ ተብየው ሕዝብ ብዙሃን ይሆናል፡፡

አሁን ላይ ግን ጭራቅ አሕመድ ኦሮሞ ብዙሃን ነው ሲል፣ የተለመደውን ቅጥፈቱን እየቀጠፈ ነው፡፡  የዚህ ጦማር ዓላማ ደግሞ የኢትዮጵያ ብዙሃን አማራ እንጅ ኦሮሞ እንዳልሆነና፣ የአማራ ቁጥር የኦሮሞን ቁጥር በሚሊዮኖች እንደሚበልጥ ማሳየት ነው፡፡

እውን አሮሞ ብዙሃን ነው?

አማራ ማለት በመላ ጦቢያ ላይ ተሰራጭቶ የሚኖር ራሱን አማራ ነኝ የሚል ጦቢያዊ ማለት ነው፡፡  በዚህ ብያኔ (definition) መሠረት አማራ በጦቢያ ውስጥ በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ብቻ ሳይሆን ሁለተኛ ነው የሚባለውን ኦሮሞን በሚሊዮኖች እንደሚበልጥ ከዚህ በታች እንመለከታለን፡፡  አማራነቱን በጉዲፈቻነትና በሞጋሳነት ተቀምቶ አማራ መሆኑን የማያውቀውን ባስር ሚሊዮኖች የሚቆጠረውን ሕዝብ ሳይጨምር እንኳን የአማራ ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ የኢትዮጵያ ብዙሃን (majority) ሲሆን፣ ኦሮሞ ደግሞ ከንዑሳኖች (minorities) ውስጥ አንዱ ነው፡፡  መሆኑን ደግሞ በዝርዝር እንመልከት፡፡

  • ኦሮምያ በሚባለው ልቦለዳዊ ክልል ውስጥ የትላልቆቹ ከተሞች ከተሜወች አብዛኞቹ አልኦሮሞወች(non-oromo) በተለይም ደግሞ አማሮች ናቸው፡፡
  • ባዲሳባ ከከተመው ኦሮሞ ውስጥ አብዛኛው በኦነጋዊ ሹሞች አድሏዊ ትብብር በወያኔና በኦነግ ዘመን የከተመ የቅርብ ሰፋሪ ነው፡፡  እንዲህም ሆኖ ባዲሳባ የሚኖረው ኦሮሞ ጠቅላላ ቁጥር ባንጻራዊ ደረጃ ሲታይ ኢምንት ነው፡፡  በሌላ አባባል አዲሳባ ውስጥ ኦሮሞ አናሳወይም ህዳጣን ነው፡፡    በተቃራኒ ደግሞ ካዲሳባ ሕዝብ ውስጥ ቢያንስ ቢያንስ 60% አማራ ነው፡፡  ናዝሬት፣ ደብረዘይት፣ ሐረር፣ ድሬድዋ፣ ጅማ፣ አጋሮ በመሳሰሉት ከተሞችም እንደዚሁ፡፡
  • ያማራ ቁጥር እንጦሮንጦስ ወርዶ የኦሮሞ ቁጥር ሰማይ የነካው በወያኔ ዘመን ነው፡፡  ወያኔ ደግሞ የሐብትና የንብረት ብቻ ሳይሆን፣ የታሪክ እና የቁጥር ሌባ መሆኑን መናገር አያስፈልግም፡፡  ማጋነን ሲሻ የትግራይ ሕዝብ ይሄን ያህል ነው፣ ሐውዜን ላይ ይሄን ያህል ተጨፈጨፈ፣ አይደር ላይ ይሄን ያህል አለቀ፣ ከጎንደር ይሄን ያህል ትግሬ ተፈናቀለ እያለ የሚያጋንን፣ ማሳነስ ሲሻ ደግሞ ከሰባት ሚሊዮን በላይ የሚገመተውን አዲሳቤ በግማሽ የሚጎመድ፣ ሲዋሽ ዓይኑን የማያሽ፣ በሐሰት ትርክት ተፈጥሮ በሐሰት ለሐሰት የሚኖር ሐሳዊ ድርጅት ነው፡፡
  • ኦሮምያ የተሰኘው ካማራ፣ ከጉራጌ፣ ከወላይታ፣ ከጉጅ፣ ከሱማሌ ወዘተ. በተነጠቁ መሬቶች አለቅጥ የሰፋው ኢፍትሐዊ ክልል በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ሊሆን ይችላል፣ ለዚያውም ከሆነ፡፡  ይህ ማለት ግን ኦሮሞ በቁጥር አንደኛ ነው ማለት አይደለም፡፡   የኦነጋውያን ጥረት ግን እነዚህን እየቅል እውነታወች ማምታታ ነው፡፡  ጥረታቸው ደግሞ በሰፊው ተሳክቶላቸው አብዛኛውን ጦቢያዊ ለማምታታት ችለዋል፡፡
  • ስለዚህም የጦቢያውያን (በተለይም ደግሞ ያማሮች) የመጀመርያ ሥራ መሆን ያለበት የኦነጋውያንን የቁጥር ቅጥፈት በመረጃ ሰይፍ መቅጠፍ ነው፡፡ ኦሮምያ በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ነው ማለት፣ ኦሮሞ በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ነው ማለት አይደለም፡፡ አለመሆኑን ደግሞ እንመልከት፡፡ 
  • በጎጠኞቹ በወያኔና በኦነግ እየተመራ ፀራማራ አጀንዳ የሚያራምደውን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ድርጅት (Central Statistical Agency) በማጣቀስ (June 4, 2018) ዊኪፒዲያ (wikipidea) እንዳስቀመጠው፣ በ 2009 ዓ.ም ላይ የአማራ ክልል ሕዝብ በግምት 22 ሚሊዮን ሲሆን፣ የኦሮሞ ክልል ሕዝብ ደግሞ በግምት 35 ሚሊዮን ነው፡፡ይህ መረጃ ደግሞ ያማራ ክልልን ሕዝብ እጅግ አሳንሶ የኦሮሞ ክልልን ሕዝብ እጅግ ያበዛ የውሸት መረጃ እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡  ላሁኑ ግን ውሸቱን እንዳለ እንቀበለውና ስሌቶችን እናስላ፡፡
  • በስታቲስቲክ ድርጅት መረጃ መሠረት፣ ካማራ ክልል ሕዝብ ውስጥ 91% አማራ ነው፡፡  ስለዚህም ባማራ ክልል ውስጥ ቢያንስ ቢያንስ 20 (= 22 × 0.91%)ሚሊዮን አማራ ይናራል ማለት ነው፡፡
  • አዲሳባን ሳይጨምር ካማራ ክልል ውጭ ቢያንስ ቢያንስ 15 ሚሊዮን አማራ ይኖራል ተብሎ ይገመታል፡፡  ላማራ ጥቅም ይቆማል ተብሎ የማይታማው የግንቦት ሰባቱ ነአምን ዘለቀደግሞ ቁጥሩን በ 12 ሚሊዮን ይገምተዋል፡፡  የማይታመነውን ነዐምንን ላሁኑ እንመነውና ካማራ ክልል ውጭ (አዲሳባን ሳይጨምር) የሚኖረው አማራ 12 ሚሊዮን ነው እንበል፡፡  ከነዚህ 12 ሚሊዮን አማሮች ውስጥ ደግሞ ጭራቅ አሕመድ በተለያዩ ጭራቃዊ ቀውሶች አማካኝነት 2 ሚሊዮኖቹን አጥፍቷቸዋል እንበል፡፡  ስለዚህም አዲሳባን ሳይጨምር በሁሉም ክልሎችና በድሬዳዋ ልዩ ዞን ውስጥ የሚኖረው አማራ 30 (= 20 + 10) ሚሊዮን ገደማ ነው ማለት ነው፡፡
  • በ 2009 ዓ.ም ላይ የአዲስ አበባ ሕዝብ በግምት 7.5 ሚሊዮን ነው፡፡  ስለዚህ ያዴሳቤ አማራ ቁጥር ቢያንስ ቢያንስ 4.5 (= 7.5 × 60%)ሚሊዮን ነው ማለት ነው፡፡  ስለዚህም በጦቢያ የሚኖረው አማራ ቁጥር 36.5 (= 32 + 4.5) ሚሊዮን ገደማ ነው ማለት ነው፡፡
  • ካማራ ክልል ውጭ (አዲሳባን ሳይጨምር) ከሚኖረው 10 ሚሊዮን አማራ ውስጥ ቢያንስ ቢያንስ ግማሹ (ማለትም 5 ሚሊዮኑ) ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ይኖራል እንበል፡፡  ይህ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚኖረውን አልአማራ (non-Amhara) (ማለትም አሮሞ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ ወዘተ.) ጠቅላላ ቁጠር ወደ 30 (= 35 – 5) ሚሊዮን ያወርደዋል፡፡
  • በተለያዩ ምክኒያቶች ኦሮሞ ከኦሮምያ ክልል ውጭ እምብዛም አይኖርም፡፡ ስለዚህም በኦሮምያ ክልል ውስጥ የሚኖሩ አልአማራ አልኦሮሞወች (non-Amhara non-Oromos) (ማለትም አማራም ኦሮሞም ያልሆኑ ሰወች በተለይም ደግሞ ጉራጌወች፣ ትግሬወች፣ ሱማሌወች፣ ወላይታወች፣ ጌድኦወች ወዘተ.) ቁጥር፣ ከኦሮምያ ክልል ውጭ ከሚኖሩ ኦሮሞወች ቁጥር በጣም እንደሚበልጥ ግልጽ ነው፡፡  ይሁንና የመጀመርያው ቁጥር ከሁለተኛው ቁጥር ጋር እኩል ነው እንበልና፣ ከኦሮምያ ውጭ የሚኖረውን የኦሮሞ ቁጥር እንዲያካክስልን እናድርግ፡፡  በሌላ አባባል በኦሮምያ ውስጥ የሚገኙ ኦሮሞም አማራም ያልሆኑ ጦቢያውያን ቁጥር ከኦሮሚያ ውጭ ከሚኖሩ ኦሮሞወች ቁጥር ጋር እኩል ነው እንበል፡፡   ስለዚህም በድፍን ጦቢያ ውስጥ የሚኖረው የኦሮሞ ቁጥር እጅግ ሲበዛ በዛ ቢባል 30 ሚሊዮን ገደማ ነው ማለት ነው፡፡
  • በሌላ በኩል ደግሞ በድፍን ጦቢያ ውስጥ የሚኖረው አማራ ቁጥር 37 ሚሊዮን ገደማ እንደሆነ በቁጥር (9) ላይ ተመልክተናል፡፡  ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ኦሮሞ ነው የሚባለውን ሕዝብ ቢያንስ ቢያንስ በ 7 ሚሊዮን ይበልጠዋል ማለት ነው፡፡
  • አማራ ኦሮሞን ቢያንስ ቢያነስ በ 7 ሚሊዮን ይበልጣል ያልነው፣  የአማራ ክልል ሕዝብ በግምት 22 ሚሊዮን ሲሆን፣ የኦሮሞ ክልል ሕዝብ ደግሞ በግምት 35 ሚሊዮን ነው የሚለውን በተራ ቁጥር (6) ላይ የተገለጸውን የወያኔ መረጃ መሠረት በማድረግ ነው፡፡  ስለዚህም የግርድፍ ስሌታችንን (approximate calculation) በፀራማራው በወያኔ መረጃ ሳይሆን፣ በትክክለኛ መረጃ መሠረት ብናደርግ ኖሮ ያማራ ቁጥር 40 ሚሊዮኖች ውስጥ ሲሆን፣ የኦሮሞ ቁጥር ደግሞ ከ 25 ሚሊዮን ባልዘለለ ነበር፡፡  ስለዚህም ያማራ ሕዝብ የኦሮሞን ሕዝብ የሚበልጠው በአሥር ሚሊዮኖች ነው ማለት ነው፡፡
  • ያማራ ቁጥር 37 ሚሊዮን ነው፣ የኦሮሞ ቁጥር 30 ሚሊዮን ነው፣ የትግሬ ቁጥር ደግሞ 6 ሚሊዮን ገደማ ነው (የወልቃይትንና የራያን አማሮች ቁጥር ሳንቀንስ)፡፡  ስለዚህም ኦሮሞ ብቻውን ይቅርና ኦሮሞና ትግሬ ቢደመሩ እንኳን (30 + 6 = 35) አማራን አያህሉም ማለት ነው፡፡
  • በመሠረቱ አማራ ኦሮሞን በሚሊዮኖች እንደሚበልጥ ለመረዳት ሕዝብ ቆጠራም ሆነ ሌላ ዓይነት ስሌት አያስፈልግም፡፡  ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎና ሸዋ አርብቶ አደር የማይኖርባቸው፣ አርሶ አደሩ የበሬ ግንባር  በሚያህሉ ርስቶች እጅግ ሲበዛ የተጨናነቀባቸው፣ ተራራው፣ ሸለቆው ሳይቀር ሁሉም የሚታረስባቸው ሰፋፊ ክፍለ ሀገሮች ናቸው፡፡  በሌላ በኩል ደግሞ ባሌ፣ ወለጋ፣ ከፋና፣ ኤሊባቡር ባብዛኛው ጠፍ መሬቶች ናቸው፡፡  በደርግ ጊዜ ሰፋፊ የምንግሥት እርሻወች የተተከሉባቸው፣ በወያኔ ጊዜ ደግሞ ለአበባ እርሻወች የተቸበቸቡት ከነዚህ ጠፍ መሬቶች እየተቆረሱ ነው፡፡  እነዚህ ክፍለ ሀገሮች በቂ ሰው ስሌላቸው አርሶ አደሮቻቸው ቡናቸውን የሚያስለቅሙት፣ ምርቶታቸውን የሚያስሰበስቡት፣ የራሳቸውን ኩርማን መሬት አርሰው ከጨረሱ በኋላ ከወሎና ከጎጃም በሚመጡ በንቀት አጠራር ጎጀ እየተባሉ በሚጠሩ (ኩሊ ለማለት ነው) ጊዜያዊ ሠራተኞች ነው፡፡  ኦሮሞወች በተወሰነ ደረጃ ተጠጋግተው የሚኖሩባቸው ምሥራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ ሸዋና አሩሲ ሲሆኑ፣ እነሱም ቢሆኑ የሕዝብ ጭፍቀታቸው (population density) (ማለትም የሕዝብ ትፍፍጋቸው) ካማራ ክፍለ ሀገሮች የሕዝብ ጭፍቀት አንጻር ኢምንት ነው፡፡
  • ስለዚህም ቁጥሩ ሚሊዮን የማይደርሰው ትክክለኛው የቦረና አሮሞ ይቅርና አሮሞ ነው የሚባለው የሞጋሳና የጉዲፈቻ ውጤት የሆነው ሰፊ ሕዝብ እንኳን ከአማራ ሕዝብ ቁጥር በ 10 ሚሊዮን ገደማ ያነሰ ነው፡፡  የጭራቅ አህመድ የኦሮሞ ብዙሃንነት እስከዚህ ድረስ ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢህአዴግ ጣና በለስን ለምን አፈራረሰው? “በሩ ይከፈት፣ በአባይ ጉዳይ አገራዊ አቋም እንያዝ”

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

2 Comments

  1. When you imagine what Abiy Ahmed is doing to the Oromo people by unwarrantedly attacking others, you wonder if he is a friend of the Oromo people or their enemy I am sure the Oromo people asked nobody to kill or lie on their behalf. Did Tigrayans really benefit from the evil policies and politics of Meles Zenawi?

    Asa gorguari zendo yaweTal, yesew felaghi yerasun yaTAl.

  2. ፕሮፍ በዚህ ስሌትህ ለኦሮሞ ያደላህ መሰለኝ ከዚህ በፊት በእንተ ሊቀ ሊቃውንት ዩተመዘገበ ድርሳን መረጃ አጣቅሶ ባስነበበን ጽሁፍ የኦሮሞ ነገድ ቢበዛ 5% እንደሆነ ነው ነጋሶ ጊዳዳን ብርሀኑ ጁላን ጨምሮ ኦሮሞ አይደሉም። እየተበራከተ በመጣው አስገድዶ ሀይማኖትና ነገድን ማስቀየር አብዝቶ ብዛታቸውን በማስነገር እዚህ ተደርሷል አንድ የDNA ማሽን ገዝቶ ያዙኝ ልቀቁኝ ኦሮሞ ሳይሆን ኦሮሞ ካልሆንኩ የሚለውን ከአብይ አህመድ ጀምሮ ብታስመረምረው ልኩን አውቆ ይሰበሰብ ነበር።

Leave a Reply

Your email address will not be published.