አማራ የሆንክ ስማ??

288358186 5211569042256804 2092752397205846827 nነገሩ እንዲህ ነው ጭራሽ በ1983ቱ ያለ ህዝበ ውሳኔ ከወሎ ምድር በሴራ ተሸርምጦ የተወሰደውን መሬት ስንጠይቅ ይባስ ብሎ አሁን ያለው ፌክ ህገ መንግስት ተብየ ከፈቀደው የራያ መሬት አልፈው እንዲፈነጭሉበት ተፈቀደ። ታዲያ በዚህ የቁጭት ሲቃ መካከል ነበር ወደ ራያ ቆቦ ወረዳ ቀበሌ ተሻግረው አንዲት የልጇን ሆድ ለመሙላት ብቻዋን በጫካው መካከል ስንጣሪ እንጨቶችን እየለቃቀመች በብሶት የምታንጎራጉርን ምስኪን እናት ወራሪው የትግራይ ቡድን የጥይት መፈተኛ አድ ርጎ እናቱን ከሚናፍቀው ልጇ ፣ልጇን የናፈቀች እናትን የነጠሏት። መቸም ስጋ ክፉ ነው ና የግድያ በደል የተፈፀመባት ምስኪን እናት የቅርብ ቤተሰቦች ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ስጋዋን የተፈቀደለትን አፈር አቅምሰው ርማቸውን ለማውጣት ወደ ሟች አስከሬን ሲጠጉ ልቡ የተደፈነው ጨካኝ ቡድን በነርሱ ላይም የጥይት ሮምታን ሲያዘንብ ራሳቸውን ለመከላከል መሬት ላይ ተኝተው ጠመንጃቸውን ማጫወት ጀመሩ። ራያ ጀግናም አይደል!!በዚህን ግዜ በዋርካው ምሬ ወዳጆ ና ሻለቃ ከድር የሚመሩት የአናብስት ግልገሎች ተቆጡ ጉዳዩን በቅርበት የተመለከቱት ቃኞች ተወርውረው የምስኪኗን አማራ እናት ሬሣ ለማውጣት ገቡ ፣ ይህን ግዜ ወራሪው ቡድን ከሇላ ሀይል ጨመረ ፣ የጀግናው ይርጋ አበበ ልጆች (ሀው ጃኖ ብርጌድ )ዓይናቸው ደም ለበሰ፣ ትንታጎቹ የራያ ቆቦ ዞብል አምባ ብርጌድ ማጉረጥረጥ ጀመሩ፣ ነበልባሉ የአሳምነው ፅጌ ብርጌድ በጀግኖች ዓይኖቹ ጥቅሻን ጀመረ፣ ሶስቱም በአንድነት ተማክረው ወሰኑ። ከሇላ በአያሌ የሎጅስቲክ ድጋፍ የተደራጀ ፣ በከባድ መሳሪያ ሽፋን የተዘጋጀውን ወራሪ ሀይል እጃቸው ላይ ባለው ሚጥጥየ መሳሪያ ና ትልቅ ልብ ለመግረፍ ቦታ ቦታቸውን ያዙ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  "የእነሱ ትልቁ ሀይል ዘር ሲሆን የእኛ ትልቁ ሞተራችን ኢትጵያዊነት ነው.." ሌተናል ጄኔራል አበባው ታደሰ

289532784 3286496131634715 2760448804624288001 n

ፍልሚያው ተጀመረ አንበሳው የምሥራቅ አማራ ፋኖ በረቀቀ ቴክኒኩ የምስኪኗ እናቱን ደም ለመመለስ አሃዱ ብሎ ጀመረ ። አረንገቦ የወራሪውን ሀይል ድርብ ድርብርብ ሬሣ ክምሮች ማስተናገድ ጀመረች ፣ጀሮታ ተመትተው የሚሸሹ ቁስለኞችን አስተናገደች፣ ብሶተኞቹ አናብስቶች እየተናበቡ ቀጠሉ የተንጣለለው ሜዳ ከጃሮታ እስከ ባቦኮርማ ፣ ከዋልካ እስከ ቁንቁራ ቀበሌ በሳቅ ተፍነሸነሸ ፣ ቀጠለ ፈሪወች እየሸሹ ጀግኖች እየለመጠጡ ፀሀዯም ጉዞዋን እያስተናገደች ከቀኑ 11:00 የዋጃ ከተማን ዙሪያ ልጆቿ ተቆጣጠሩ፣ በትንሽ መስዋእትነት እጅግ አያሌ ድልን ተቀዳጁ። በዚህን ግዜ ከሇላ ያለ ሀይላቸውን በማጠናከር አናብስቶቹን በከበባ ውስጥ ለማስገባት የፈርጣጮቹ ወገኖች ተደራጅተው ጉዞ ጀመሩ። ጀግናው አለቃ ቆፍጠን ብሎ እንዲህ ሲል ለልጆቹ ትዛዝ አስተላለፈ<< በቃ ተመለሱ ሬሣቸውንም ፣ቁስለኞቻቸውንም ያንሱ ለግዜው እኛ እንደ እነሱ የተጠናከረ የሇላ ደጀን ና ሎጅስቲክ የለንም>> በአንዲት አማራ እናት ሞት የተበሳጩት የምሥራቅ አማራ ፋኖ አናብስቶች ጣምራ ጣምራ መቶውን ረሽርሸውት በተስፋ ና በናፍቆት ሲጠባበቃቸው የነበረው የራያ አለማጣ ህዝ በአካል ተገናኝተው ባይዘይሩትም እንኳን በናፈቁ አይኖቹ የጠላቶቹን ኪሳራ በዓይኑ በብረቱ ከትንንሽ የጋሪ ተሽከርካሬወች እስከ ከፍተኛ ከባባድ መኪናወች ጭኖ ሲወረወር አስቃኝተው ወደ ሇላ የአለቃቸውን ትዛዝ አክብረው ተመለሱ።

289659386 10159901026834393 7717595044600991369 n 1

ትላንት የምሥራቅ አማራ ፋኖ አናብስቶች የጦር ሜዳ ችሎታ አቅማቸውን በተግባር አስመስክረው በጀኔራሎች ሳይቀር ተጨብጭቦላቸዋል። ነገ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ራያን ነፃ አውጥተው እንዲያስረክቡን ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፣ እነሱ የሚሰጡን ስለ እኛ ሰላም ውድ ህይወታቸውን ደቅነው የድል ብስራትን ነው ። እኛስ???

289377367 10158593738471237 3238691939383568555 n

አማራ የሆነ ሁሉ አናብስቶቹን የምሥራቅ አማራ ፋኖ በራያ ግንባር በሎጅስቲክ ድጋፍ በማገዝ ወገኖቹን ነፃ ያውጣ????

ተጨማሪ ያንብቡ:  አንድነት ፓርቲ የደቡብ አፍሪካ ኢምባሲ ተወካዩች በነገው መርሐ ግብር እንደሚገኙለት አስታወቀ

አማረ ደሳለኝ ተገኘ

ከቦታው

Leave a Reply

Your email address will not be published.