ስማኝ የሸገር ልጅ (ከአሁንገና ዓለማየሁ) 

ጠኔውም ቢገልህ ስጋም አንቆህ ብትሞት
መዝግቦት ተጓዘ ታሪክ ያንተን ሐሞት

ስትሳለቅ ነበር ትናንት በእስክንድር
በአቋራጭ ቀዳድሞህ ቆሞልሃል ብድር።

ስማኝ የሸገር ልጅ ኳስ ዳንኪራ ብርቁ
ጊምቢ ቶሌ አይደለም እልቂቱ ፍጅቱ ያንተኑ ነገ ነው ያሳዩህ በሩቁ
ንብረትህን ዘርፈው ቤትህን ሲያነዱ
እትና እናትህን ልጅና ሚስትህን እንዴት እንደሚያርዱ

ምን እንደሚመስል ያንተኑ ነገ ነው ያሳዩህ በሽንቁር
ወለጋ ሩቅ መስሎህ የዋሁ ሸገሬ እንዳትደነቁር

ከነግብራበሩ ነገ ብልጽግና
ባንተ ደም ይዋኛል ግንፍሌ፣ ቡልቡላ፣ ቀጨኔ፣ ቀበና

ጅቡ ርቆ ሄዷል ዛሬ ካዲሳባ
ማን (man) ነው የሚበላው ነገ ያንተን ሬሳ ያካልህን ገራባ?

ያ እንጂ ጥያቄው ያልመለሱት ገና
በወለጋ ተውኔት የሸገርን እጣ ሲያሳይ ብልጽግና

ሁሉን ጨርሶታል ነግ ያንተ ነው ተራው
ገዳይህ ለታሪክ ተነግሮት አደራው
ቃል እየጠበቀ ቆሟል በየሥፍራው
ስምክም ተጽፎበት ተቀምጧል ገጀራው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወይፈን ሆይ ነቃ በል!

Leave a Reply

Your email address will not be published.