ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ያወጣው ወቅታዊ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል

addis ababa zehabesha

1—የአዲስ አበባ ከንቲባ ያለመከሰስ መብት ተነስቶ ለህግ እንዲቀርቡ ስለማሳሰብ

2. የኦሮሚያ ሰንደቅ ዓላማ እና መዝሙር በአ/አ ት/ቤቶች እንዳይይሰቀል እና እንዳይዘመር ስለማሳሰብ!!

የኢትዮጵያ ሕዝብ በገዥው ፓርቲ እየተፈጸሙበት ያሉት የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውሶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፉ በመሄድ ላይ ይገኛሉ። አዲስ አበባ ከተማም የኦሕዴድ መራሹ ብልጽግና የጥፋት ክንዱን ካሳረፈባት የአገራችን ክፍሎች ዋናዋ ናት፡፡

የከንቲባ አዳነች አበቤ የሥልጣን ዘመን ከተማዋን ከገጠሟት አስከፊና ብልሹ አስተዳደሮች መካከል ግንባር ቀደሙ ከመሆኑም ባሻገር፣ ለሕዝቡ ማንነት ባለው የጠላትነት መንፈስ ከተማዋንም ሆነ አገሪቷን ወደ ቀውስ በፍጥነት እና በጥልቀት እየገፋት ይገኛል፡፡

ከፍተኛ ሙስና ውስጥ እንደተዘፈቀም ሰሞኑን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለባለ እድለኞች ለመስጠት በወጣው የተጭበረበረ ዕጣ ወለል ብሎ ታይቷል፡፡ በዚህ ሂደት፣ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በከንቲባነታቸው ካለባቸው ሓላፊነት ባሻገር፣ በድርጊቱ መሪ ተዋናይ እንደነበሩ በርካታ መረጃዎች ተገኝቶባቸዋል፡፡

No photo description available.ከእነዚህ መካከል፥ የተጭበረበረው ዕጣ ከመውጣቱ ጥቂት ሰዓታት በፊት፣ በከንቲባዋ የተላከ አንድ ግለሰብ የታሸገውን ኮምፒዩተር ከፍቶ ሲነካካ እንደነበር እና መልዕክተኛው ምን ይሠራ እንደነበር የሚከታተል ሌላ ሰው በአጠገቡ ያልነበረ መሆኑ አንዱ መረጃ ነው፡፡

ይህ መረጃ፣ ከንቲባዋ በፖሊስ ለመጠየቅ የሚያበቃቸው መሆኑ የአገራችንን የቆየ የፍትህ ሥርዓት በርቀት እንኳን ለሚያውቀው የተሰወረ አይደለም፡፡ ከንቲባዋ የወቅቱ ቱባ ተረኛ ባለሥልጣን በመሆናቸው ግን ተጠያቂ እንዳይሆኑ ተደርገዋል።

ከዚህ በተጨማሪም፣ ከንቲባዋ የዕጣውን መረጃ የያዘ ፍላሽ፣ ከመንግሥት አሠራር ውጭ በግል መውሰዳቸውም ታውቋል፡፡ ከዚህ ቀደም ብሎ፣ እሳቸው በሚመሩት እና በሚቆጣጠሩት የከተማው አስተዳዳር የተሰራው የዕጣ ማውጫ ሶፍትዌር ለማጭበርበር እንደሚያመች ከፌድራሉ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በደብዳቤ እንዲያውቁት ተደርጎ፣ ምንም እርምጃ እንዳልወሰዱ ከመረጃም ባሻገር በማስረጃ ተረጋግጦባቸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያ ከህወሓት ጋር እየተደራደረች ነው? ኦቦሳንጆ ትላንት መቀሌ ዛሬ ባሌ ናቸው – መሳይ መኮነን

በዚህ አውድ፣ ከንቲባዋን ትቶ ሌሎች የአዲስ አበባ አስተዳዳር ባለሥልጣናት እና ሙያተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱ የፍትህ ሥርዓቱን ባዶነት እና አድሎኝነት አጋልጧል፡፡ ሁሉም ዜጎች በህግ ፊት እኩል ናቸው ከተባለ፣ የከንቲባዋ ያለመከሰስ መብት ተነስቶ በተነሱት ጥያቄዎች ላይ ለፖሊስ ቃላቸውን መስጠት ይገባቸዋል፡፡

ከንቲባዋ በህግ ሊያስጠይቋቸው የሚችሉ በርካታ ጉዳዮች እያሉ፣ በሥልጣን ላይ ያሉት ተረኞች ከለላ ሰጥተዋቸው የሚገኙት በአዲስ አበባ ማንነት፣ አስተዳደራዊ ነፃነት እና ስነ-ልቦና ላይ ከተከፈተው ሁለ-ገብ ጦርነት ጋር ካላቸው ቁርኝት አኳያ እንደሆነም የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡

በከተማዋ ላይ የተከፈተው ድምጽ አልባ ወረራ፣ በዚህ ሳምንት የመጨረሻው ከፍታ ላይ ደርሶ የኦሮሚያ ክልል ህገ መንግሥት በከተማዋ ተግባራዊ እንደሚሆን፣ እንዲሁም፣ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልል መዝሙር እንደሚዘመር እና ባንዲራውም እንደሚሰቀል ከከንቲባዋ አንደበት ተደምጧል፡፡

በመሆኑም፣ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ መንግሥት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ያሳስባል። እነዚህም፥

1. ከተጭበረበረው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ጋር በተያያዘ፣ የከንቲባዋ ያለመከሰስ መብት ተነስቶ ለህግ እንዲቀርቡ፣

2. የኦሮሚያ ክልል ህገ መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ እንዳይሆን፣

3. የኦሮሚያ ክልል ባንዲራና መዝሙር በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች እንዳይሰቀል እና እንዳይዘመር በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

293970528 632852735072652 813796078975163545 n

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ—- ሐምሌ 13/2014 ዓ.ም.

3 Comments

  1. ዱሮምኮ በለቤቷን የተማመነች በግ ላቷን ከውጭ ታሳድራለች አይደል ተረቱ፡፡
    እፉኝቱና አውሪኤው አብይ አህመድ ሽመልስ አብዲሳንና ( በጡንቻው የሚያስበውን) አዳነች አበቤን( ዘረፈች ገንዘቤን) አሰማርቶ ህዝቡን መከራ ስቃዩን እያሳየው ነው፡፤ ህዝቡም በተለይ አማራው በአግብዳጅ የአማራ ሆዳም ሹመኞች ተጠርንፎ በታሰሩና በመያዙ ሌላው ሁሉ ለጊዜው ቢቀር አለንታውን ፋኖን የሚያሳድደውን የተገዛ ሀይል እንኳን ሊከላከለው አልቻለም፡፡ ተው ሊለው አልቻለም፡፡
    ግደለም ለጊዜው ነው፡፤ ፋኖ አፈር ልሶ ይነሳል፡፡ በእርግጠኝነትም ድፍን የአማራ ሰፊ ህዝብ(46 ሚሊዮኑ) ከጎኑ በደጀንነት አብሮት ይሰለፋል፡፤ ለነገሩ አብይ የአማራ ህዝብ 46 ሚሊዮን ነው የሚለውን አያምንም ብቻ ሳይሆን እንደ ጦር ይፈራዋል፡፤ ወንድ ከሆነ እስኪ ተአማኒ የህዝብ ቆጠራ አስደርጎ እውነትነቱን ይረዳ???

    አማራ እያለቀ ያለው በአማራነቱ ተለይቶ ሲሆን መዳን የሚችለውም ተለይቶ በአማራነቱ በአንዲነትና በጽናት ቆሞ ከታገለ ብቻ ነው፡፡

    አዲስ አበቤ አትነሳም ወይ የባንክ፣ የህንጻ፣ የቦታና የገንዘብ ዘረፋ አይበቃህም ወይ ነው መዝሙሩ መሆን ያለበት፡፤ ካልጓሼ አይጠራምና ድብልቅልቁ ይውጣ፡፤ ለጊዜው ኦሮሙማ የተሳለ አደረጃጀት ስላለው ያሸነፈ ሊመስለው ይችል ይሆናል፡፡ በዘረፋና በቀፈፋ ተመራርጠውና ተመራርቀው ያዘጋጁት ድርጅትም ሆነ ወታደር የህዝብን አመጽ ፈጽሞ ሊመክት አይችልም፡፡ ወደፊት!!!

  2. አትልፉ ነገር አለሙ ሁሉ ጠምብቷል። ሰው በብሄሩ የሚምልበት ጊዜ ላይ ቆመናል። ያም የእኔ ጥያቄ ይመለስ፤ ይህ ደግሞ እኔ ብቻ ልኑርበት ከክልሌ ውጣ በማለት ሰውን እያሳደደ የሚያርድባት የሃበሻዋ ምድር እድል ፈንታዋ እየጨለመ ነው። ልክ እንደ ወያኔ ሃርነት (ባርነት) ትግራይና አሁን ሃገር እንደ ሆነችው ኤርትራ ሁሉም ለራሱ ሲቆርስ አለማሳነሱ የጸቡን ክፋት ያሳያል። ሰው አንድ ሃገር ላይ ተቀምጦ በወሰንና በድንበር የሚፋጅባት ሃገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት። በነጮች በ1936 ተቀስቅሶ በ1939 ገደማ የተገታው የስፔኑ የእርስ በርስ ፍጅች ያተረፈው እልቂትና የህዝቦቿን መበተን ነበር። ገና ስፔናውያኑ እፎይ ሳይሉ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተቀሰቀሰና አውሮፓን እየማገደ ስታሊንግራድ ድረስ ዘለቀ። ሰው በባህሪው አውሬ ነው። መኖርን ቢናፍቅም፤ ሌላው ግን እንዲኖር አይፈልግም። የእኛም የነጻ አውጭ ጋጋታ፤ የክልል ፓለቲካ፤ የብሄር ባንዲራ ማውለብለብና በየጊዜው ሊጨበጥ በማይችል ህልማዊ ሃሳብ መዘላበድ ያመጣውና የሚያመጣው የመከራ ዶፍ ነው። በምድር ላይ ያለውን እውነት ለይተን ማየትና ዓለም አቀፉን የፓለቲካ ትኩሳትና ቅዝቃዜ መመዘን አልቻልንም። ሶማሊያንና ኢትዮጵያን ስፍራ እየቀያየሩ ያኔ ያጋደሉን ሃይሎች ዛሬም አሰልጣኝና አስታጣቂዎቹ እነርሱ ናቸው። ግን በብሄሩ ለሰከረ ሰው ይህ አይታየውም። አሁን ያቺ ሶማሊያ ለሶስት ተከፍላለች። ሁልጊዜ ከወያኔ ጎን የምትቆመው ሱዳን ደግሞ ደ/ሱዳንን አጥታለች። ገናም ብዙ ገመና ይጠብቃታል። የራሷ እያረረ ለግብጽ ተላላኪ ሆና እንሆ ዛሬ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሳ ገብታለች። ፓለቲካ የወስላቶች የገበጣ ጫወታ ነው፡ ምዕራቡ ዓለም ይሁን ምስራቁ ፓለቲካቸው ሸፋፋና ወልጋዳ ነው። ዲሞክራሲ የሚባል ነገር በምድር ላይ የለም። ዝም ብሎ መዋዥቅ እንጂ። ዛሬ ዲሞክራሲ ሰፍኗል በምንላቸው ሃገሮች ጾታህ/ሽ ሲባሉ ጾታ የለኝም የሚሉ ጉዶች የሚተራመሱባቸው ከተሞች ሞልተዋል። ሰው ጠፈር ላይ ስለወጣ ስልክ እጅ ላይ ሰለገባ፤ ከንፎ ከስፍራ ስፍራ ስለተዘዋወረ ሰለጠነ አይባልም። ስልጣኔው በተግባሩ ነው። ተግባሩ ደግሞ እየቆየ ወደ እንስሳነት ባህሪ እየተቀየረ ነው። በሃበሻው ምድር የምናየው ጭካኔና አረመኔነት ከዚሁ ራስን ብቻ ከመውደድ የመነጨ ነው።
    እኔ የባልደራስ ደጋፊ አይደለሁም። ሲጀመር የፓለቲካ ድርጅቶችና ፓርቲ ነን የሚሉ ሁሉ እንደ ልጆች ጫወታ ሥራቸው ሁሉ “ጫወታ ፍርስርስ ያደረ እንጀራ ቁርስርስ” ስለሚሆንብኝ በጅምላ አልወዳቸውም። በተለይ ብሄር ነክ የሆኑትን ነፍሴ ትጸየፋቸዋለች። የማምነው ሰው በሰውነቱ እንዲመዘን በመሆኑ። ታዲያ ይህ ሁሉ እንኩሮ የፓለቲካ አቲካራ 99 መርፌ አንድ ማረሻ አይወጣውም እንዲሉ ዋጋ ቢስ ነው። የቆመን አፍርሶ ከመስራት ለጊዜውም ቢሆን ጠግኖ መገልገሉ አስፈላጊ ነበር። ግን ስንካሰስ፤ እከሌ ይውረድ፤ ትውረድ፤ ይታሰር፤ጊዜአዊ የሽግግር መንግስት ይቋቋም ስንል አለማፈራችን። ያውቃሉ ስንቶች “መሬት ላራሹ”ብለው አካላቸው እንደ ጎደለ ወይም እንደተሰው? አሁን ታዲያ መሬት የማነው? መልሱ ” የባለሃብትና ቀን የሰጠው” ነው። በሌላው ሞት ሻምፓኝ ከፍቶ ከሚጨፍሩ ጉዶች ጋር እንዴት ነው አዲስ ነገር መጀመር የሚቻለው? ጎበዝ አብደናል። ዞሮብናል። ስርቆቱ፤ ግድያው፤ የከተማና የገጠሩ የፍርድ መዛነፍና ሥርዓት አልበኝነት መብዛቱ ገና ብዙ መከራ ያዘንብብናል። የኦሮሞ ብሄራዊ መዝሙር ተማሪዎችን እንዲዘምሩ ማድረጉ ላሰቡት የኦሮሚያ ሪፕብሊክ ምስረታ ልምምድ ነው። ግን መኪና ያለጠጋኝ ዋጋ ቢስ ነው። የሃረሩ፤ የሽዋው፤ የአርሲው የሌላውም ኦሮሞ እንደ ወለጋው ኦሮሞ ያስባል ማለትም ገልቱነት ነው። አማርኛ ተናጋሪ ሁሉ አማራ እንደማይሆን ሁሉ፤ ኦሮሚኛ ተናጋሪ ሁሉ ኦሮሞ አይደለም። ሃገርን ለማፍረስ ከሚሰሩት ጋር ሁሉም ኦሮሞ አይሰለፍም። ያኔ ደግሞ ሌላ ጦርነት ይቀሰቀሳል። በሊቢያ፤ በየመን፤ በሶሪያ ያየነውና የምናየው እሱን ነው። ግን ማን ገዶት ለዛሬ ዘርፎ ካደረ ነገ ደግሞ ሌላ ዘራፊ ራሱ ዘርፎ ሊመለስ ወደ እማይችልበት አለም ይሸኘዋል። የመገዳደል ፓለቲካ ፍሬው መራራ ነው። ስንቶች ተበልተዋል አሁንም እየተበሉ ነው። ከላይ ባልደራስ ያስቀመጣቸው ሶስት ነጥቦች እንደ ወረድ ተሰሚነት አግኝተው ቢፈጸሙ ሌላ የሚያፋልጠን ነገር ፈልገን ከዜሮ እንጀምራለን። ይህም እግዚኦ አታድርስ፤ አውጣኝ ያሰኛል እንጂ ሌላ ቱሩፋት የለውም። በቃኝ!

  3. አዬ Tesfa …..የቆመን አፍርሶ ከመስራት ለጊዜውም ቢሆን ጠግኖ መገልገሉ አስፈላጊ ነበር።
    አዬ Tesfa …….ግን ስንካሰስ፤ እከሌ ይውረድ፤ ትውረድ፤ ይታሰር፤ጊዜአዊ የሽግግር መንግስት ይቋቋም ስንል አለማፈራችን።
    Tesfa:- ከዱሮ ጀምሮ በዘሀበሳ ላይ በምታቀርባቸ የደላላነት ጽሁፎችህ ማንነትህን በሚገባ እናውቃለን፡፤ የአውሬው አብይ አህመድ ተከፋይ ዲጂታል ነህ፡፡ ለአንተ ሀሳብ መልስ መስተት አያስፈልግም፡፡ ከላይ ከአንተው የቅዠት ጽሁፍህ copy-paste ተደርጎ የተቀመተልህ ሁለቱ ሀሳቦችህ ብቻ ማንነትህን ቁልጭ አድርገው ገላጮች ስለሆኑ ዝባዝንኬ አያስፈልግም፡፡
    እፈር!! አብይ ወደድክም ጠላህም እያለቀለት ያለ በማበድ ሂደት ውስጥ የሚገኝ ፍጡር ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.