የኦህዴድ አመራር በአዲስ አበባ ጉዳይ ሚስጥራዊ ስብሰባ አድርጎ ውሳኔ ማስተላለፉ ተሰማ!!

Abiy Ahmed Liarበጠቅላይ ሚኒስቴሩ መሪነት ከፍተኛ የኦህዴድ አመራር አባላት ሰሞኑን ሚስጥራዊ ስብሰባ አድርገው በአዲስ አበባ ጉዳይ ውሳኔ ማስተላለፋቸው ተሰማ፡፡
በስብሰባው ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ፣ አቶ አዲሱ አረጋ፣ የፌደራል ኮሚሽነሩ ደምመላሽ ገ/ሚካኤል እና ሌሎች ተገኝተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ጉዳይ በ2010 ዓ.ም ለተከሰተው ለውጥ ምክንያት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ፣ ይህም ቢሆን ባለፉት አራት ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ ከከተማዋ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም እስካሁን ማግኘት አልቻለም ብለው አማረዋል፡፡
ለዚህም ጥሩ ማሳያ ሰሞኑን የተካሄደው የኮንዶሚኒየም እጣ ነው ብለዋል፡፡ “እጣው ባይሰረዝ ኖሮ በኦሮሚያ ትልቅ ተቃውሞ ይነሳ እንደነበር እናውቃለን” ብለዋል።
እንደሚታወቀው፣ አብዛኛው የእጣው ተጠቃሚ ኦሮሞ መሆን ይገባዋል የሚል ቅስቀሳ ውስጥ ውስጡን እየተደረገ ይገኛል። እጣው የወጣ ዕለትም በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦህዴድ/ኦነግ/ሸኔ ያደራጃቸው ቄሮዎች በመኪና ተጭነው ወደ ከተማዋ በተለያዩ አቅጣጫዎች እንዲገቡ ተደርጎ ነበር። ጭፈራቸውን የከተማው ህዝብ በትዝብት ተመልክቶታል።
Addis Aba condoበመጭው ዓመት በከተማዋ ባሉ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልል መዝሙርና ባንዲራ ያለምንም ችግር እንዲሰቀልና እንዲዘመር የተቀናጀ እንቅስቃሴ መደረግ እንዳለበት፣ በኢኮኖሚው ዘርፍ ባለሀብቶችን መፍጠር እንደሚያስፈልግ፣ የኢኮኖሚውን በላይነት ሳይያዝ አዲስ አበባን መቆጣጠር እንደማይቻል አመራሮቹ አፅንኦት ሰጥተውታል፡፡
ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያ ክልል በከተማዋ ውስጥ ያለውን የአስተዳደር፣ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ቁመና ለማሳደግ እስካሁን የተሰራው በቂ አይደለም ብለው አማረዋል፡፡
በጥቅሉ፣ ተሰብሳቢዎቹ አዲስ አበባን የኦሮሚያ አካል የማድረግ እንቅስቃሴው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጠው መለያየታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዘገባው—- ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ
ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢዜማ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን በድጋሚ መሪ አድርጎ መረጠ

Leave a Reply

Your email address will not be published.