የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ቀውስና የአይኤምኤፍና የዓለም ባንክ ፕራይቬታይዜሽን ሴራ!!! የብሔራዊ የጋራ ኃብታችን በኦሮሙማ ውርስና ስልቀጣ?

(ክፍል 4)  ሚሊዮን ዘአማኑኤልና ፂዮን ዘማርያም  (ኢት-ኢኮኖሚ)

ኢትዮጵያ በአይኤምኤፍና ዓለም ባንክ  የፕራይቬታይዜሽን ፈንጂ ወረዳ!

በዶክተር ኢዮብ ተስፋዬ በሪፖርተር ጋዜጣ እሁድ ሰኔ 17 ቀን 2010 ዓ/ ም በፁሁፍ ያቀረቡት ‹‹ኢኮኖሚው ያጋጠሙትን የማክሮ ኢኮኖሚ ተግዳሮቶች ለማቃለል የቀረበ የመፍትሄ ሐሳብ››……………………..……….(1)

‹ስለአገራችን የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ችግር በአቶ ሚሊዮን ዘአማኑኤልና በጽዮን ዘማርያም የቀረበውን ጽሁፍ የሚመለከት ሀተታዊ  ትችት!  ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ነሐሴ 21፣ 2022  የቀረበውን ገንቢ አስተያየት እያመሠገንን በዶክተር ኢዮብ ተስፋዬ የቀረቡ ስምንት የመፍትሔ ሃሳቦች (1) ከምንጩ ይመልከቱ) ስምንተኛውን የፕራይቬታይዜሽን ሚና ከማቅረባችን በፊት የቀረበ አስተያት መሆኑንና እርዕሱ ‹‹ የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ቀውስና የአይኤምኤፍና የዓለም ባንክ  ፕራይቬታይዜሽን ሴራ!!!›› የሚለው ርዕስ ሙሉው ፁሁፍ ሳይቀርብ የቀረበ ትችት መሆኑን ዶክተር ፍቃዱ በቀለ በትህትና እንዲያውቁልን እንሻለን፡፡ የሃገራችንን የኢኮኖሚ ዘርፎች  በቀላሉና ምንም ሰው አንብቦ ለመረዳት  እንዲችል የኢኮኖሚክስ ጹሁፎች መቅረባቸው በማመስገን ሌሎችም በዘርፉ ያሉ ጥናታቸውን እንዲያቀርቡ  እንመኛለን፡፡

{8} የፕራይቬታይዜሽን ሚና:-

‹‹ የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ ሙሉ በሙሉ በከፊል ወደ አገር ውስጥ ባለሀብቶችና ለውጭ ባለሀብቶች በሽያጭ የሚተላለፉ ‹‹ከፍተኛ›› የሆኑ የመንግስት ተቌማትን ይፈ ካደረገ በኃላ የተዘበረረቁ  አስተያየቶችና ስሜቶች በመደመጥ ላይ ናቸው፡፡ ለመሆኑ መንግሥት በሽያጭ  የሚያስተላልፋቸው ኩባንያዎች  የውጭ ዕዳ ጫናን ብቻ ለማቃለል ተብሎ የተወሰደ እርምጃ ነውን? ይህ ፕራይቬታይዜሽን ከመንግሥት ስትራቴጂክ ጋር ይጣረሳል? የግል ባለሃብቱ ሳይጠናከር  ፕራይቬታይዜሽኑን መካሄድ አግባብ ነው? ወዘተ የሚሉትን  ጥያቄዎች መመለስ ተገቢ ይሆናል፡፡››

‹‹ በመጀመርያ ፕራይቬታይዜሽን ዓላማ ለኦኖሚው መዋቅራዊ ሽግግርን (Structural transformation)

ከማምጣት አኳያ  የጎላ ሚና እንዳለው  የበርካታ  አገሮችን ልምድ ማንሳት ይቻላል፡፡ መንገሥት ያቀደው  ፕራይቬታይዜሽን ፕሮግራም ምንም  እንኳ የውጭ ዕዳ ጫና  አንዱ ምክንያት ቢሆንም መንግሥት ልክ ገንዘብ እንደቸገረው  ንብረቱን ሸጦ  ዕዳውን እንደሚከፍል  ግለሰብ ተበዳሪ ሳይሆን    ፕራይቬታይዜሽኑ ይዞ  የሚመጣውን ሀብት በአግባቡ  ተጠቅሞ ከተሸለ የኢኮኖሚ ውጤት (Economic efficiency) ምርትና ምርታማነት ከመጨመር ከሥራ ዕድል ፈጠራ ከቴክኖሎጂና ከካፒታል አቅምና ከዘመናዊ  አስተዳደር በመነጨ በጥራት ላይ የተመሠረተ ምርትና አገልግሎትን በማቅረብ ተወዳዳሪነትን  ለማጠናከርና የዓለም ገበያን ሰብሮ ለመግባት የሚያስች አቅም መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡››

‹‹ መንግሥት ገንብቶ አስተዳድራቸዋለሁ ያላቸው እንዲሁም እስከ ዛሬ በበላይነት ሲያስተዳድራቸው የነበሩ ኩባንያዎች ለኢኮኖሚው የራሳቸውን ድርሻ  ቢያበረክቱም አሁን ያጋጠመው የኢኮኖሚ ተግዳሮቶችን  ለመወጣትና የተሸለ የኢኮኖሚ የመወቅር ሽግግር ለማምጣት የኢኮኖሚውን የአካሄድ ሥልት  መቀየር የግድ ነው፡  የሥልት ወይም የአካሄድ ቅየራ የስትራቴጂ ቅየራ አለመሆኑ  ሊሰመርበት ይገባል፡፡  የማሌዥያ  ተሞክሮን  ለአብነት ማንሳት ይቻላል፡፡  ማሌዥያ የልማታዊ መንግሥት  ስትራቴጂን ከሚከተሉ አገሮች በዋናነት  የምትጠቀስ ሲሆን  መንግሥት የልማታዊ መንግሥት ኃላፊነቱን በተሸለ  ለመወጣትና የግል ባለሃብቱ የኢኮኖሚ መሪ እንዲሆን በሞኖፖል የያዘውን የኤሌትሪክ ኩባንያና ሌሎችንም ድርጅቶች ወደግል ይዞታ በማዛወር የኢኮኖሚ ሽግግሩን  ሊያሳልጥ ችሎል፡፡ የሲንጋፖር የደቡብ ኮሪያ  ልማታዊ መንግሥታት ተመሳሳይ አካሄድ ተከትለዋል፡፡››

‹‹መንግሥት ሲገነባቸው የነበሩና የገነባቸውን ተቆማት ለግል ባለሃብቱ ቢያዛውር፣  የግል ሴክተሩ ከባንኮች የሚያገኘው  የብድር መጠን የሚጨምር ሲሆን (ምክንያቱም የመንግሥት የሚበደረውን የብድር መጠን ስለሚቀንስ) የግል ክፍለ ኢኮኖሚው ለማደግና ለመስፋፋት አመቺ እድል ያገኛል፡፡ በመንግሥት ፕሮጀክቶች ላይ ጥገኛ ከመሆን ቀጣይነት ያለው የግል ሴክተር (Sustainable private sector) እንዲኖር ከተፈለገ መንግሥት የግሉ ሴክተር የብድር መጠን እንዳያገኝ  አድርጎል ወይም እንቅፋት ሆኗል የሚባለውን ለመቅረፍ ያግዛል፡፡››

‹‹ፕራይቬታይዜሽን ሲታሰብ ግን የድርድር የዋጋ ትመና፣ የክትትልና የቁጥጥር አቅም መኖር ማረጋገጥ መንግሥት በውጭ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን አቅም  መጠቀም ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ትርፋማና  ውጤታማ የሆኑትን በተለይም በከፍተኛ ፍጥነት አቅሙ የተገነባውን የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ  በከፊል በሽያጭ ለግል ባለሀብት ከማስተላለፍ መለስ ያሉ ሌሎች አማራጮችን (የአየር መንገዱን ሼር በዓለም አቀፍ የስቶክ ገበያ ፍሎት ማድረግን) መፈተሸ ያስፈልጋል፡  መንግሥት የኩባንያዎቹን ባለቤትነት በሙሉ ወይም በከፊል ሽያጭ በጥንቃቄ  ማስተላለፍ  ተገቢነት ያለው ከመሆኑም በላይ፣ የፋይናንስ ሴክተሩም ባልተራዘመ ጊዜ ለውድድር  ክፍት ማድረግ  ይጠበቅበታል፡፡ የኢኮኖሚ መዋቅር  ሽግግሩን ለማቀላጠፍ  የፋይናንስ ሴክተሩን  በሒደት ለውድድር  ካልተከፈተ ፕራይቬታይዜሽኑ  ለብቻው የሚፈለገውን ሽግግር  አያመጣም፡፡  ዋናውና ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ  ግን ፕራይቬታይዜሽኑ  የአጠቃላይ የኢኮኖሚ ሪፎርም አካል  ተደርጎ መውስድና ቀጣይ የኢኮኖሚ የፖሊሲ  ማሻሻያዎችን ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎችን በማድረግ ይጀምራል፡፡››   በማለት ዶክተር ኢዮብ ተስፋዬ ሰኔ 17 ቀን 2010ዓ/ም በፁሁፍ ያቀረቡት ‹‹ኢኮኖሚው ያጋጠሙትን የማክሮ ኢኮኖሚ ተግዳሮቶች ለማቃለል የቀረበ የመፍትሄ ሐሳብ›› ይደመድማል፡፡ ዶክተር ኢዮብ ተስፋዬ እንደ ማሌዥያ፣ ሲንጋፖር፣ የደቡብ ኮሪያ  ልማታዊ መንግሥታት ተመሳሳይ አካሄድ የ‹‹ፕራይቬታይዜሽን››  ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ መንግሥት ተግባራዊ ቢደረግ ውጤታማ እንደሚሆን እምነት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡ በእኛ እምነት ደግሞ በህወሓት ኢህአዴግ መንግሥት ዘመን የተካሄደው የ1980 እስከ 2000 ዓ/ም 365 (ሦስት መቶ ስልሳ አምስት) የመንግስት ኮርፖሬሽኖችንና  ንብረቶች ባለቤትነትን ወደ ግሉ ዘርፍ ንብረትነት የማዘዋወር ፕሮግራም ውጤቱ ውድቀት እንደሆነ ጥናታዊ መረጃው ለህዝብ ይፋ ማድረግ ከዶክተር ኢዮብ ተስፋዬ ይጠበቃል እንላለን፡፡ ይህን ሳያደርጉ ሁለተኛውን አትራፊ የሆኑ መንግሥታዊ ኮርፖሬሽኖችን በፕራይቬታይዜሽን በመሸጥ  ሃገራችን ተጠቃሚ መሆን ለመቻሎ የሚያሳምን መረጃ ማቅረብ ግን ግድ ይላል፡፡ ስለዚህ ‹‹ኢኮኖሚው ያጋጠሙትን የማክሮ ኢኮኖሚ ተግዳሮቶች ለማቃለል የቀረበ የመፍትሄ ሐሳብ››  በፕራይቬታይዜሽን ላይ ያለንን ልዩነት እናስቀምጣለን፡፡

‹‹ የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ቀውስና የአይኤምኤፍና የዓለም ባንክ  ፕራይቬታይዜሽን ሴራ!!!›› የአህያ ባል ጅብ አያስጥልም!!!

የአይኤም ኤፍና የዓለም ባንክ የኢኮኖሚ መዋቅር  ሽግግር መርሃ-ግብር ለሦስተኛው ዓለም አገሮች ለማደህየትና ከተረጅነት እንዳይላቀቁ የተበተቡት የስውር ቅኝ አገዛዝ ሥርዓት ዋነኛ ሴራ ነው፡፡ ደሃ አገሮች ለምዕተዓመት በምግብ ራሳቸውን እንዳይችሉ በማድረግ ስንዴ እየሠፈሩላቸውና ህሊና አልባ አሻንጉሊት መንግሥቶችን እየፈለፈሉ ስውር አገዛዛቸውን በመጫን የኢኮኖሚ መዝበራቸውን ማስቀጠል ችለዋል፡፡ የደሃ አገሮችን የግብርና ምርቶች በርካሽ በመግዛት፣ ምሁራኖቹን በማስኮብለል፣ ርካሽ ባህላቸውን በመጫን፣ ትውልዱን በአደንዛዥ ዕጽ በመበከል  ጥቅማቸውን ማስከበር ዋነኛ ዓላማቸው ነው፡፡ ዱሮ መሬትህ ነበር በቅኝ አገዛዝ የሚያዘው ዛሬ ሰውነትህን ስብዕናህን የቅኝ ገዥዎች ሚዲያ አደንዝዘው ሊይዙትና ሊገዙት ይሻሉ!!!  የውጪው ሚዲያዎች በሁለት ወንድማማቾች ጦርነትን ግፋ በለው ይላሉ፣ ያንዲት ኢትዮጵያ ልጆች መሆናችንን ረስተዋል!!! ከእናት አገራችን ኢትዮጵያ ኤርትራን አስገንጥለዋል፣ ትግራይን ለማስገንጠል ሽር ጉድ እያሉ ይገኛሉ፡፡ በአንደኛውና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት አውሮፓ ሃገራትና አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጎን ቆመው አያውቁም፡፡ ትግራይን መንግሥት የማድረግ የምዕራባዊያንን የፖለቲካ ሴራ ትግራዊያን ያከሽፉታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ‹‹የኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት በ2.56 ቢሊዮን ዶላር አሽቆልቁሏል!!!›› ምነው ጃል አብይ!!!

አይኤምኤፍና የዓለም ባንክ በፕራይቬታይዤሽን ስም የታላቆ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፣ ኢትዮቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንና ሌሎችም በሙሉና በከፊል ለሽያጭ  የሚቀረቡ ድርጅቶች በእጅ አዙር እንዲሸጡ በመደለል ላይ ይገኛሉ፡፡ ለሃገራችን ውድቀት እንጂ እድገት ይዞ አይመጣም እንላለን፡፡ ሃገር በቀል የሆኑ የሃገር ውስጥና ዲያስፖራው ወገኖች እነዚህን ድርጅቶች በአክሲዮን እንዲገዙ በማድረግ ሁኔታውን ማመቻቸት ያስፈልጋል፡፡  ከደርግ መንግሥታዊ የፓርቲ የልማት ድርጅቶች ወደ ህወሓት ኢህአዴግ  መንግሥታዊ የፓርቲ የልማት ድርጅቶች ብሎም ወደ ኦዴፓ ብልፅግና መንግሥታዊ የፓርቲ የልማት ድርጅቶች መሸጋገሩ ሂደት መቆም አለበት እንላለን፡፡

  • ከ1980 እስከ 2000 ዓ/ም የመንግስት ኮርፖሬሽኖችንና  ንብረቶች ባለቤትነትን ወደ ግሉ ዘርፍ ንብረትነት ማዘዋወር ዓለም ዓቀፋዊ ክስተት በመሆን በበለፀጉ አገሮች፣ በታዳጊ አገሮችና በሽግግር ኢኮኖሚ ላይ በሚገኙ አገሮች ሁሉ ተፈፃሚ ሆነዋል፡፡ በታዳጊ አገሮች ውስጥ የመንግስት ኮርፖሬሽኖችንና  ንብረቶች ወደ ግሉ ዘርፍ መተላለፍና መሸጥ ዋነኛ ምክንያቶች መኃል፣ (1) የገንዘብ አያያዝ ብክነትና ሙስና  በየግዜው እየጨመረ መሄድ፣ (2) ንብረቶቹን የማስተዳደር ብቃት ደካማነት (3) በዚህም ምክንያት በየአመቱ የመንግስት ድጎማ እየተደረገላቸው በኪሳራ መስራታቸው ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኢህአዲግ ዘመን የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ባለፈው 27 አመታት ውስጥ 365 መንግስታዊ ድርጅቶች ወደ ግል ዘርፍ አዘዋውሮል፡፡ከ1996 ዓ.ም እስከ 2006 ዓ/ም እኢአ ድረስ ከመንግስት ወደግል ዘርፍ ንብረትነት ካዘዋወራቸው ወይም ከሸጣቸው የመንግስት ልማት ድርጅቶች 18.3 ቢሊዩን ብር  ገቢ ተገኝቶል፡፡
  • በደርግ ዘመን የተወረሱ መንግስታዊ የልማት ድርጅቶች በፕራይቬታይዜሽን ፕሮግራም ተሸጠው ወደ ኢህአዴግ ድርጅቶች በእጅ አዙር እንደተሸጡ የአደባባይ ሚስጢር ነው፡፡ የህወሓት ኢፈርት፣ የብአዴን ጥረት፣ የኦህዴድ ዲንሾ እና የደቡብ ወንዶ መንግሥታዊ የልማት ድርጅቶች ህልውና ምን እንደሆነ የተባለ ነገር የለም፡፡ በዶክተር አብይ አህመድ ዘመን  የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች (State Owned Enterprise)፡- የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ከህወሓት ኢህአዴግ መንግሥት መንግሥታዊ ዘርፍ ኢንቨስትመንት በማስፋፋት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር በመውሰድ አትራፊነታቸው ያልተረጋገጠ ፕሮጀክቶች በመገንባትና የግሉ ዘርፍ ሊሰራቸው የሚችሉትን ሥራዎች በመሻማት ዘለቄታና ቀጣይነት የሌላቸው ፕሮጀክቶች በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በህወሓት ኢህአዴግ የሃያ ሰባት አመታት አገዛዝ ዘመን 780 ቢሊዩን ብር እዳ ያለባቸው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች እንደ ኢፈርት ድርጅት ዓይነቶችን በኦህዴድ ብልፅግና ዳግም እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡
  • በዓለም ዓቀፋ የገንዘብ ድርጅት ተቌምና በዓለም ባንክ ግዳጅና ተፅዕኖ የመንግስታዊ መዋቅር ወይም አቅም ስርዓት ማሻሻያ መርሃ-ግብር (structural adjustment program) ለማሻሻልና ለመቀየር የመንግስት ኮርፖሬሽኖችንና  ንብረቶች ባለቤትነትን ወደ ግሉ ዘርፍ ንብረትነት ማዘዋወር ዋነኛው ምክንያት ሆነ፡፡ የዓለም ዓቀፍ ፋይናንሻል  ኢንስቲቱሽን በተለይ  በታዳጊ አገሮች ላይ ትልቅ ጫና በመፍጠር ፕራይቬታይዜሽን መርሃ-ግብር ከመንግስታዊ መዋቅር ማሻሻያ ፕሮግራም ዋነኛ አካል እንደሆነ ተሰበከ፡፡ በዚህም ምክንያት በብዙ ታዳጊ አገሮች የፕራይቤታይዜሽን ሽግግር በብቃት፣ በእኩልነትና በግልፅነት ለማካሄድ አስፈላጊው ግዜና ጥናት ባለመካሄዱ የተኮላሸ ለመሆን በቅቶል፡፡ በታዳጊ አገሮች ውስጥ (1) የገበያ ውድድር ያለመኖር፣ (2) የመዋለ-ንዋይ ፍሰት ደካማነት፣ (3) የፋይናንሻል ሃብት እጥረትና (4) የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚጫወተው ሚና ደካማነት ወዘተ ተደማምሮበት የፕራይቬታይዜሽን ሽግግር የተጨናገፈ ለመሆን በቅቶል፡፡

ሊብራላይዜሽን (ኢኮኖሚውን ክፍት ማድረግ)  ከአይኤምኤፍና የዓለም ባንክ የብርድ አቅርቦት ለማግኘት ትርፋማ የሆኑ የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ፕራይቬታይዝ ማድረግና ኢኮኖሚውን ክፍት የማድረግ ፕሮግራም ግዴታ እንደሆነና ይህንንም መንግሥት እየተገበረው እንደሚገኝ ተገልጸል  ለዚህም የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ ለመሸጥ የተያዘው ዕቅድና የቴሌኮም ሊብራላይዜሽን ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ ከሚችሉት ጉዳዮች አንዱ የፋይናንስ ዘርፉን ክፍት  በማድረግ የውጭ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ማድረግ በመሆኑ የአገር ውስጥ ባንኮችና ኢንሹራንሶች ከፍተኛ ውድድር እንደሚጠብቃቸው ተገምቶል፡፡ ሌላው የዓለም ባንክ ስትራክቸራል አድጀስትመንት በሊብራላይዜሽን ፕሮግራም ሥር እንዲፈጸም የሚጠይቀው ለውጭ ኩባንያዎች ዝግ የነበሩ ዘርፎች ተከፍተው የውጭ ተወዳዳሪ ኩባንያዎች እንዲመጡ የሚያስገድድ መሆኑን ታውቆል፡፡  ”The partial privatization of Ethio Telecom aims to make the company, which has some 44 million subscribers out of a total population of about 110 million in Ethiopia, more efficient.”

የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ፡- ከኢትዮጵያ 110 (መቶ አስር ሚሊዮን) ህዝብ ውስጥ 44 (አርባ አራት ሚሊዮን) ደንበኞች ያሉትን ትርፋማ ድርጅት በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ፕራይቬታይዝ በማድረግ ሃገራችን ያለባትን 55.6 (ሃምሳ አምስት ነጥብ ስድስት) ቢሊዮን ዶላር ብድር ለመክፈል ከአይኤም ኤፍና የዓለም ባንክ ብድር በማግኘት የኢኮኖሚ ቀውስ ወጥታችሁ የኢኮኖሚያ ተሃድሶ ታገኛላችሁ በሚል ተስፋ ነው ትርፋማው ድርጅት ለፕራይቬታይዤሽን ገበያ የቀረበው፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም ሀብት በመንግሥት ከተገመተው 42 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጾል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከጥቂት ወራት በፊት የኢት ቴሌኮምን የተከፈለ ማሚያ ካፒታልን ከ 40 (አርባ) ቢሊዮን ብር ወደ 400 (አራት መቶ) ቢሊዮን ብር ማሳደጉ ይታወሳል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ጂዲፒ ስድስት ትሪሊዮን ሁለት መቶ ሃያ ሁለት ቢሊዮን ብር ተመነደገ!!! (122 ቢሊዮን ዶላር!!!) የመደመር ኢኮኖሚክስ!!! ‹‹ምን ቢታለብ በገሌ!

በመዋቅራዊ ተሃድሶ ፕሮግራም የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሠረት (1) የመንግስታዊ ተቆማት ወጭዎችን መቀነስ፣ (2) ግብርና ታክስ መጨመር፣ (3) የዋጋ ንረትን መቀነስ፣  (4) የንግድ ጥበቃ ወይም ከለላ ማንሳት (5) ኢኮኖሚያዊ ነፃ ንግድን መክፈት የመሳሰሉት የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች መተግበር የአይኤም ኤፍና የዓለም ባንክ ብድር ለማግኘት የተጣለ ግዴታ ነው፡፡ ኢኮኖሚውን ክፍት በማድረግ (ሊብራላይዤሽን) ለውጭ ኩባንያዎች ፈቃድ መስጠት መጀመሩንና ከቴሌ ኮሙዮኒኬሽን ዘርፍ በተጨማሪ መንግሥት ወደ ግል የሚዛወሩትን የመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን 13 የስኳር ፋብሪካዎች፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንና ሌሎችም በሙሉና በከፊል ለሽያጭ  የሚቀረቡ ድርጅቶች ናቸው፡፡

“A structural adjustment Program is a set of economic reforms that a country must adhere to in order to secure a loan from the International Monetary Fund and/or the World Bank. Structural adjustments are often a set of economic policies, including reducing government spending, opening to free trade, and so on.” የብልጽግና መንግስት ከአይኤም ኤፍና ዓለም ባንክ ብድር በማግኘትና ኢኮኖሚውን ክፍት ለማድረግ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ላይ ያለውን 45 (አርባ አምስት) በመቶ ድርሻ ለግል ባለኃብቶች ኢንቨስተሮች የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ ለመሸጥ ተስማምቶል፡፡ በዚህም መሠረት የኢትዮቴሌኮም ከፊል 45 በመቶ ድርሻ የኬንያ ሳፋሪኮም 850 (ስምንት መቶ ሃምሳ) ሚሊዮን ዶላር በመሸጥ እንዲሁም በሚቀጥሉት አስር አመታት ውስጥ የ8.5 (ስምንት ነጥብ አምስት) ሚሊዮን ዶላር ወጪ  ኢንቨስትመንቱን ለማስፋፋት እቅድ ነድፎል፡፡ “At the end of May, one of the licenses was awarded to a consortium led by Kenya’s Safaricom, which offered $850 million and also plans to invest $8.5 million over ten years, according to the authorities.”

ከህወሓት ኢህአዴግ ልማታዊ መንግሥት ወደ ኦህዴድ ብልፅግና ልማታዊ መንግስት  የኢኮኖሚ ውድቀት

  • የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲም በዘረኛነትና በተረኛነት ስሜት አዲስ አበባን ከተማ ዲሞግራፊውን ለመቀየር ‹‹ፊንፌኔ ኬኛ›› የፖለቲካ ሴራ ብዙ ንጹሃን ዜጎች ከከተማዋ ሲያፈናቅሉ ኮንዶሚኒየም ሲዘርፉ ተስተውለዋል፡፡ የኦዴፓ ብልፅግና የኦሮሙማ በአዲስ አበባ ህዝብ ውስጥ የመስፋፋት ፖሊሲ የጥላቻ ቅስቀሳ በመንዛት በከተማው ህዝብ ላይ  የዘር  ፍጅት የጥላቻ ቅስቀሳ ይስተዋላልል፡፡ ዶክተር አብይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳ፣ አዳነች አቤቤ  ለአንድ ዘር ኮንዶሚኒየም ቤቶች በአድሎ በማደል የአፓርታይድ ሥርዓት ፖሊሲ በከተማው ውስጥ አስፋፍተዋል፡፡
  • በአዲስ አበባ የኦሮሙማ መንግሥታዊ ተቆማት ግንባታ የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት መር ኢንቨስትመንት፡- በኦሮሚ ክልል የኦነግ ሸኔ ሽብር የተነሳ፣ የግል ኢንቨስትመንት ዋስትና ባለመኖሩ የተነሳና ብዙ ኢንቨስተሮች ከክልሉ መውጣት ዋና ምክንያት ንብረትና ኃብታቸው የወደመባቸው ባለኃብቶች ከመንግሥት ምንም የዋስትናና ደህንነት ጥበቃና ካሣ ባለማግኘታቸው ነው፡፡ የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት መር ኢንቨስትመንት ወጪ በናሙናነት (1) የኦሮሞ ክልል ፍርድ ቤት ግንባታ በ1.8 (አንድ ቢሊዮን ስምንት መቶ ሚሊዮን) ብር፣ (2) የኦሮሚያ ፖሊስ ፅህፈት ቤት በ700 (ሰባት መቶ) ሚሊዮን ብር፣ (3) ለኦሮሚያ ጀግኖች መታሰቢያ  አንድ ቢሊዩን ብር በጠቅላላው ሦስት ቢሊዮን አምስት መቶ ሚሊዮን ብር በማውጣት መንግሥት መር ኢንቨስትመንት ወጪ ጨምሮል፡፡ (4) ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (Oromia Broadcasting Network)ህንፃ ግንባታ 1.5 billion dollar (5) የኦሮሚያ ባህል ማዕከል ግንባታ ቦታ  ወዘተ በማስፋፋት ላይ ይገኛል፡፡

ውኃ ቅዳ፣ ውኃ መልስ ፕሮግራም

ካች አምና  መንግሥት መር ኢንተርፕራይዞች ግንባታ፣ ዘንድሮ በፕራይቬታይዜሽን የመሸጥ ፕሮግራም!!!

  • የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት መር ኢንቨስትመንት ውስጥ (1) ኦዳ ኢንቲግሬትድ ትራንስፖርት አክሲዩን ማህበር ODAA Integrated Transport S.C.፣ (2) ኬኛ ቤቬሬጅ(ኬኛ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ) Kegna Beverages  ኬኛ ቤቬሬጅ በጊንጪ ከተማ የሚገነባ ሲሆን 5.5 (አምስት ቢሊየን አምስት መቶ ሚሊዮን) ብር የግንባታ ወጪ የሚሰራ ሲሆን አንድ መቶ አንድ ሄክታር መሬት ላይ ግንባታው ያርፋል፡፡ (3) ኬኛ የግብርና ትራክተር መገጣጠሚያና ማሽነሪዎች Kegna Agricultural Machinery፣ኬኛ የትራክተር መገጣጠሚያ ማሽነሪ በሻሸመኔ ከተማ በ37000 (ሰላሳ ሰባት ሽህ ) ስኩየር ሜትር  ላይ የተገነባ ፋብሪካ ሲሆን በሃምሳ ሠራተኞች ሃያ ትራክተሮች  በቀን የመገጣጠም አቅም አለው፡፡  (4) የኢትዮጵያ አብሥራ ዓየር መንገድ፡- የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ (Ethiopian Airlines) የአፍሪካን ትልቁን ዓየር መንገድ ለመስራት ማቀዱን አስታውቆል፡፡ ዓየር መንገዱ ይህን እቅዱን ለማሳካት አምስት ቢሊዮን ዶላር (ሁለት መቶ ስልሳ ቢሊዮን) ብር የግንባታ ወጪ ይጠይቀናል፡፡ የአዲሱን ዓየር መንገድ ትልቅ ኢንቨስትመንት እንደሆነ በቀላሉ ለመረዳት የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አምስት ቢሊዮን ዶላር የግንባታ ወጪ ጋር እኩል መሆኑን በመገንዘብ ነው፡፡ አዲሱ ዓየር መንገድ በውድድር ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት፣ ብዙ መንገደኞችን በማስተናገድ ከደቡብ አፍሪካው ጆሃንስበርግ ዓየር ማረፍያ የበለጠ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅበታል፡፡
  • ከተማት ግንባታ በፊት የሰው ኃይል መገንባት ይቅደም!(1) ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (Oromia Broadcasting Network) ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ  አንድ ቢሊዮን አምስት መቶ ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚገነባ ተገልፆል፡፡    ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ የሚዲያ እውቀትና ልህቀት በሌላቸው አድርባይ ምሁራን የተሞላ በጥላቻ ንግግርና የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ ወንጀል ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ኦሮሙማ ጨፍላቂ ባህል ፀረ-ዴሞክራሲ ባህል ነው፡፡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መሪ ሽመልስ አብዲሳ የጥላቻ ንግግርና የዘር ማፅዳት ቅስቀሳ ነገ በዓለም አቀፍ ወንጀለኖች ፍርድ ቤት ቀርቦ ፍርዱን ማግነቱ አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡ (2) የአፍሪካ ቀንድ ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ  (‘OBN Horn of Africa’) የአፍሪካ ቀንድ ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ  በአፍሪካ ቀንድ አገሮች የኢኮኖሚ ግንኙነትን በማሳለጥ ትልቅ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው  ተገልፆል፡፡  የአፍሪካ ቀንድ ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ  በምስራቅ አፍሪካ፣ በአፍሪካና ለዓለም ዜናውን በማሰራጨት ስራውን ጀምሮል፡፡ አንዴ በዘጠኝ አንዴ ባስራ ዘጠኝ የሃገር ውስጥና በውጪ ቌንቌዎች ስርጭቱን ጀምራል፡፡ በተመሳሳይ የኦሮሞ የውጪ ብሮድካስቲንግ  ስቱዲዬና ሦስት ኤፍኤም ስቱዲዬ በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ በሦስት መቶ ስልሣ ሚሊዮን ብር ወጪ ተገንብተው በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ተመርቀዋል፡፡  (3) የሕክምና መንደር ግንባታ 300 ሚሊዮን ዶላር ወይም 12 ቢሊዮን ብር ወጪ ይገነባል፡፡ በአዲስ አበባ ቦሌ ሃያት ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ዓድዋ ፓርክ ሜዳ  ላይ ከተማዋን የጤና ቱሪዝም ማዕከል በ12 ቢሊዮን ብር የሚፈጀው የሕክምና መንደር ግንባታ ተጀመረ፡፡ (4) የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ 40ዎች ወዘተ ጊዜ ስልጠና ተደርጎል፡፡ የአዲስ አበባ የፌዴራል ፖሊስ ተቆም ግንባታ ባለው ከመጠቀም ይልቅ በሌለ ገንዘብ ህንፃ ከመቆለል ማለትም ከቁሳዊ ልማት ይልቅ ስብዓዊ ልማት ለፖሊስ ሠራዊት አባላት ኮሌጅ በመክፈት እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን በዲጂታል ቴክኖሎጂ መገንባት ያሻል እንላለን፡፡
  • ለአዲስ የአብይ አህመድ (1) ቤተ-መንግሥት ግንባታ 49 (አርባ ዘጠኝ) ቢሊዮን ብር ወጪ የግንባታ ወጪ ከፈረንሳይ ለጋሲዬን፣ እስከ የካ ወረዳ አስር ከበዶ እስከ የእንጦጦ ስንሰለታማ ተራሮች ያካተተ ብዙ ህዝብ የሚያፈናቅል ግንባታ ተጀምሮል፡፡ በጀቱ ከየት መጣ!!! (2) ለአንድነት ፓርክ አምስት ቢሊየን ብር ወጪ፣ (3) እንጦጦ ፓርክሁለት ነጥብ አምስት ቢሊየን ብር ወጪ፣ (4) አድዋ ዜሮ ኪሎሜትር አራት ነጥብ ስድስት ቢሊየን ብር ወጪ፣ (5) መስቀል አደባባይ ሁለት ነጥብ ስድስት ቢሊየን ብር ወጪ፣ (6) ወዳጅነት ፓርክ ሁለት ነጥብ አምስት ቢሊየን ብር ወጪ፣ (7) ቢተወድድ ጎሹ ወ/ፃዲቅፓርክ መቶ አንድ ሚሊዮን ብር ወጪ፣ (8) አንባሳደር ፓርክ አርባ ዘጠኝ ቢሊየን ብር ወጪ፣ እንዲሁም (9) የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት እድሳት ሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር  ወጪ በጀት ተይዞላቸው የተገነቡ አይደሉም፡፡
  • የኦዴፓ/ኦህዴድ ብልጽግና ፓርቲ መንግሥታዊ ዘረፍ ወጪ በዶክተር አብይ የአራት አመት አገዛዝ እየጨመረ መሄዱን በአንድ በኩል ለመንግሥታዊ ዘርፍ የተሰጠ ብድር 530 (አምስት መቶ ሠላሳ) ቢሊዮን ብር ሲሆን በሌላ በኩል ለግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ የተሰጠው ብድር 484.4 (አራት መቶ ሰማንያ አራት ነጥብ አራት) ቢሊዮን ብር ለግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ ትኩረት አለመሰጠቱን ያሳያል፡፡ በህወሓት ኢህአዴግ የሃያ ሰባት አመታት አገዛዝ የህወሓትኢህአዴግ ቀጥሎም ኦህዴድ ብልፅግና መንግሥታዊ የፓርቲ ልማት ድርጅቶች (State Owned Enterprises) ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው መክፈል ያልቻሉት 780 (ሰባት መቶ ሰማንያ) ቢሊዮን ብር ከንግድ ባንክ ተበድረው አለመክፈላቸው እየታወቀ ከወያኔ ኦዴፓ ብልጽግና መማር አልቻለም እንላለን፡፡ ኦዴፓ ብልጽግና ዓየር በአየር ቢሊዮነር ለመፍጠር በጠፍ ጨረቃ እየፈለገ ይገኛል፣ ፋብሪካ ከፍቶ ሸቀጣ ሸቀጥ አምርቶ፣ እርሻ አርሶ ሰብል አምርቶ፣ የሥራ እድል የሚፈጥር ኢንቨስተር ከሃገራችን ምድር ጠፍቶል፡፡ በዚህም የተነሳ (1) የሃገሪቱ ኢኮኖሚ የመንግሥትና መንግሥታዊ የልማት ድርጅቶቸ የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ እዳ ጨምሮል፣ (2) አመታዊ የእዳ ወለድ የመክፈል አቅም ማጣፍያው ማጠር፣ (3) የመንግሥታዊው ዘርፎች ወጪ ጨምሮል፣ (4) የግብርና ታክስ መሰብስብ ችሎታ ዝቅተኛነት፣ (5) ህዝብ በኑሮ ውድነት መሰቃየት የሸቀጣ ሸቀጦችና ምርቶች የዋጋ ግሽበት  መናርና (6) ሃገሪቱ በኮማንድ ፖስት ወታደራዊ አስተዳደር ወጪና በጦርነት ኢኮኖሚ ኪሳራ ተዘፍቃ ትገኛለች፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ቀውስና የአይኤምኤፍና የዓለም ባንክ ፕራይቬታይዜሽን ሴራ!!!

 

ምንጭ

(1) https://online.fliphtml5.com/qhkn/nmft/ (ቅጽ 23 ቁጥር 1894 / እሑድ ሰኔ 17 ቀን 2010)

ሪፖርተር ጋዜጣ እሁድ ሰኔ 17 ቀን 2010ዓ/ም በዶክተር ኢዮብ ተስፋዬ

(2) መንግሥት ከአገር ውስጥና ከውጭ የተበደረው ውዝፍ የዕዳ መጠን 2.4 ትሪሊዮን ብር ደረሰ/ ሪፖርተር ጋዜጣ / 1 ሴፕቴምበር 2021

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.