ኢትዮጵያዊያን ቅድሚያ ለሀገር ሉአላዊነት መስጠት ግዴታቸው ነው –  ሲና ዘ ሙሴ

ከኢትዮጵ መከላከያ ጎን ነን  !

ሲና ዘ ሙሴ

” ምን እጅ አለኝ ና እጄ እኮ ነው የእሣት ሰደድ
ሺ ባንዳን ፣ ሺ ገንጣይን የሚያነድ ። ”

የትህነግ ጭፍን ፣ ባንዳ ቡድን ፣ በእውነቱ ቅጥረኛ ነው ፡፡ የቀጠሩትም የባሰባቸው አልጠግብ ባዮች እና ስግብግቦች ናቸው ፡፡ የትህነግ / ወያኔ  ፤ በጣት የሚቆጠረው ቡድን ፣ እንደ ቀጣሪዎቹ ሁሉ ፣ እጅግ ጨካኝ ና በቃላት የማይገለፅ ስግብግብነት በህሊናው የሰፈረ ” የጅብ ሆድ ያለው ” ከንቱ ፍጡር ነው ፡፡ መጨበጫ የሌለው  የሸለምጥመጥ ስብስብ ነው ፡፡ አድብቶ አራጅ እና ሰልቃጭ ቡድን ነው ፡፡ ሰው በላ ነው ፡፡ ድህነትን አስፋፊ የግብፅ ተላላኪ ነው ፡፡ እናም ይህንን ሰው ያልሆነ ያበደ የጅብ ስብስብ ቡድን እስከ አስተሳሰቡ  ከኢትዮጵያ ምድር እስካላጠፋነው ጊዜ ድረስ ለፍቶ አዳሪው ፣ በዚች ጊዜያዊ የምድር ድንኳን ውስጥ በእንግድነት በሰላም ከቶም ለመኖር አይችልም ፡፡ እናም  ይህንን ጨካኝ ቡድንያለርህራሄና ያለምህረት  ከማጥፋት ውጪ ሌላ አማራጭ የለም  ።

ይኽ ስግብግብ ቡድን ህሊና ቢስ በመሆኑ የተቀረውን የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ፈሪ የሚቆጥር በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ሙሴ ዘመን ቅጣት ሆ ብሎ ተነስቶ በህዝባዊ ማዕበል  ሊቀጠው ይገባል ። መንግስትም አደባባይ ወጥቶ የአማራን ህዝብ በይፋ ይቅርታ በመጠየቅ ለህዝባዊ ማዕበል ሊሰናዳው ይገባል ፡፡ ባለፈው እና በተቀበረው ቀን ለስልጣን ተብሎ የተደረገው ሸለምጥማጣዊ አካሄድ እጅግ የሚናድድ እና የሚስተዛዝብ ነው ፡፡ በህዝብ ውስጥ ያለውን ታላቅ አእምሮና ጥበብም መናቅ ነው ። የወያኔን ዓይነት ሞት መናፈቅም ነው ፡፡ … በዚህ ረገድ የሰከነ የፖለቲካ ሰው አስተያየት ተደጋግሞ በመሰጠቱ ወሬ ማብዛት አልፈልግም ፡፡ የምስራቁን ሰው የሞገሴን አስተያየት ግን በቅንነት ማዳመጥና ጠቃሚውን መውሰድ የሀገሬፖለቲከኞች የቤት ስራ ቢሆን እመርጣለሁ ፡፡ እነ ተመስገን ደሳለኝማ ዕድሜ ለዋኔ ብር ታፍነዋል ፡፡ ስብሃት እና ቢሊየነሮቹ ከተፈቱ በኋላ ነው እኮ በምሁር ላይ ወከባና አፈና ተባብሶ የቀጠለው ፡፡ ወይ ብር ?  ዛሬስ በብር አገርን ለመሠት የተሰናዳ ባንዳ በመህል አገር የለም እንዴ ? እነዚህ አፋኞች በጦርነቱ ላይ የሚሰሩት ታላቅ ሴራ በእርግጠኝነት አብይን  ከባድ ዋጋ ያስከፍለዋል ፡፡ ይህ እንዳይደርስ በጭብጨባ መዘናጋቱን ያቁም ። ጭብጨባ ተቃውሞም ሊሆን ይችላልና…¡ ሳክስ ይቀነስልን ማለትም ሊሆን ይችላል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሕግ ማስከበር ዘመቻው በሰሜናዊ ክልሎች አወቃቀር ረገድ የፈጠረው ግርታ (ከመርሐጽድቅ መኮንን አባይነህ)

በሳክስ  የወያኔን ጥቂት አውሬ ቡድን ሂትለራዊ  ጭካኔ ማቆም  አይቻልም ።  ከነሱ ጭካኔ በላይ የሚጨክን እንደለ መገንዘብ ካልተቻሉ በሥተቀር በወሬ የሚቆም የሴጣን ድርጊት የለም  ። … እነዚ እብዶች እኮ ፣ ከነሱ ጭካኔ በላይ የሆነ ድርጊት መፈፀም የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚችል በተግባር ካላዩ በስተቀር ጦርነትን ፣ ዘረፋን ና ሂትለራዊ ተግባርን ከቶም አያቆሙም ።  በሃሺሽ እያሥጦዙ  የትግራይን ወጣት እንደ ፍየል በማሯሯጥ በከንቱ መሰዋትነት ለእነሱ ዘበኛ ሆኖ እንዲሞት ማድረጋቸው አያባረም ፡፡  በየቀኑ ቡፌ እየበሉ እና በጥጋብ  እየመረቀኑ ፣ ምርቃናቸውን ለመሥበር ፣ በውስኪ መጨበሳቸው የማይቆመው በጦርነት ውስጥ ሲኖሩ እንጂ በሰላም ውስጥ ሲኖሩ እንዳይደለ አሳምረው ያውቃሉ ፡፡

በዚህ ምክንያት ነው ፣  ኢትዮጵያም  አሥደንጋጭ በትር በወያኔ መሪዎች ላይ ማሳረፍ መቻል አለባት የምለው ። የደብረ ፂዮን እና የመሰሎቹ ሀብት ህንፃና ንብረት ሁሉ መውደም አለበት ፡፡  የጦርነትን አስከፊነት ህዝቡ ተገንዝቦ እንዲረዳ የሚያደርግ ህዝባዊ ማዕበል በአፋርና በአማራ በኩል በአፋጣኝ መደረግ ይኖርበታል ። ከኢትዮጵያ ህዝቡ አንድ አራተኛውን ብቻ በማሰለፍ በእርግጠኝነት እነ ደብረፅዮንና መሰሎቻቸውን  ጠራርጎ ማጥፋት ይቻላል  ።

ህዝቡ እራሱ አታሥጨርሱን ብሎ ፣ እስከዛሬም ያልበላቸው በሚከተሉት ምክንያቶች እንደሆነ የፖለቲካ ተንታኞች መናገራቸውንም አስታውሱ እና ህዝባዊ ማዕበልን ባቸኳይ ፍጠሩ ። 1ኛ .   ” ሥላላወቀ ነው ።  2ኛ . በድንቁርናው ሰበብ ነው ። 3ኛ . በፍርሃት ነው ። 4ኛ . ጠመንጃ ከኋላውቸው ተደቅኖባቸው  ነው ። ” በማለት ። ይኽ እውነት ነው እንዴ ? 1,2,3 አያሥኬዱም ። 4 ኛው ያሥኬዳል ። ላብራራ ፣

1ኛ / የትግራይ ከተሜም ሆነ ገጠሬ  ህዝብ የትህነግ አንድ ለአምሥት ተጠርናፊ በመሆኑ ፣ ድብን አድርጎ የጦርነቱን ዓለማ ያውቃል ።

2ኛ / በድንቁርናው ሰበብ ነው የሚባለውም ሚዛን አይደፋም ። ቄስ ፣ ዲያቆን ፣ ምሁር እና ተማሪ በዚህ ጦርነት ህዝባዊ ማዕበል በመሆኑ የሚሳተፈው ፣ ለአንድ የኢትዮጵያ ወታደር 50 ሰው በማሰለፍ ፣ የሞተው ሞቶ የተቀረው  በሌሎቹ  ወንድሞቹ ከንቱ መሰዋትነት  በወረራው የተቆጣጠረውን ቀበሌ ፣ ወረዳ እየዘረፈ በመብላት ይካሣል ። ገንዘብ በማግኘትም ይበለፅጋል ። ” የሚል  የጅላንፎዎች ምክር እንጂ በድንቁርና ወደ እሣት ዘሎ አልገባም ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ግርማዊነታቸው የአቡነ ጴጥሮስን ሐውልት ሲያቆሙ የተናገሩት

3ኛ ፣ በፍርሃት ነው ። የሚባለውም ተረት ተረት ነው ። እንዴት ጠመንጃ ይዘህ ትፈራለህ ? ለማታምነበትስ ዓላማ እንዴት በከንቱ ትሞታለህ ? ደሞም እኮ ” የትግራይ ሰው ጀግንነት እንጂ ፍርሃትን አያውቃትም ነው ። ” የሚባለው ። ታዲያ ለምን ይሆን እነ ደብረፅዮንን እና መሠል ጨካኝ እና ሥግብግብ  ሂትለሮችን ፈርቶ ወደ ጦርነቱ የተሰማራው ?

4ኛ ጠመንጃ ከጀርባው ተደቅኖበት ነው ። እውነት ከተደቀነበት ይሄ ሰበብ ያሥኬዳል ። ግን ደግሞ ወደ ወታደሩ ሲቃረብ ፣ ጠበመንጃ የያዘውን ተረባርቦ በመያዝ እጁን ለመከላከያ መሥጠት ይችላል ። በዚህ ወቅት ጥቂቶች ሊሰው ይችላሉ ። የበዙት የዋሃን ግን ይተርፋሉ ።

ለማንኛውም አነ ደብረፅዮን መታረጃቸውን ራሳቸው ገዝተዋል ። የመቀበሪያቸውንም ጉድጎድ ራሳቸው ቆፍረዋል ። ዛሬ እንደ በፊቱ እቤቱ ቁጭ ብሎ የሚጠብቃቸው የአማራም ሆነ የአፋር  ገበሬ ና ከተሜ የለም ። ሁሉም ቤቱን ለቆ  በጫካ ና በገደሉ አድፍጦ   ይጠባበቃቸዋል ። ሲጠጉም በህዝባዊ መዓበል ሆ ! ብሎ ለወሬ ነጋሪ ሳያሥቀር ያጠፋቸዋል ። የአማራ እና የአፋር ህዝብ እንደቀድሞው ከቀየው ፣ ከጎጆው ውስጥ ግፍ ሲፈፀም ከቶም አያይም ። እልፍ ሆኖ በመሰዋትነት ድል ለማድረግ ቆርጦ ተነስቶል ። እነ ደብረ ፅዮን ከፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ጦር በሺ እጥፍ የሚበልጥ ጭካኔ እና ነውረኝነት እንዳለቸውም ያውቃል ።

እነሱ ብቻ አይደሉም ተከፋይ ካድሬዎቻቸው እነ “እሥታሊን ና ቴድሮስም ”  በነውረኛነት የተሞላ የጭራቅ ምላሥ ያላቸው የእፉኝት ልጆች ናቸው ። ግብዞች እና ሆድ ብቻ የሆኑ ቀጣፊዎች ። ለመሆኑ ትህነግ የማንን ጦርነት እንደሚዋጋ ያውቃሉ ? የድሮ የመንፈስ አባቶቹን የቅኝ ገዢዎች ጦርነት ነው የሚዋጋው ። ከጀርባው መሳሪያ በመደቀን ፣ የትግራይ ህዝብን የሚፈጀው በባንዳነት ነው ። ይኽንን የጭካኔ ትግባር  ለማውገዝ ይቅርና  ከጦርነት ይልቅ ሠላም ለህዝብ እንደሚበጅ ለመናገር አንደበታቸው አይፈቅድም ። ” መሬታችን ተወሮ ፣ ተከበን ። መፈናፈኛ አጥተን ። ህዝባችን ተርቦ ። ወዘተ ። ”  እያሉ ግን ይጮኻሉ ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ህዝበ-ሙስሊሙን ያለአግባብ በስጋት መፈረጅ፤ ማዋከብና መግደል በአፋጣኝ ይቁም!!

በመሠረቱ ፣ ምድርና ሰማይ የፈጣሪ ናት እንጂ የሰው ልጅ እንደ መኖሪያ ጎጀው የሰራት የግል ፈጠራው አይደለችም እና መሬታችን ብሎ መሞዘዝ ተገቢ አይደለም ። የኢትዮጵያ መሬት ሁሉ የትግራይ ህዝብም መሬት ነው ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ትግሪኛ ተናጋሪዎች እኮ መኖሪያቸው መላ ኢትዮጵያ ነው ።

መፈናፈኛ አጣን ለሚሉት ፤  ህዝቡን መፈናፈኛ ያሳጡት እኮ ራሳቸው ናቸው ። ላከማቹት ሀብት ና ንብረት በእጅጉ በመሥቆንቆን ፣ በሐሰት ትርክትና በጠመንጃ እያሥፈራሩ ፤ እንዲሁም በዕርዳታ ስንዴ በሆዱ ህሊናውን ሸብበውት አይደል እንዴ ህዝቡን የሚጫወቱበት ? ።

ለመሆኑ የትግራይን ህዝብ እያሥራበው ያለው ሂትለሩ ትህነግ በደብረፂዮን ፊትአውራሪነት እና በህሊና ቢሱ ጌታቸው ረዳ አለቅላቂነት አይደለም እንዴ ? በሶሻል ሚዲያ ደግሞ አይኑም ልቡም የታወረው ቴዎድሮስ እና ከጌታቸው ረዳ ባልተናነሰ የሚቀባጥረው እሥታሊን ፣ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰሙ ፣ በእኩይ ፕሮፖጋንዳቸው የህዝብ መራብን እና ሰቆቃን   ከቀን ወደዓመትት ያሳደጉት ? ያባባሱት እነሱ አይደሉ እንዴ ? …

ዛሬም ሥለ ጭራቁ ወያኔ የጦርነት ገድልና ድል በሐሰት መተረካቸውን ቀጥለዋል ። እንደ ከዚህ ቀደሙ  በወሬና በሽብር ግን የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚንበረከከ እንዳልሆነ ይወቁት ። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እነ ደብረፅዮንን ሣያጠፋ ከእንግዲህ አያንቀላፋም ። እወቁ እዚህ በኢትዮጵያ ቤት ያለው የእሳት ሠደድ እናንትን ዘንድ ካለው በሚሊዮን እጅ ይበልጣል ። ከናንተ ጥርግርግ በሎ ማለቅ በኋላ  ደግሞ ወደ ውስጡ የቤት ስራ ጀግናውን መከላከያ ይዞ ይመለሰል ፡፡ በመጀመርያ መቀመጫዬን እንዳለቸው ነው …እናም አላስቀምጥ ፣ አላስኖር ፣ አላስበላ ፣ ወዘተ ብሎ ሁሌም ሞታችንን እየናፈቀ በተላላኪነት ፣ በባንዳነት አገራችንን ለማስበዝበዝ እና ደሃ ሆና እንድትኖር ለማድረግ የግብፅን ጦርነት እየተዋጋ የለውን የትህነግን ቡድን በቅድሚያ ማውደም የሁሉም ኢትዮጵያዊ ቅድሜ ተግባር ነው ፡፡

 

 

3 Comments

  1. መቼም የህወሃትን (የትህነግን) እኩይነት የሚያስተባብል ወይም የሚከላከል ባለ ሚዛናዊ ህሊና የአገሬ ሰው የሚኖር አይመስለኝም። በሌላ አገላለፅ የህወሃት ሥራ መሬት ላይ ተነጥፎ (በተግባር) የሚታይ እውነታ ነውና ብዙም ትንታኔና ማብራሪያ አይጠይቅም።

    ህወሃትን ብቻ አምርሮ የመጥላት ፖለቲካ ግን ከቶ የትም አላደረሰንም። መቸም ቢሆን የትም አያደርሰንም!
    እናም በዚህ ረገድ ያለብንን በስሜትና በንዴት ፈረስ የመክነፍ ፖለቲካ ባህል በመግታት ቆም ብለን ለማሰብና ተገቢውን ለማድረግ በእውን የምንፈልግ ከሆነ ለማሳያነት ብቻ ከዚህ በታች በጥያቄ መልክ የማነሳቸውን ነጥቦች ከምር ልብ ማለት ጥሩ ነው፦

    1) ለተደጋጋሚ የለውጥ ፍለጋ ትግል መጨንገፍ የዳረገን ህወሃትን ራሱ ህወሃት ጠፍጥፎ ከሠራው ሥርዓተ ኢህአዴግ ነጥሎ የማየት በእጅጉ የተንሸዋረረ አመለካከታችን ወይም እምነታችን አይደለም ወይ?

    2)ላለንበት እጅግ አስከፊ ሁኔታ የዳረገን አንዱና ዋነኛው ምክንያት ሥርዓቱን እንደ ሥርዓት ከመፀየፍና ከመታገል ይልቅ በህወሃት ጥላቻ ላይ ብቻ ተተክሎ የቀረው አመለካከታችን አይደለም ወይ? እንዲህ አይነት ጎደሎ የትግል መንገድ አይደለም ወይ አሁን ላለንበት አሳፋሪና አስፈሪ የውድቀት አዙሪት የዳረገን?

    3) የለውጥ ፍለጋው ትግል ህወሃትን ከቤተ መንግሥት አባሮ ህወሃት ሠራሹን ሥርዓት ከነ ሙሉ ቁመናውና አቋሙ በተረኛ የኢህአዴግ አንጃ ቡድን ለመተካት ነበር እንዴ?

    4) ለመሆኑ አራት ዓመታት ሙሉ በከንቱ ለፈሰሰው የአያሌ ንፁሃን ደም ይበልጥ ተጠያቂው የቤተ መንግሥቱ ኦህዴድ መራሽ አንጃ ነው ወይንስ ህወሃት?

    5) አዎ! ህወሃት የግብፅን ፍላጎትና ጣልቃ ገብነትን ቫይረስ ተሸካሚ መሆኑን ለመገንዘብ ብዙም ምርምር አይጠይቅም።
    ከፖለቲካ ሴራና ጣልቃ ገብነት አልፎ በብዙ ኪሎ ሜትር የሚቆጠረውን የኢትዮጵያ የግዛት ልኡላዊነት በሱዳን ገዥዎች ያስደፈረ እውን የብልፅግናው አብይ አህመድ አይደለም እንዴ? ለጎረቤት ደቡብ ሱዳን ስደተኞች የዜግነት መብት ሰጥቶ የኢትዮጵያን ልኡላዊነት አደጋ ላይ እየጣለ ያለ ማነው? “የኢትዮጵያው ሙሴ” አይደለም እንዴ?

    6) በአራት ዓመታት ውስጥ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሲጨፈጨፉ እና በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ደግሞ የቁም ሰቆቃ ሰለባዎች ሲሆኑ እንደ መሪ አዝናለሁ ያለማለቱ የሞራል ዝቅተት አልበቃው ብሎ በሰለባዎች ላይ የፖለቲካ ስላቅ የሚሳለቅ አብይ አህመድ የትክክለኛ ጦርነት (Just war) መሪ የሚሆነው እንዴት ሆኖ ነው?

    7) አራት ዓመታት ሙሉ ለማታላያነት ባሰለጠነው አንደበቱ (ምላሱ) ውሸትን እውነት እያስመሰለ በማቅረብ (በመደስኮር) በመሠረታዊ የህዝብ ግንዛቤ ችሎታ ላይ የሚሳለቅ ፖለቲከኛ በፖለቲካ ወልደው ካሳደጉት የቀድሞ ጌቶቹና የአሁን ተቀናቃኞቹ ምን አይነት መሠረታዊ ልዩነት አለው?

    8) አሁንስ ቢሆን መከረኛውን ህዝብ እርስ በእርሱ የሚያጋድሉት ከአንድ እጅግ ግዙፍ ሰይጣን (ኢህአዴግ) የተገኙና በሥልጣንና ሥልጣን በሚያስገኘው ሽኩቻ ያበዱ ሁለት የሰይጣን አንጃዎች እንጅ አንዱ ቅዱስ ሌላው እርኩስ የፖለቲካ ፍጡራን ናቸው እንዴ?
    ብዙ ፈታኝ ጥያቄዎችን መጠየቅ ይቻላል ። ለማሳያነት ግን ይበቃኛል።

    ለማጠቃለል ፦ ትክክለኛው አገር ማዳን ይበልጥ ቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረት የሚሻውን አገር አፍራሽ ሃይል (አካል) የመዋጋቱ አስፈላጊነት እንደ ተጠበቀ ሆኖ ጎን ለጎን ግን ሁለቱንም አጋንንቶች አስወግዶ በመቃብራቸው ላይ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊት አገርን አምጦ የመውለድ ትግል የግድ አስፈላጊ ነው።
    ከዚህ የወረደ የፖለቲካ ትግል ለዘመናት ከዘለቀውና እርስ በእርሳችን ከሚያባላን (ከሚያጨራርሰን) ክፉ የጎሳና የቋንቋ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ነጋዴዎች ፈፅሞ አይገላግለንም !

  2. ሲና ዘ ሙሴ በፕሪንስፕል ደረጃ ያልከው እዉነት ሊመስል ቢችልም በአመራር ላይ ያሉት ሰዎች ተንኮለኞች ህዝባቸውን በእኩልነት ሳይሆን በጠላትነት የሚመለከቱ ናቸው አካባቢው የጦር ቀጠና መሆኑን እያወቁ ጠላት በከፍተኛ ደረጃ እየታጠቀ መሆኑን እያወቁ እነሱ የተጠመዱት አማራ ሊያንሰራራ ይችላል እንዴት እናድቅቀው በሚለው ሂሳብ ነው አንዴ ትነከሳለህ ሁለቴም ልትነከስ ትችላለህ ከዛ በላይ ሲሆን ግ ን የብሳል፡፡ ብልጽግና ዛሬ ከትህነግ ጄነራሎች በላይ ዘመነ ካሴን ያሳድዳል፡፡ እነ ዘመነ እነሱ አዝረክርከው የሄዱትን መልክ እያስያዙ እዚህ የደረሱ የሃገር የቁርጥ ቀን ልጆች ነበሩ፡፡ ትህነግ በዛ ላይ አይቀርም አዲስ አበባ መግባቱ ግልጽ ነው የዛን ጊዜ በስልጣናቸው ይቆዩ አይቆዩ የሚያዉቁት እነሱ ናቸው፡፡ ዜጋን ከጠላት በላይ እያሰቃዩ እያላገጡ መቀጠላቸው ግ ን አጠራጣሪ ነው፡፡ የአንድ ሃገር መከላከያ እያስጠነቀቀው ገብቶ ሲያተራምሰው ለነሱስ ዉርደት አይሆንም? ከግብጽ ጋር ቢሆን ከሱማሌ ጋር ቢሆን ከኤርትራ ወይም ከጅቡቲም ቢሆን የገጠሙት ምን ሊሆኑ ነው በብልጽግ ና አመራር አገርም ዜጋም አፍሯል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.