የትግራይ ኃይሎች ባወጡት መግለጫ “በጸረ ማጥቃት ዘመቻ” የቆቦን ከተማ መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል

የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከምትገኘው ቆቦ ከተማ ለቅቆ መውጣቱን መንግሥት አስታወቀ።የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት በትናንትናው ዕለት ነሐሴ 21፣ 2014 ዓ.ም እንዳስታወቀው “የህዝብን ፍጅት ለማስወገድ ሲባል” መከላከያ የቆቦ ከተማን መልቀቁን ገልጿል።

 የትግራይ ኃይሎች በበኩላቸው ባወጡት መግለጫ “በጸረ ማጥቃት ዘመቻ” የቆቦን ከተማ መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል። የመንግሥት ኮሚዩኑኬሽን መግለጫ ህወሃት የቆቦ ከተማን ከውጭ “በብዙ አቅጣጫ” እያጠቃ አንደሆነ ገልጾ “የህዝቡን ደህንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል” ብሏል።

በዚህም የተነሳ “መከላከያ የቆቦ ከተማን ለቆ ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚያስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል” ብሏል። የትግራይ ኃይሎች በበኩላቸው ባወጡት መግለጫ” የተከፈተባቸውን ጥቃት ለመከላከል በተደረገ የጸረ ማጥቃት ዘመቻ” የቆቦን ከተማን ጨምሮ ጉጉውዶ፣ ፎኪሳ፣ ዞብል፣ መንደፈራ፣ሮቢት፣ ሽዎች ማርያምና ተኮሎሽ የሚባሉ ስፍራዎችን መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል።

DW

ተጨማሪ ያንብቡ:  በምሥራቅ ወለጋ ዞን የታጠቁ ቡድኖች ባደረሱት ጥቃት የንጹሃን ህይወት አለፈ

3 Comments

 1. ክፋታቸው እንዳለ ሆኖ ወያኔን አለማድነቅ አይቻልም። ተበተኑ፤ ድቄት ሆኑ ገለ መሌ ሲባል ይኸው ለ 3ኛ ጊዜ ልጅም አስከተሉ አሮጌ ሰው ገፍተው ይህንም ያንም እያርበደበድት ይገኛሉ። ሥራቸውን ጀግንነት ማለት አይቻልም። ወንድምና እህቱን ገድሎ የሚፎክር እብድ ነውና። ሲጀመር የትግራይ ህዝብም ሆነ ቀሪው የሃገራችን ክፍል ጦርነትን አይሻም። ግን ወያኔ ከተጠያቂነት ለማምለጥ የግድ ራሱን በጦርነትና በቅስቀሳ ህዝቡን ማዋከብ አለበት። መንግስት ተብዬው አንዴ እየተረፈረፉ ነው ሌላ ጊዜ ህጻናትን አስከትሎ የትግራይን ወጣት እያስፈጀው ነው በማለት ይናገሩ እንጂ ዓለም እንደሆነ ጸጥ እረጭ ብሏል። አለሙ ሁሉ የሚተነፍሰው በተሳሳተው የወያኔ ፕሮፓጋንዳ እየተጠለፈ እንደሆነ ለማየት አይከብድም። ለመጀመሪያ ጊዜ አሁን ወያኔ የዓለም የምግብ ፕሮግራምን ነዳጅ ከዘረፈ ወዲህ ጠንከር ያሉ ቃላቶች በወያኔ ላይ ተሰንዝረዋል። ይህ ግን ውሸት ነው። ያኔ የምግብ ማጓጓዣ ካሚዎኖችን ሲዘርፍና ለጦርነት የሰው ማጓጓዣ ሲያደርጋቸው ምንም ያላሉት አሁን ያስለቀሳቸው የነዳጅ ጉዳይ ለምን ይሆን? ይህ ግን የፓለቲካ የሾኬ ጠለፋ እንጂ ወያኔ ሌባና ገዳይ እንደሆነ ገና በስልጣን ላይ ሳይወጣ በረሃ እያለ ያውቃሉ። ለዚህ ነው ነጩ ዓለም ለትግራይ ህዝብ ወዘተ ይበል እንጂ ደንታ አይሰጠውም የምለው። ሲጀመር የእኛን መገዳደል ማየት ደስ ይላቸዋል። በሶሪያ፤ በሊቢያ፤ በኢራቅ፤ በየመንና በሌሎች ሃገሮች እጃቸውን በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ እያስገቡ ስንቶችን ነው ሃገር አልባ ያረጓቸው? ወያኔን ወይም የአብይን መንግስት የሚደግፉ ሃሎች ሁሉ ሊረዱ የሚገባቸው አንድ ጉዳይ እሳቱንና ጭድን ለሁለቱም የሚያቀብሉት እነዚህ ሃይሎች ከአረብ ሃገሮች ጋር በማበር ነው።
  ጦርነት የኋላ ቀርነት ምልክት ነው። ወያኔም ከጊዜ ወደ ጊዜ በአስተሳሰቡ እንደ ግመል ሽንት የኋሊት መሆኑ እጅግ አሳዛኝ ነው። ስንቱ የትግራይ ልጅ ሞቶና ቆስሎ ነው ትግራይ ለትግራዋይ የሚባለው? ማን ቆሞ ማን ሞቶ? ስለዚህ በውጭና በውስጥ ያሉ የትግራይ ልጆች በወያኔ ላይ ያላቸውን አቋም እውነትን በተመረኮዘ መንገድ ሊፈትሹት ይገባል። ዝም ብሎ በየጊዜው ከወያኔና ከአብይ መንግስት በጠራም ሆነ ከቅንጫቤ እውነት ጋር የሚወረወረውን የሃሰት ፕሮፓጋንዳ አክ እንትፍ ማለት ይመረጣል። በዚህ ግጭት አትራፊ አይኖርም። ምድሪቱን የድኩማን ሃገር ከማድረግ ሌላ። እንዴት ፊደል ቆጥሬአለሁ፤ አቶና ዶ/ር ነኝ የሚሉ ሃበሾች የተሸረበውን ሴራ ማየት ተሳናቸው? አሁን ቆቦ ተያዘ አልተያዘ ምን ፋይዳ አለው? ሲጀመር ወያኔ ቆቦ ድረስ እስኪገባ የሃገር ጦር የተባለው የት ነበር። ሁሌ ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ አይነት ነው። እኔ ሳስበው የአብይ መንግስትና ወታደራዊ አመራሮቹ እንደገና ወያኔ ሽዋ ሮቢት እንዲገባ የሚፈልጉ ነው የሚመስለው። ይገርማል። ሰው እንዴት ካለፈው አይማርም።
  ለወያኔ መሳሪያ ሲያቀብል ተመትቶ ወደቀ ስለተባለው አውሮፕላንም ከቃላቸው በስተቀር አንድም መረጃ የለንም። አንድ አንቲኖቭ 24 ነው ሲል ሌላው 26 ነው ይላል። ዝብርቅርቁ የወጣ ነገር። ግን ይህ ጉዳይ አንድ ነገር አስታወሰኝ። ልንገራችሁ ታገሱ። ወያኔ ከኤርትራ ጋር ባድሜን ሰበብ አርጎ እየተፋለመ እያለ አንድ አውሮፕላን ከመቀሌ ወጣ ባለ ቦታ ላይ መትቶ ይጥልና ተስፈንጥሮ ተንሳፎ የወረደውን ፓይለት ተሸክሞ በመቀሌ ከተማ ሆ ይላል። ሰውየው ጉዳቱ እየተሰማው ኸረ ምን ሆናችኋል እኔ እኮ የኢትዪጵያ አብራሪ ነኝ በማለት መርዶአቸውን ሲነግራቸው ተኩሰው የጣሉት የራሳቸውን አውሮፕላን እንደሆነ አረጋገጡ። ነገሩም በዚያው ተሸፋፍኖ ቀረ። ይህ አንቲኖቭ አውሮፕላን ለኢትዮጵያ የጫነ ቢሆንስ? ሲጀመር ወያኔ ሌሊት ሌሊት መሳሪያ ከውጭ ወደ መቀሌ ያስገባ እንደነበረ የሁመራና የአካባቢው ኗሪዎች ገና በፊት ይናገሩ ነበር። ሰሚ ግን አልነበረም። ግን ይህ ሁሉ የሚያሳየው አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ ነው። የአብይ መንግስት ለትግራይ ህዝብ ሰላም፤ ሰው እርሻ እንዲያርስ እንዲህ እና እንዲያ እያለ ባያማታንስ ምን አለበት? አሁን ለወያኔ የሰው ማረስና አለማረስ ይገደዋል? ያ ቢሆን የእርሻ ጊዜን እየጠበቀ የትግራይ ወጣቶችንና አዛውንቶችን ለዘረፋና ለግድያ ወደ አማራና አፋር ክልል ባላሰማራም ነበር። ግን ከላይ እንዳልኩት ቁርጠኝነታቸውንና የተንኮላቸውን ጥልቀት አለማድነቅ እራስን ማሞኘት ነው። ችግሩ ጊዜና ዘመን የሻረውን የሻገተ አስተሳሰብ መቀየር አለመቻሉ ገና ለዘመናት ያፋጃናል። አኖሌን ያቆመው ወያኔ ለሃገር አንድነት የማይገደው በሰው ደም ዛሬም ወደፊትም የሚቀልድ ነውረኛ ድርጅት ነው። ግን መቼ ይሆን የትግራይ ህዝብ ከወያኔ ነጻ የሚሆነው? ያ ጊዜ ይመጣ ይሆን? አይታየኝም። በቃኝ!

 2. An excellent comment by Tesfa above. I share your agony “ግን መቼ ይሆንየትግራይ ህዝብ ከወያኔ ነጻ የሚሆነው? ያ ጊዜ ይመጣ ይሆን? አይታየኝም” As the idiological-cultural nexus of the Ethiopia concept, if the people of Tigray are not liberated from TPLF and its pseudo-Stalinist (Stalinism modified for neo-colonial end) creed, the rest of Ethiopia will not be liberated.
  In evolutionary biology, there is a concept called selection.
  Sadly, TPLF’s Tigray is like a bacterial colony to which an antibiotic has been applied for a very long time. The antibiotic selects for resistant species. The bacteria that cannot resist the antibiotic all die and strains of bacteria that have resistance gradually multiply and become the entire colony. In Tigray, individuals, families and entire communities that were pro-Ethiopia had been wiped out by the TPLF antibiotic leaving only strains of submissive or TPLF-brainwashed individuals to eventually dominate the Tigrayan colony. This anti-Ethiopian antibiotic TPLF has just been applied in Tigray for too long!

 3. Hi there,

  Unless the federal government sends the army- Amhara militia and Fanno – to Tigray region and control supply lines to TPLF ragtag soldiers already in Amhara and Afar regions, it cannot end the invasion. How can the army -Amhara militia and Fanno – defend Amhara and Afar regions while TPLF is free to recruit, train, equip and mobilize without hiderance in its region? What a military strategy is it to let the enemy free to come and invade without the defense line extended to enemy lines? I think it’s politicians who’re scared of genocide accusations from TPLF that disallowed the army, Amhara militia and Fanno enter Tigray region to cut the supply lines to TPLF. Politicians should let the army to lead and reverse TPLF invasion. The only way to end the invasion is to enter Tigray to cut the TPLF army already in Amhara regions with a quick, selective and continuous military action in Tigray itself. Believe me! Tigray left to itself, there is no possibility to to end the invasion. They have nothing to defend because they are not attacked at home. So, they invade. Even a stupid can see what’s going on. Go to Tigray, guys.

Leave a Reply

Your email address will not be published.