አሸባሪ ትህነግ ዛሬም ሀገር የማፍረስ አጀንዳ አንግቦ ጦርነት እያደረገ መኾኑን የሰሜን ወሎ ዞን አስታወቀ

ወልድያ በጠላት እንደተያዘች የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት መኾኑን ዞኑ አረጋግጧል።

የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋው ባታብል አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ኀይል በዞናችን በድጋሜ ወረራ ለመፈፀም ያለ የሌለ ኀይሉን አሰባስቦ ለሁለተኛ ጊዜ ጦርነት አውጆብናል ብለዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋው ባታብል ዛሬ የሰጡት መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ኀይል በዞናችን በድጋሜ ወረራ ለመፈፀም ያለ የሌለ ኀይሉን አሰባስቦ ለሁለተኛ ጊዜ ጦርነት አውጆብናል።

ከትናንት ስህተቱ የማይማረው የትህነግ ወራሪ ኀይል መንግስት ያቀረበለትን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው ለትግራይ ሕዝብ ግድ የሌለው መኾኑን በተግባር ማረጋገጡን ገልጸዋል።

ጦርነትን እንደ ዋነኛ ግብ ቆጥሮ፣ በሰው ደም ላይ የሚረማመደው የትህነግ አሸባሪ ቡድን፤ ዛሬም ከትናንት ስህተቱ ሳይማር የጦር ነጋሪት ሲጎስም ከከረመ በኋላ ሀገር የማፍረስ አጀንዳ አንግቦ ወደ ጦርነት ገብቷል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በየዘመናቱ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ጠላቶች ሲገጥሟት ኑሯል ። ከጥንት ጀምሮ የገጠማትን የውሰጥና የውጭ ጠላቶችን አሸንፋ በድል እየተረማመደች የመጣች የጥቁር አፍሪካ ሕዝቦች የነፃነት ፈርጥ መሆኗን የታሪክ ድርሳናት አስረግጠው ይመሰክራሉ።

ወራሪው የትግራይ ኃይል በመንግስት በኩል የቀረበለትን የሰላም አማራጭ አልቀበልም ብሎ ጦርነትን አማራጭ ያደረገው ለትግራይ ሕዝብ አስቦ ሳይሆን የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት፣ የባንዳነት ተልዕኮውን ለማስፈፀም አበክሮ እየሠራ ስለመኾኑ አንዱ ማሳያ ነው።

ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ሉአላዊነትና አንድነት ላይ የማይደራደሩ፣ በደምና በአጥንታቸው አፅንተው ያቆሟትና ሀገር የመሠረቱ ያፀኑ የእንቁ ልጆች ባለቤት ናት ። ዛሬም ቢኾን ከዚህ ከፍታዋና ክብሯ ማንም ዝቅ ሊያደርጋት አይችልም።

የሀገራችን ትናንት በደምና በአጥንት ያቆሟት ጀግኖች ልጆች እንደነበሯት ሁሉ፤ ዛሬም የሀገራቸውን ሉአላዊነትና አንድነት በደምና በአጥንታቸው የሚያፀኑ ጀግኖች ልጆች አሏት።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ "አዲሱ አበባ ቆራጭ" ሆኑ

ወራሪው ኀይል በዞናችን ወረራ ሲፈፀም ትናንት ይጠቀምባቸው የነበሩ የሀሰት ቅስቀሳና ፕሮፖጋንዳዎች አሁንም ተጠናክሮ ሕዝብን ለማደናገር በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።

ይህ የሽብር ቡዱኑ ፕሮፖጋንዳ በማህበራዊ ሚዲያ ተከፋይ አክቲቪስቶች ብቻ የሚተገበር ሳይሆን የፈጠራ ወሬዎችን በሚያራግቡ እና የጠላት ፕሮፖጋንዳ ከውሰጥ ሁነው በሚደግፉ ስዎች ጭምር የሚተገበር በመኾኑ ዛሬም እንደለመደው ወልድያን ተቆጣጠርኩ እያለ ያራግባል ።

ስለዚህ ኅብረተሰቡ ከእንደዚህ ዓይነት የሀሰተኛ መረጃዎች ራሱን ሊጠብቅና አጠራጣሪ መረጃዎችን ሲመለከት ለመንግስት የፀጥታ መዋቅር ጥቆማ መስጠት ይጠበቅበታል።

የዞናችን ሕዝብ በወራሪው ኃይል የደረሰበት የሰብዓዊ፣ ስነ ልበናዊና ቁሳዊ ውድመት መንገር ለቀባሪ እንደማርዳት ይቆጠራ፤ የችግሩ ቀጥተኛ ተጠቂና ገፈት ቀማሽ ነው።

ሰለሆነም ወራሪው ኃይል እንደ ሀገር ወረራ ሲፈፀም ዞናችን ቀጥተኛ የትግሉ ቦታ ላይ የሚገኝ በመኾኑ ፤ ከትናንት ችግሮች ትምሕርት በመውሰድ ያለ የሌለ አቅማችንን አሟጠን ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከአማራ ልዩ ኀይልና ፋኖ ጋር ደጀን በመኾን አጋርነታችንን እንደ ወትሮው አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል።

ሰላማችን የሚረጋገጠው በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይደለም። መንግስት ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነትና አማራጭ አሟጦ ተጠቅሟል። ለሰላም ሲባል ረጅም ርቀት በመንግስት በኩል የተወሰዱ አዎንታዊ እርምጃዎች የሚደነቁ ናቸው። ያም ሆኖ በጠላት የቀረበለትን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን ብሎ ጦርነትን እንደ ብቸኛ አማራጭ ተጠቅሞ ዳግም ወረራ ከፍቷል።

ሰለሆነም የዞናችን ሕዝብ የተቃጣብንን ወረራ የኀልውና ጉዳይ በመሆኑ አያጠያይቅም። ትናንት ብዙ ትምህርት ወሰደናል፤ ዛሬ ለነፃነታችንና ለአንድነታችን ዘብ መቆም ይጠበቅብናል።

ነሐሴ 24/2014 ዓ.ም

ወልድያ/ APP

 

5 Comments

  1. አይ ፊልድ ማርሻል እንደው ነገሩ ሁሉ ቀልድ ሆነ ማለት ነው? አብይ ከዛ ይቀዳል ጁላ ዱቄት አድርጊያለው ይላል ባጫ አቡክተን ጋግረነዋል ይላል ሌላው ዱቄት አድርገነዋል ይላል፡፡ ዱቄት የሆንነው እኛ ነን ሁሉም ትያትር ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሰው እስክታገኝ ትያትሩ ይቀጥላል፡፡ ነብስ ያጠፋ አገር የዘረፈ ታሪክ ያጠፋ ወንጀለኛው ስብሃት ነጋ ከእስር ተስተናግዶ በክብር ሲቀመጥ በረከት ስሞን በከፍተኛ ክብር ሲያዝ ክቡር አቶ ታዲዮስ ታንቱና ተመስገን ደሳለኝ በእስር ይማቀቃሉ ይህ ነው የብልጽና ኢትዮጵያ፡፡

  2. How could the tplf – the powder scattered in the air manage to achieve all these victories against innocent citizens? Where is the Ethiopian Defence force? Where is the field marshal? where is the prime massacre head?

  3. Folks,

    Unless the federal government sends the army- Amhara militia and Fanno – to Tigray region and control supply lines to TPLF ragtag soldiers already in Amhara and Afar regions, it cannot end the invasion. How can the army -Amhara militia and Fanno – defend Amhara and Afar regions while TPLF is free to recruit, train, equip and mobilize without hiderance in its region? What a military strategy is it to let the enemy free to come and invade without the defense line extended to enemy lines? I think it’s politicians who’re scared of genocide accusations from TPLF that disallowed the army, Amhara militia and Fanno enter Tigray region to cut the supply lines to TPLF. Politicians should let the army to lead and reverse TPLF invasion. The only way to end the invasion is to enter Tigray to cut the TPLF army already in Amhara regions with a quick, selective and continuous military action in Tigray itself. Believe me! Tigray left to itself, there is no possibility to to end the invasion. They have nothing to defend because they are not attacked at home. So, they invade. Even a stupid can see what’s going on. Go to Tigray, guys.

  4. የአገሬ ህዝብ በቅጡ የሚያነቃው ፣ የሚያደራጀውና የሚመራው የነፃነትና የፍትህ ሃይል (ድርጅት) ለማግኘት ቢታደል ኖሮ በዴሞክራሲያዊ የአርበኝነት ትግል ወደ መቃብር መሸኘት የነበረበት የአንድ እኩይ ሥርዓት ውላጆች የሆናችሁትን (እናንተንና ህወሃትን) ነበር። አዎ! አልሆነለትም እንጅ ቢሳካለት ኖሮ የአንድ እኩይ ሥርዓት (ኢህአዴግ) አንጃዎች ወይም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች የሆናችሁትን (ህወሃትን እና ኦህዴድ/ብልፅግናን) ከዙፋናችሁ ጠራርጎ ማስወገድና እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን ማድረግ ነበር ፍቱኑ የፖለቲካ ወለድ ደዌ መድሃኔት! አዎ! ሀወሃትን አሸባሪ፣ ጦርነት ናፋቂ፣ ገዳይ፣ አስገዳይ፣ ጁንታ፣ አገር አፍራሽ የሆነ ሃይል መሆኑ ግልፅ የሆነው እኮ ገና እናንተን ሳይፈጥራችሁና ለእኩይ ተልእኮው ሳያሰማራችሁ ነበር።

    አሁን እናንተ የምትነግሩን የእኩይ ተግባር መገለጫ ቅፅል ስሞች ሁሉ ድሮም የእርሱው ታማኝ አገላጋይ ሆናችሁም ሆነ በዚህ በሁለት አንጃ ተከፍላችሁ አገርን ምድረ ሶኦል እያደረጋችሁ ባላችሁበት ወቅትም የምትጋሩት እንጅ የምትለያዩበት አይደለም።
    ለመሆኑ ህወሃትን ብቻ “ደም የጠማው” ስትሉ እናንተ ለሩብ መቶ ክፍለ ዘመን በህወሃት አሽከርነት ሥር እና በዚህ ለውጥ እያላችሁ በምትቀልዱበት አራት ዓመት ውስጥ ምን ያህል የንፁሃን ደም እንደጎርፍ ፈሰሰ ትክዱ ይሆን? ምን ያህል ቁጥር ያለው ማህበረሰብ ነው ለምድረ ሲኦል የተዳረገ? ስንት እናቶች ማህፀናቸው በስለት ተዘነጠለ?
    ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት እጅግ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ስንት መዝናኛ ሠራችሁ? ስንት ችግኝ ተከላችሁ? “ለሙታን ጥላነት” የሚውል ስንት ልዩ ችግኝ ተከላችሁ? ስንት “በዳቦ የሚበላ ሙዝ” አለማችሁ? በአገር ታሪክ የመጀመሪያ የሚባል የመከላከያ ሃይል ገንብተናል የመትሉት እንዲህ የምታጣጥሉትን (የምትንቁትን) ህዋሃትን ለማጥቃት ባይችል እንኳ እንዴት መከላከል አቃተው?

    አሽከርነትን ያልተፀየፈ የብአዴን ስብስብ በየትኛው የፖለቲካና የሞራል ልእልና ነው ከህወሃት የተሻለ ሥርዓት እየገነባ ያለው?

    አገር ጠባቂውንና ገንቢውን ንፁህ ወገን ድራሹን እያጠፉ ህወሃት ወረረህ፣ ዘረፈህ፣ አሸበረህ፣ አገር አሳጣህ ፣ወዘተ ማለት የቀጣፊዎች ካልሆነ በስተቀር ምን የሚሉት የፖለቲካ ጨዋታ ነው?

    ህወሃት/ኢህአዴግ የመሠረተው ሥርዓት እንደ ሥርዓት እስከ ቀጠለ ድረስ ጦርነት ኖረም አልኖረም የሰላምና የእድገት ነገር ጨርሶ አይታሰብም። እናም የሚያዋጣው ሁለቱም ይህን ጦርነት እንዲያቆሙና ሁሉን አቀፍ የሆነ እውነተኛ የለውጥ ምክክር ሳይውልና ሳያድር እንዲጀመር የማያወላዳ ትግልን መቀጠል ብቻ ነው። ከዚህ ያነሰ ትግል እያወቁ ማለቅ ነው የሚሆነው።

  5. ወገናችን የሰሜን ወሎ ህዝብ አይዞን ይቺም ቀን ታልፋለች: የህውሀት ፕሮፓጋንዳ በዚህኛው ዘመቻ በጣም ቀሼ ስራ ድለሆነ ማንንም አልገዛም እውነተኛ መረጃዎችም በቶሎ ስለምትለቁ እውነት እያሸነፈች ነው::ውጪ ያለነውም ለገበሬው ፋኖ የሚደርስ ገንዘብ እያዋጣን ነው በአካል ባንሳተፍም በፀሎትና በገንዘብ እንረዳለን በርቱ:: ጦርነቱን የጀመረው ህውህት ስለሆነ ውጊያውም ትግራይ ቢሆን ፍትሀዊ ነው:: በቅርብ ቀን ይህም ይቻላል ኢትዮጵያችን ታሸንፋለች

Leave a Reply

Your email address will not be published.