የከንቲባው ፍጻሜ…!! (ከመምር ዘመድኩን በቀለ የቴሌግራም ገጽ የተወሰደ)

አማራ ነፃ መውጣት ሊጀምር ነው፡፡ አማራው ለኅልውናው ሲል በብአዴን ስም እላዩ ላይ ተጭነው የሚያላግጡበትንና እነሱም ጌታቸው ኦነግ/ኦህዲድም እየፈጁት የሚገኙትን በቁማቸው የሞቱ ፀረ አማራ አማራ ተብዎችን በዚህ መልክ ማስወገዱን ከቀጠለ በቅርብ ጊዜ ውስጥ አማራ ራሱንም ኢትዮጵያንም ነፃ እንደሚያወጣ ቅንጣት መጠራጠር አይገባም፡፡ “ጠላትማ ምንጊዜም ጠላት ነው፤ አስቀድሞ መግደል አሾክሹዋኪውን ነው” እያለ የሚፎክር ሕዝብ በውስጡ መሽገው እየገደሉትና እያስገደሉት የሚገኙትን ባንዳዎች ካላስወገደ ዕድሜ ልኩን እያለቀሰ ይኖራልና ይህ ነገር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ እነሱ አማራን ለመጨረስ የሚያደርጉት ግፍና በደል እንደጽድቅ ከተቆጠረ ራስን ከጥፋትና ውድመት መከላል ኩነኔ ሊሆን አይገባም፡፡ ከዚህ በታች ያለውን የዘመዴን ወቅታዊ ዘገባ እንከታተል፡፡

  • ቆይቼየአስተያየትመስጫውን ሰንዱቅ እከፍትላችኋለሁ። እስከዚያው እያነበባችሁ ቆዩኝ።

“…በሰሜን ሸዋ በሸዋሮቢት ከተማ በትናንትናው ምሽት የከተማዋ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው ባልታወቁ ሰዎች ተመተው መገደላቸው ይታወሳል። ከአቶ ውብሸት በተጨማሪ የአቶ ውብሸት ባለቤትም  ተመቱ ሲሆን ነገር ግን ለከፍተኛ ህክምና ወደ ደብረብርሃን ይሁን ወደ አዲስ አበባ ለጊዜው ወዳልታወቀ ሥፍራ ለህክምና መላካቸው እንጂ እስከአሁን የሞታቸው ዜና አልተሰማም።

“…የሸዋሮቢት ከተማ የተለየያዩ ከንቲባዎችን አስተናግዳ ታውቃለች። ከአቶ ውብሸት በፊት አቶ ቴዎድሮስ እና ወሮ ሉባባ የሚባሉ ሁለት ከንቲባዎችም ተሾመው ነበሩ። አቶ ቴዎድሮስ በፋኖዎች የፌስቡክ  ፅ ውስጥ ገብተው በኮመንት መስጫ ሳጥኑ ላይ ” አንድ ሞርታር ይዞ መጎረር አይከብድም?” ብለው አስተያየት ከሰጡ በኋላ በደረሰባቸው ውግዘት ተደናግጠው ሥልጣን ለቀው አሁን ሰላማዊ ሰው ሆነው ብስክሌት እየነዱ በሰላም መኖር ከጀመሩ ሰነባብተዋል ነው የሚባለው። ወሮ ሉባባም በሁሉ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩና በእድገት ወደ ዞን ያደጉ ሴት ከንቲባ ነበሩም ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች። ቀጥሎ የመጡት አቶ ውብሸት ነበሩ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እቺ ወፍ ዘቅዝቃ ነፋች - የአስናቀ ይርጉ ተንኮል ቀስቶ ነኝ (ከባህር ዳር)

“…አቶ ውብሸት የተረከቡት የሸዋሮቢት ከተማ ህዝብ በጁንታው የደቀቀ፣ በኦነግ ሴቶቹ የተደፈሩባት፣ ንብረት የተዘረፈባት፣ ዕልፍ ጀግኖች የወደቁባት፣ በአጠቃላይ የኢኮኖሚዋም፣ የሥነ ልቦናም ድቀት የ ጠማት፣ ሆደባሻ ከተማን ነበር። ለዚህ በዘርፈ ብዙ ሀዘን ለተመታ ከተማ ህዝብ ደግሞ የሚያስፈልገው የሚያጽናና፣ የሚያበረታታ፣ ለሥራ የሚያፋጥን፣ የሥነ ልቦና ህክምና የሚሰጥ ሰው ነበር መመደብ የነበረበት።

“…መንዝን በቤተሰብ የሚያስተዳድረው አቶ ግርማ የጅብጥላ ግን ይሄን ትእቢተኛ ሰው መደበ። ህዝቡን ሰብስቦ የሚደነፋበት፣ አሳይሃለሁ፣ እቆርጥሃለሁ፣ እፈልጥሃለሁ እያለ እንደ ከንቲባ ሳይሆን እንደ ጀነራል የሚያደርገው፣ ከወፈሩ አይፈሩ ሆኖ ጮማው አዕምሮውን ደፍኖበት በጦርነቱ የሞቱ የፋኖና የሚሊሻ ቤተሰቦች ላይ ሳይቀር እንደግርማ የጅብጥላ ሲያቅራራ ከረመ ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች።

“…ከዚህም አልፎ ዐቢይን ተሳደባችሁ ብሎ የሸዋ ሮቢትን ወጣቶች በጅምላ ፈጃቸው። በቅርቡም ሁለት ወጣቶችን አስገደለ። ግርማ የሺጥላ ለዚህ ጀብዱ ቪ8 መደበለት። በዐማራ ልዩ ኃይልም እንዲጠበቅ ተደረገ። በቃ ሚጢጢዬ አምባገነን ሆነ። ትናንት ምሽት ግን ውብሸት ባልታወቁ ሰዎች ተገደለ። አብረውት የነበሩትና ግርማ የሺጥላ የመደበለት የዐማራ ልዩ ኃይል አባላት ፖሊሶችም ጥለውት ሸሹ። አላዳኑትምም። አልተከላከሉለትምም። ሚስቱም ተመታች። ቨ8ቱም ቀረ። የግርማ የጂብጥላም ሞራል አብሮ ደቀቀ። ዐማራን ለማዋረድ ይደክም የነበረው አንደበትም ተዘጋ።

“…ከንቲባው ባለፈው የሸዋሮቢት ወጣቶችን ከረሸነ፣ ካስረሸነ በኋላ የሟች ቤተሰቦች ሀዘን እንዳይቀመጡ አስደረገ። ከለከለ። ሁሉም አዘኑበት። ለዚህ ተግባሩም የመንዙ ግርማ የጅብጥላ ጀግና ብሎ ጠራ። አሞካሸውም። ዛሬ በከንቲባ ውብሸት መኖሪያ ቤት ለቅሶ የሚደርሰው አንድም ሰው ጠፋ። ወዳጄ የሸዋ ህዝብ አይጥላህ። እንዲያውም በከንቲባው ሞት የተነሣ ግርማ የጂብጥላ ጦር ይልካል ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም ከተማዋ የተለመደ ሰላማዊ እንቅስቃሴዋን ቀጥላለች። ቀጣዩ ከንቲባም ከውብሸት ትምህርት የወሰደ እንደሚሆን ይታመናል ይላሉ ሸዋሮቢቶች።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሃገራችንን በዲፕሎማሲው መስክ ዋጋ እያስከፈሏት ያሉ የኢህኣዴግ ጭንጋፍ ኣስተሳሰቦች

“…አሁን ከዘመነ ህወሓት ጀምሮ 30 ዓመት ሙሉ ብአዴን ሆነው ዐማራ ህዝብ ላይ ያላገጡ ነውረኞች ደንግጠዋል ይላሉ። አያ ግርማ የጂብጥላም ጠባቂ ቁጥር ይጨመርልኝ ብሏልም ተብሏል። በጠባቂ ብዛት ግን አይዳንም። ቤተሰቡ ያለቀበት፣ የታሠረበት ዐማራ፣ የዐማራ ፋኖ ከሸዋሮቢት ትምህርት የወሰደም ይመስላል። ሃዘን ከገባ አይቀር ብአዴኖች ቤትም ይግባ እንጂ ያሉም ይመስላሉ። አባቱ የተገደለበት፣ ወንድሙ የተገደለበት፣ የታሰረበት ሁላ በቀጣይ ወደ ምሥራቅ ወደ ሸዋሮቢት መመልከቱም አይቀርም። ጎን ለጎን ኦነግም አስወግዶት ቢሆንስ የሚሉም አሉ።

“…የሆነው ይሄ ነው…!! የሞቱትን የዐማራ ወጣቶች ግን ነፍሳቸውን ይማር። በቀጣይ እንዲሁ ዘገባ ሲኖር አቀርብላችኋለሁ።

#ማሳሰቢያ፦ ከእንግዲህ ወዲህ በፔጄ ላይ እገሌ ታሰረ፣ እገሌ ታፈነ ብዬ የማልዘግብ መሆኔ ይታወቅልኝ። እንደበግ መነዳት ዜና አይሆንም። ውሻው ሰውዬውን መንከሱ ዜና አይሆንም። የተለመደ ነ ። ዜና የሚሆነው ሰውዬው ውሻውን የነከሰ እንደሆን ነው።

“… ጠብቁኝ ቆይቼ እመለሳለሁ…!!

2 Comments

  1. Those who had been pushing the Amhara to extremism should start rejoicing; sparks are starting to be seen here and there. When the overly patient Amhara have been brought to the brinks of radicalism, our mutual annihilation as Ethiopians is guaranteed. Internal and external enemies of Ethiopia should be elated at this prospect for they have worked on overdrive to see this moment.

  2. እውነት ለመናገር ከንቲባው የጦርነት ቀጠና ሹመኛ አይመስልም፡፡ አቶ አገኘሁ ተሻገር ምነው በጨረር እንደተመታ ደርቀው ቀሩ? ስጋት ነው ወይስ መጠጥ? ሽጉጤን ጠጥቼ እሞታለው የሚሉት ቀልድ አላቸው ረስተው ልሞክረው እንዳይሉ ስጋት አድሮብናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.