ከዘመነ ዕኩይ ወደ ዘመነ ሠናይ ያድርሰን !

ያለፉትን አራት ዓመታት የመራውን ግለሰብ አብይ አህመድን ብንመለከት በሕዝብና በአገር ስም የሚሰጠውንም ሆነ በብድርና በእርዳታ የሚገኘውን ገንዘብ እንደ ግል ሃብቱ ሲበትን፣ለምን  እንዲህ ይሆናል ብለው የጠዬቁትን ምን አገባችሁ እያለ ሲሳደብና ሲያንጓጥጥ ማዬቱ የተለመደ ነው

ያለፉት የሶስት አስርተ ዓመታት  የመከራ እና የጥልመት ግሳግሶች እና ኮተቶች ተጠራርገዉ ይዉደሙ ፡፡ ኢትዮጵያን የደም ፤ የአጥንት እና የህይወት ዋጋ ከፍለዉ አሁን ላይ በነጻነት የነፃነት ህይወት መኖር በምንችልባት አገር ላይ አሳዳጂ እና ተሳዳጂ ፣ባለቤት እና መፃተኛ  ህዝብ ፣ በማንነት ላይ መኃልቁን የጠላ  የበታችነት ስሜት በወለደዉ ጥላቻ ከፍተኛ ሠባዊ እና ቁሳዊ በደል ደርሷል፡፡

ለዚህ ሁሉ የመከራ ገፈት ቀማሽ የሆነዉ ኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያ ያስተናገደዉ እና የሚያስተናግደዉ  የመከራዉ ዙር ሞልቶ የተረፈዉ ህዝበ -ዓማራ በማይካተትበት እና ባልተሳተፈበት  ዕንቅፋት፣ ጉድጓድ እና ወጥምድ  ምክነያት ነበር ፤ ነዉ ፡፡

በቀዳሚዉ ትህነግ እና ተባባሪዎች  በተቀዳሚ ኢህአዴግ  ተሸርቦ የተገመደዉ የአገር እና የህዝብ ወጥመድ ምንጭ እና መሰረት የኢትዮጵያ አንድነት እና ቀዳሚ ገናናነት ታሪክ የሚያቀረሻቸዉ ፀረ -ኢትዮጵያዉያን በኢትዮጵያ እና ህዝቧ ላይ ብቸኛ አዘዥ ናዛዥ ሆነዉ እንዲደላደሉ ያደረጋቸዉ ታሪካዊ ጠላቶች የቆፈሩት የክህደት እና ሞት ወጥመድ  በህገ.ኢህአዴግ ይጥላቻ እና መድሎ መጋራጃ የተከረቸመዉ እና ብዙሀኑን ያገለለዉ ይህ ህገ-ኢህአዴግ ጥቁር መጋረጃ አስካልተወገደ የኢትዮጵያም ሆነ ህለዉናዉ እና ባላአገርነቱ የተካደዉ እና የተገፋዉ ህዝበ ዓማራ  ትንሳዔ እና ህልዉና ዕዉን ይሆናል ብሎ ማሰብ ከንቱ  ምኞት እና የጭለማ ሩጫ ነዉ ፡፡

የኢትዮጵያን እና የህዝቧን መፃኢ ህልዉና፣ ነጻነት ፣ ሠላም ፣ ዕድገት እና አንድነት መመኘት ጠላት ዲያብሎስም እንደመላክ የሚያስተጋባዉ መሆኑ ታዉቆ ኢትዮጵያ እንደ አገር ወደ ቀደመ የከብር ማማዋ እንድትወጣ እንዲሁም ህዝቧ በገዛ ዘገራቻ ከባርነት ፣ስደት እና ድህነት  ቀንበር ይላቀቁ ዘንድ የአንድነት እና ዕድገት ዕንቅፋት፣ ጉድጓድ እና ወጥመድ በመሆን የጥላቻ እና ማግለል መድብል የሆነዉ ህገ- ኢህአዴግ የሠላሳዓመት የጥልመት እና ሞት  የጥፋት፣ ዉድቀት እና ሞት ግሳግሱን ይዞ  ወደ አዲሱ ዘመን -ዘመነ  ሉቃስ እንዳይተላለፍ ይህ የፀረ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉን መደበቂያ እና መመፃደቂያ  የጥፋት ፣ጥልመት፣ ስደት እና ሞት  ምሽግ “ጉድጓድ እና ወጥመድ  ”  ከነከፋፋይ ግድግዳዉ ይናድ፣ ይንደድ ልሳኑ ይዘጋ  የጥልመት ዓመታት ፍፃሜ ወደ መጪዉ አዲስ ዘመን ላይደርስ  የጥላቻ እና ሞት  መጋረጃ እና ግንብ ይገርሰስ ፤ይፍረስ   ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰሞንኛው ደሴን በጨረፍታ

መጪዉ ዘመነ -ሉቃስ  ዕዉነተኛ እና ዘላቂ ህልዉና ፣ ነፃነት  እና አንድነት  ይረጋገጥ ዘንድ ብቸኛዉ መንገድ  በአንድነት እና ህብረት የሚነሳ ክንድ እና ህገ -ኢትዮጵያ (ኢትዮጵያዉያን) ወይም ህገ -ህዝብ እንዲሰፍን አሮጌዉን  ወጥመድ እና ጉድጓድ  መቆረጥ እና መደምሰስ ይኖርበታል ፡፡

መጪዉ አዲስ ዓመት ከዘመነ ስቃይ እና ዕኩይ ወደ ዘመነ ሠናይ የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን  የጤና ፣ የነፃነት ፣የሠላም ፣ የዕድገት እና አንድነት  ዘመን ይሆን ዘንድ  መድኃኒት ዓለም እየሱስ ክርስቶስ ቸርነቱ እና ጥበቃዉ ኩላችን ጋር ይሁን ፡፡

 

“አንድነት ኃይል ነዉ ፤ ኃይልም የዕዉነተኛ ህልዉና እና ነፃነት መንገድ ነዉ ”

 

NEILOSS –Amber

Leave a Reply

Your email address will not be published.