ይድረስ ለአገሬ ሕዝቦችና መሪዎች፣ የቋንቋና የእምነት ቅራኔ፣ – ከጆቢር ሔይኢ

09/13/2022

በአሁኑ ጊዜ ሕዝባችንን እርስ በርስ እያነካከስ ያለው፣ የቋንቋና የሃይማኖት ጭቆና ዱሮም ነበር፣ ዛሬም አለ፣ገና አልተወገደም።ቀድሞ ክርስቲያኖች ወንግሌን በዓለም ላይ ለማሰራጨት ሲሉ ነበር ወደ ቅኝ ግዛት የተሸጋገሩት። ስለሆነም የብሔሮች በቋንቋቸው ራስን በራስ የማስተዳደር መብት፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር የጸደቀ፣ብዙዎች ከቅኝ አገዛዝ ቀንበር ነፃ የወጡበት መርህ ነው። በአገራችንም ጀብሓ፣ ሻቢያ፣ ሕወሐት፣ ኦነግና መሰል የብሔር ድርጅቶች የተመሠረቱት፣ ብሔራቸውን ከቋንቋና ከሃይማኖት ጭቆና ነፃ ለማውጣት ነበር።

ይህም በአገራችን የተቀጣጠለው የቋንቋና የሃይማኖት ነፃነት ትግል፣በተለይ በሊቢያ፣ በግብፅ፣ በሱዳን፣ በሱማሊያና በአረብ አገሮች ይደገፍ ነበር።ስለሆነም ቅራኔው ከእስራኤና ከፊልስጢኤም ጦርነት ጋር ተያይዞ፣ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ከአዲስ አበባ ወደ ማስነሳት በመቃረቡ መንግሥታችን ሰግቶ፣ ከእሥራኤል ጋር የነበረውን ዲፖሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጧል።አስመራ የነበረውንም የአሜሪካን ጦር ሰፈር ዘግቷል። ሰለሆነም አገራችን ከምዕራቡም ከምሥራቁም ሳትሆን ቀርታ፣ በመካከሉ ስታወላውል ነበር የቆየችው፣ክዚህም የተነሳ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ደጋፍና ተባባሪ አጥታ፣በትረ ሥልጣኗን ለወታደራዊ መንግሥት ለማስረከብ የተገደደችው፡፡

ወታደራዊ መንግሥትም ሥልጣን እንደ ያዘ፣ ከነፃነት ተዋጊዎች ጋር ለመታረቅ ፈልጎ፣ጄንራል አማን አምዶምን ወደ አስመራ ልኮ፣ከሸብያና ጀብሓ ጋር ተደራድሮ ነበር። ከድርድሩም አንዱ የኤርትራ ተማሪዎች ከፍተኛ ነጥብ እያለቸው በአማርኛ ፈተና እየወደቁ፣ ዩንቨርሲቲ መግባት አልቻሉምና አማርኛ የግዴታ ትምህርት መሆኑ ይቅር የሚል ነበር።ይህ ጥያቄ የደርግ አባላትን በማበሳጨቱ፣ በእኛ ዘመነ መንግሥት፣ አማርኛ ቋንቋ የግዴታ ትምህርት መሆኑ አይቀርምበማለት ተቆጥተተው፣ ጄኔራሉንና ስድሳዎቹን ባለሥልጣኖች በመረሸን ድርድሩን አከሸፉት፡፡ ይህም የብሔር ቄራኔውን አባብሶ ለአስራ ሰባት አመት ለእርስ በርስ ጦርነት ዳረገን፣ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የዜግችን መስዋዕትነት አስከፈለን።ብመጨረሻም ኤርትራንም የባህር በሩንም አሳጣን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ ፀሐይ ያጠላው ጥቁር ደመና ቹቹ አለባቸው (ከፍትሕ መጽሔት)

ይህ ቅራኔ ነበር ኢሕአዴግን ለመንግሥት ሥልጣን ያበቃው፣ዛሬም ያልተፈታውና እርስ በርስ እያገዳደለን ያለው ይኸው የብሔር ሥልጣን ጥያቄ ነው።ይህም ዓለም ያወቀው ገሃድ እውነት ነው። ይህን ሀቅ በመካድ የቅራኔው ምንጭ ሕገ መንግሥት ነው የሚሉ አሉ።እነርሱም እውነት አላቸው፣የሚከራከሩት ለቋንቋቸው፣ ለእምነታቸውና ለብሔራቸው የመብት የበላይነት ነው። ስለሆነም ነው ትግላችንን የተወሳሰበ መፍትሔ አጥቶ የቆየው።

አሁንም ቢሆን በመንግሥት ሥልጣንና በወታደራዊ ኃይል በመመካት፣በጊዜያዊ ድል በመርካት፣የደርግና የኢሕአዴን ስህተትን ከመድገም መጠንቀቅ ይገባናል።እስከ አሁንም በግራውም ሆነ በቅኝ ብዙ ስህተቶች ተፈጽመዋል።በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የዜግች ደም በከንቱ ፈሷል፣አጥንት ተከስክሷል።ሃብትና ንብረት ተደምስሷል።ቅዱሳት ቦታዎች ረክሰዋል፣ እናቶች አፍረዋል። ጥላቻና ትእቢት ነግሶአል።

ይህም ለመንግሥት ሥልጣን፣ለመሬት ወረራ፣ለቋንቋና ለእምነት የበላይነት፣ በግልፅና በስውር እይተካሔደ ያለው ጦርነት፣በውስጥም ሆነ በውጭ ብዙ ደጋፊና ተቃዋሚዎችም አሉት፡፡ስለሆነም ይህ ጦርነት ፈጥኖ ካልተግታ፣የውጭ ጣልቃገብነትን ሊጋብዝ፣ የኢኮኖሚ ማዕቀብንም ሊያስከትል፣ ሕዝባችንንም ይበልጥ ከፋፍሎ፣ በመንግሥት ላይ ሊያስነሳ ይችላል፣በውስጥ የተሰገሰጉ፣በውጭም የተከማቹ፣ የጦርነት አራጋቢዎችም ፍላጎትም ይኸው ነው።

ስለሆነም የፌድራል መንግሥቱ ለሕገ መንግሥቱ የቅድሚያ ትኰት በመሰጠት፣ ብሔር ብሔረሰቦች ሁሉ ተፈጥረው በኖሩበት አካባቢ፣ትንሽ ትልቅ ሳይባሉ ተደራጅተው፣ በቋንቋቸው ራስን በራስ ለማስተዳደር እንዲችሉ ማገዝ ይገባዋል። አደረጃጀቱም እንደ መኖሪያ አካባቢያቸው ስፋትና ጥበት፣በክልል ራስ ገዝ፣ በዞን ራስ ገዝም ሆነ፣ በወረዳ ራስ ገዝ ሊሆን ይችላል።ይህ ከሆነ የብሔር ቅራኔ ይለዝባል፣ ጥላቻ ይቀረፋል፣ሰላምና ፍቅር ያብባል።

ሌላው ሕዝባችንን በእርስ በርስ ጦርነት እየማገደ ያለው፣ የመንግሥት ሥልጣን ጥያቄ ነው።የመንግሥት ሥልጣን የሚያስፈልገው ሕዝቡን በቅንነት በማገልገል በሰላም በማስተደደር ወደ ጋራ ብልፅግና ለመምራት ከሆነ፣ ሕዝቡ ራሱ መሪዎቹን መምረጥ ይኖርበታል። ሕዝብ የሚያምንባቸውን ሊመርጥ የሚችለው ደግሞ ለምርጫ ከሚቀርቡለት ዕጩዎች መካከል በመሆኑ፣የአቢዮታዊ ዴሞክራሲ ድርጅታዊ አሠራር ተወግዶ፣ለተወዳዳሪ ፓርቲዎች ሁሉ እኩል፣ሰላማዊ የውድድር መድርክ ሊሰፋ ይገባል። ፓርላሜንተሪያዊ ቅርጸ መንግሥትም፣ ወታደራዊ ደርግም ሆነ ኢሕአዴግ፣በድርጅታዊ አሰራር፣ የመንግሥት ሥልጣንን ከሕዝቡ በመነጠቅ የተጠቀሙበት ስልት በመሆኑ ተወግዶ፣ በፕሬዚደንታዊ ቅርፀ መንግሥት ሊተካ ይገባዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  “ፌዴሬሽናችን ለዘላለም!! ኮሚቴዎቹ ግን…” MD 2013

ስለሆነም ሕዝባችን አሁን ካለበት ጦርነትና ጥላቻ ለመገላገል እንዲችል ፣ መንግሥትም ሆነ ክልሎች ፣ የፌድራል ሕገ መንግሥቱን አክብረው፣ ግዴታቸውን በመፈጸም፣ መብታቸውን ማስከበር ይገባቸዋል። በዚህም ረገድ ከሁሉ በፊት የትግራይ ሕዝብ በክልሉ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሕገ መንግሥታዊ መብቱ ሊከበርለት ይገባል። ሕወሐትም በበኩሉ የፌድራል መንግሥቱን ሥልጣን አክብሮ፣ከውጭ ጉዳይ ግንኙነት፣ ከገንዘብ ሕትመትና ከባንክ አስተዳደር፣እንዲሁም በመከላካያ ኃይል አደረጃጀትና ግንባታ መታቀብ ይኖርበታል።

በዚህ ላይ ከመግባባት ላይ ከተደረስ፣ ከአፍሪካ አንድነት አደራዳሪ ላይ በተጨማሪ፣ በሐወሐት የተጠቋሙ አደራዳሪ መቀበል ያስፈልጋል።በባህላችንም አስታራቂ ሽማግሌ የሚመረጠው ከግራና ከቀኙ ነውና። በሌላውም በኩል የአፍሪካ አንድነትን በፋይናንስና በሎጅስቲክ የሚረዱ የአውሮፓ ኅብረትና የአሜሪካ አማካሪዎችንና ታዛቢዎችን መጨመር እርቁን የሚያፋጥን ይሆናል።መቼም ቢሆን አደራዳሪዎቹ ወሳኞች አይደሉም፣ ወሳኞቹ በሁለቱ በኩል የተመረጡ ተደራዳሪዎች ናቸውና።

ስለሆነም እስከ አሁን ድረስ የፈሰሰው የወገኖቻችን ደም አይታፈስምና፣ ተጨማሪ ደም እንዳይፈስ ድርድሩ በፍጥነት ተጀምሮ፣የአፍሪካ የሰላም ልዑክ ተጋብዞ፣ በሁለቱ ጦር መካከል ተገኝቶ ጦርነቱን መግታት ይኖርበታል። ከዚያም የእርዳታ በሮች ተከፍተው፣ በሁለቱ እጅ የሚገኙ፣እስረኞችና መርኮኞች ሊለቀቁ ይገባል። በሁለተኛ ደረጃም የፌድራል መንግሥቱ፣ ለትግራይ ሕዝብ የተመደበውን ባጄት ለቅቆ፣ የባንክ፣ የቴሌፎን፣ የማብራትና የውሃ አገልግሎትን በቀደመው መልኩ መስጠት ይኖርበታል።ይህ ከሆነ ሕወሐትም የቡድን ትጥቁን ፈትቶ ለስላም አስከባሪው ማስረከብ ይገባውል።የትግራይ የሕዝብ ተወካዮችም ወደ ሁለቱ ምክር ቤቶች ሊመለሱ፣የታገደባቸውም ሐብትና ንብረት ሊለቀቅልቅቸው ያስፈልጋል።

የከረረው ቅራኔ በዚህ መልኩ ከረገበ፣ የተረፈው ችግር፣ በአገራዊ ምክክር ኮሚሽን በውይይት፣የሚለዝብና በህግ አግባብም የሚፈታ ይሆናል። ይህም የሰላማችን፣የልማታችን፣ የዕድገታችንና የአንድነታቸን ጸር የሆነው ጦርነት፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከሕዝባችን እንዲወገድ፣ የሁላችንም ጸሎት ወደ ቸሩ ፈጣሪ አምላካችን ይሁን።እርሱ ሁሉንም መልካም ማድረግ ያውቅበታልና።አሜን! ይሁን!

ተጨማሪ ያንብቡ:  ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. እና ኢትዮጵያ - ከገብረመድህን አረአያ (አዳዲስ መረጃዎች)

3 Comments

  1. ጆብር ሄይ አባ ዊርቱ ነዎት? በውነት የችግራችን ምንጭ ቋንቋና ሀይማኖት ነው? እንደሚሉን አሁንም አልተገበረም ነው የሚሉን መፍትሄውም ህገ መንግስቱን በሚገባ መተግበር ነው። ለርሶ ህገ መንግስት ለሌላው ህገ አራዊት ከአቅም በላይ እየተተረጎመ ነው። ዜጎች በህብረት የፈጠሩትን አፍሪካዊ ቋንቋ አሽቀንጥረው ጥለው በላቲን እየተራቀቁ ነው የሀይማኖት ነጻነትን ተሰጥቷቸው እነሱ የማያምኑበትን የሀይማኖት ተቋም እያወደሙ ነው እነሱ የማያምኑትን ሀይማኖት የሚያምኑትን እያዋከቡ እረፍት እየነሱ አስገድደው እያስቀየሩ ነው። እንግዲህ ከባህር ማዶ በምንም ከማይመሳሰሉት ህዝብ ጋር ያለ ችግር እየኖሩ በሀገሩ በሚኖር ዜጋ ከላይ የከተቡትን የመፍትሄ ሀሳብ ከላኩ ምን ይባላል። ሲጠቃለል ሁሉም ጠፍቶ እኛ እንኑር ነው ይህ ደግሞ ከየት ሊመጣ እንደሚችል በሚገባ እንገነዘባለን።

  2. አሁን እኝህን ማን የድሮዋ አዳነች አቤቤ ናቸው ይላል እሳቸውም እንደ ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ አለም አቀፍ ሞዴል መስለዋል ሲራመዱም ሆነ ሲናገሩ እንደ ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ በታላቅ ጥንቃቄ ነው እረ ስንቱ ይነገራል እንኳንም ከናዝሬት ነው ከአምቦ መጡልን አዲስ አበባ እንደእርሶ አይነት ሰው ከየት ይገኝልን ነበር? ከሉባው አጠገብ ዘና ብለው ቁጭ ብለዋል ያድርግሎት፡፡ 50 ሚሊዮን ብር አካውንቶ ውስጥ የከተተው ጠላት ነው አይመልሱለት፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.