እንደ ታደሰ ወረደ ስለ ጥምር ጦሩ ብርታት የተናገረ የመንግስት አካልም የለም

ጥምር ጦሩ ስላዘነበበት መልሶ ማጥቃት ቃላት አጥሮታል። ታደሰ ለጥምር ጦሩ ያለውን አድናቆት ለመግለፅ እኔም ቃላት አጠረኝ ታደሰ ለጥምር ጦሩ ያለውን አድናቆት ምራቁን ውጦ ደግሞ ይቀጥላል። ጋዜጠኞቹ ስለ አሸባሪው ትህነግ ኃይል ብርታት እንሰማለን ብለው ሄደው የሚሰሙት ጉድ ስለ ጥምር ጦሩ ነው። እንዲህ አይነት ነገር ይገጥመናል ብለን አስበን አናውቅም ብሏል።
ግን አሁንም ተመልሰው ያጠቁናል። አሁንም ወረራውን ይቀጥላሉ። ምክንያቱም የጥምር ጦሩ ብርታት በራሱ ራስ ምታት ሆኖባቸዋል። ይህን ቶሎ ካላስቆምን በሕይወት መኖር አንችልም ብለው ሰግተዋል። በዚህም ምክንያት የመጣብንን ኃይለኛ ጦር ለማስቆም ከእስካሁኑ የባሰ ሕዝባዊ ማዕበል ያስፈልጋል ብለው እየሰሩ ነው። ሰሞኑን መጠነ ሰፊ ወረራ ለማድረግ ዝግጅት ላይ ናቸው።-
ጌታቸው ሽፈራው

\

ተጨማሪ ያንብቡ:  በ‹‹ጀሃዳዊ ሃረካት›› ፊልም ላይ ከ28ቱ ዋንኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ

Leave a Reply

Your email address will not be published.