በምርጫ ቦርድ የቱሻ ፖለቲካ፣ በብልጽግና ጉባዔ ዕጩ ተመራጭ አስመራጭ ሆኖ ተወነ! ህሊናቸው ያረጠ ተዋናይ ፖለቲከኞች!

ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

‹‹ ጊዜው ጎዳኝ እንጂ እኔ ሰው አላማ

የአህያ ልጅ በቅሎ ወርቅ ተሸልማ!!!››

‹‹ምነው እማምዬ ለምን ታለቅሻለሽ

                            በወፍጮው ላይ መጁ ሲጨፍር እያየሽ!!!››……………አለማየሁ እሸቴ

በብልፅግና ጉባዔ ዕጩ ተመራጭ አስመራጭ ሆኖ መሰየሙ ትክክል እንዳልነበር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ከስድስት ወር በኃላ አስታውቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከስድስት ወራት በኃላ የወረወረው አለሎ ተንከባሎ  የብልፅግና ፓርቲ  ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተላትሞ፣ የፓርቲው ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት አመራረጥን በተመለከተ፣ ዕጩ የሆነ ሰው አስመራጭ የሚሆን ከሆነ፣ በተለይ አስመራጭ የነበሩት የአገር መሪ ዶክተር አብይ አህመድ በመሆናቸው በምርጫው ሒደት ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር አሠራር መሆኑን አስታውቆል፡፡   ጠቅልይ ሚንስትር አብይ አህመድ ራሳቸው አስመራጭ ሆነው ጥቆማ በመቀበል ‹‹ዓብይ ዕጩ መሆን አለበት ወይስ የለበትም ›› ከተሳታፊዎች ፊት ለፊት ተቀምጠው ምርጫውን ሲያካሂዱ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የብልፅግና ፓርቲ  ጠቅላላ ጉባዔ የምርጫ አካሄዱን አስመልክቶ ለምርጫ ዕጩ ሆኖ የሚቀርብ ሰው፣ አስመራጭ እንዳይሆን የሚከለክል አንቀፅ በማስፈር ፣ መተዳደሪያ ደንቡን አስተካክሎ ወደፊት በሚደረገው ጠቅላላ ጉባዔ እንዲያፀድቅ  ምርጫ ቦርድ አሳስቦል፡፡ ምርጫ ቦርድ የብልፅግና ፓርቲ የመተዳደሪያ ደንቡን አስቀድሞ አለመቀበሉን በገሃድ በሪፖርቱ ሠነድ አምነዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ የሌሎች ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ማሞላት የሚገባቸውን ሲያሞሉ አድሎ በመፈፀም እንዳይወዳደሩ ያገዶቸው ፓርቲዎች ምስክር ናቸው፡፡ የብልፅግና ፓርቲ የመተዳደሪያ ደንቡ ሳይኖረው የምርጫው አካሄድና ሂደት፣ የምርጫ አሰፈፃሚ አካል እንዴት እንደሚመረጥ፣ የዕጩ ጥቆማ፣ በሚስጢር ድምፅ አሰጣጥ፣ ድምፅ ቆጠራ፣ ውጤት ማዳመር፣ ውጤት አገላለፅ የመሳሰሉት አንኮር የፓርቲ መተዳደሪያ ደብቦች እንደሌሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በፍርሃት ድፍረት ገልፃለች፡፡ ከፈረሱ በፊት ጋሪው ቀደመ ማለት እንዲያ ነው፡፡ ትላንት በሽመልስ ከማል ዛሬ በሽመልስ አብዲሳ አሳሮን አየች ብርቱካን ሚደቅሳ!!!  ብለው ዘፈኑላት ወይ የሶ አበሳ፡፡ አበበ በሶ በላ አይ የህግ ሰው ያስተማረሽ ህዝብ አያውቅም ብለሽ፣ የጮኸልሽ ህዝብ አያውቅም ብለሽ የህሊና ሠላም አጣሽ፡፡ ‹‹ ጊዜው ጎዳኝ እንጂ እኔ ሰው አላማ፣ የአህያ ልጅ በቅሎ ወርቅ ተሸልማ!!!›› በማለት የአለማየሁ እቴን ዘፈን በገጠር እረኞች በከተማ አዝማሪዎች ያዜሙት ለዚያ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ለህዝብ በመቆም የህዝቡን ብሶት በማስተጋባትና  ርሃብ፣ ስደት፣ እስራትና ጦርነት በማጋለጥ ሲያዜሙ ዘመናት ተቆጥሮል፡፡ ከዛሬ ያረጡ ፖለቲከኞች ሙዚቀኞች መንግሥትን በማጋለጥ በህዝብ ዘንድ ለሠላም፣ ለፍቅርና ለአንድነት በመስበክ ትልቅ ተሰሚነት አላቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከሕዝብ እውነተኛ ፍላጎቶች መማር ብልኅነት ነው - አምባቸው ደጀኔ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  ባለሙያዎች የብልፅግና ፓርቲ  ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዬ) እንዳይቀርፁ ተከልክለው ነበር፡  የብልፅግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ የስራ አስፈፃሚ ምርጫ ጊዜ የምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች ስብሰባው እንዳይገቡ ተከልክለው ነበር፡፡ የሌሎች ፓርቲዎችን ከግር እስከ ራሱ ስትቀርፁ የብልጽግና ፓርቲን ዝም ማለታችሁ የእንጀራ ጉዳይ ሆኖባችሁ እንደሆነ ህዝብ ያውቃል፡፡ ድኃ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ንጣት ይገለው ነበር ይላሉ አበው፡፡ ብልፅግና ፓርቲ  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  ሹማምንቶች ቪላ ቤት ተሠጥቶችኃል፣ ሦስት መኪና ተመድቦላችኃል፣ በቦዲጋርድ በቀይ ኮፍያ ኮማንዶች ትጠበቃላችሁ፣ ረብጣ ዶለር የደም ወዝ ይቆረጥላችኃል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ገና ካመሠራረቱ የአንድ ፓርቲ ሥነምግባር መመዘኛዎች ሳያሞላ የተመሠረተ መሆኑንና ምክትል ፕሬዜዳንት ያልመረጠ፣ የፓርቲው ኢንስፔክሽን ኮሚሽን አባላት ያልመረጠ እንደነበር ምርጫ ቦርድ ያውቅ ነበር፡፡ ይባስ ብሎ ኢንስፔክሽን ኮሚሽን አባላት ለጠቅላላ ጉባዔ ብቻ ቀርበው የተሸሙ መሆናቸው ህገወጥ አሰራር መሆኑን ባርዱ እያወቀ እንዳላወቀ ሆኖ አሳልፎል፡  በማጠቃለያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ህሊናቸው ለጥቅም የሸጡ ቅጥረኛ በመሆን የሙያ ስነምግባራቸውን ያላሞሉና የዴሞክራሲያዊ ሂደቱን ያቀጨጩ በመሆናቸው በሚቀጥለው ትውልድ ሙያቸውን በማርከስ በታሪክ ሲታወሱ ይኖራሉ፡፡

 

ምንጭ

(1) በብልፅግና ጉባዔ ዕጩ ተመራጭ አስመራጭ ሆኖ መሰየሙ ትክክል እንዳልነበር ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡ ሪፖርተር ጋዜጣ ሴፕቴንበር 14 ቀን 2022

 

4 Comments

  1. ፂዮን ዘማርያም፣
    ምናለ ባትዘላብድ? መንግሥት በምርጫ ኮሚሽን ውስጥ ጣልቃ የሚገባ ከሆነ ሥራውን እለቃለሁ ያለችው ብርቱካን ሚዴቅሳ ነች። መንግሥት እጁን መሰብሰብ ነበረበት! ምርጫውና ውጤቱ ትህነግ ሲያካሄድ ከኖረው እጅግ የተሻለ የሆነው ለዚህ ነው። ብርቱካን ሚዴቅሳን በመንቀፍ ምርጫውን ማዋረድ የትህነግ ሥራ ነው። ስንት እንደከፈሉህ አንተ ታውቃለህ። የኢትዮጵያን ሕዝብ ግን ማሳመን ቀርቶ ራስህ ማዋረድክን ማ ይንገርህ?

  2. hey wait a minute ato nebiyu…..what the auth wrote seem that you did not saunderstand plz read it again….you just can not condemn the guy for telling his opinion…next time think before you write

  3. Nebiyu በትክክለኛ ስምህ “እውነት ቢሆን”ብትጽፍ ምን አለበት? መተዳደሪያህ ስድብ ሆነ ማለት ነው? ስላንተ ማውራት ጊዜ ማጥፋት ሁኖ ወደ ሌላው ስንተላለፍ ወ/ሮ ሚደቅሳ ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ፤ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ትክክል ሰርታችሁ ከዚህ የተቀማጠለ ኑሮ ውረዱ ማለት ግፍ ነው፡፡ ባይሆን የሚባለው እግዚሃርን ፍሩ ነው፡፡ ሬሳቸው ይጎተታል እንጅ አሁን ካሉበት አይወርዱም፡፡
    ሴትዮዋ ሚደቅሳ ማለት ነው የገረመኝ፤ ኦነግ የተባለውን፤ትህነግ የተባለውን በሰው ልጅ ታሪክ ሊደርስ ይችላል ተብሎ የማይገመተውን በደል የፈጸሙ ድርጅቶችን እውቅና ስ ት ሰ ጥ ኢሰፓ ወንጀለኛ ድርጅት ነው እውቅና አልሰጠውም ትላለች፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ ያሳያችሁ ኢሰፓ ኢትዮጵያ ላይ ያደረሰው በደል ከነዚህ ድርጅቶች የከፋ ነው? ኢሰፓ የኢትዮጵያን አንድነት ለመጠበቅ ያደረግሁት ነው ብሎ ቢናገር ምክንያታዊ ይሆናል ኦነግና ትህነግ ግ ን ኢትዮጵያ ሲባል ክፉ ዛር እንዳንዘረዘራቸው ያማቸዋል፡፡ ኢሰፓ በሃገርና በህዝብ ያደረሰው ኦነግ ና ትህነግ ካደረሱት የከፋ አይሆንም ፡፡ ስለዚህ ተገዳዳሪ ድርጅት እንዲኖረን ወ/ሮ ሚደቅሳ ከራስሽ ተማክረሽ ፍቃድ ይሰጣቸው ከዛ በተረፍ በህዝብ ካመናችሁ መራጩ ህዝብ ይሆናል ስለዚህ ሌላውን ለህዝብ ተይው፡፡ ምንም እንኳን በብርሃኑ ቀለበት ስትሽክከሪ ትግሬዎች ቢያስሩሽም ትፈታ ብለን በሃሩር በበርዶ ተንገላተናል አንችም አሁን ለፍትህና ለህዝብ ያንን ብድርሽን ክፈይ የዚህ አለም ምቾት ጊዜያዊ ነው፡፡

  4. It is difficult to understand Birtukan’s treasonous involvement in the fake election and the ludicrous business of the PP party congress. Is she operating as a foreign agent or was she ensnared into the Oromumma project of the OLFites n power? There is nothing she could to reverse this great wrong and injustice she committed against the people of Ethiopia at this historic moment. She has practically played the most crucial role in helping PP bury the prospect of democracy.
    How justified Lidetu Ayalew has become when we see the involvements of Berhanu Nega and Birtukan Mideksa against the democratic interests of the Ethiopian people!

Leave a Reply

Your email address will not be published.