አሸባሪው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (ትሕነግ) ድርድር እና ሰላማዊ የግጭት መፍቻ አማራጮችን በድጋሜ የጦርነት ማራመጃ እና የሽብር ማሳለጫ መሳሪያ አድርጎ እንዲጠቀም ሊፈቀድለት አይገባም

  • የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ለድርድር እና ለሰላም አማራጮች ቅድሚያ የሚሰጥ፣ እና ያልተቆጠበ ድጋፍ የሚያደርግ ቢሆንም ፣ የሽብር ቡድኑ የድርድር እና የሰላም አማራጮችን የጦርነት ማራመጃ እና የሽብር ማሳለጫ መሳሪያ አድርጎ የሚጠቀመምበትን አግባብ በጽኑ ያወግዛል፡፡
  • በዚህ አጋጣሚ ፓርቲያችን አብን መመዘኛውን ለሚያሟሉ የአማራ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውን ወጣቶች በሙሉ ፣ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ያወጣውን የምልመላ ጥሪ በመቀበል ሠራዊቱን እንድትቀላቀሉ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

______

ተስፋፊው ፣ ሽብርተኛው እና ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (ትሕነግ) እያለ የሚጠራው የዘር ማጥፋት “ፖለቲካ” አራማጁ የወንጀለኞች ቡድን ፣ በጦር ግንባር የደረሰበትን ከፍተኛ ሽንፈት ተከትሎ መስከረም 01 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት ላይ ባወጣው የማደናገሪያ መግለጫ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ይሁንና መግለጫው የተጻፈበት ቀለም ሳይደርቅ በማግስቱ መስከረም 2 ቀን 2015 ዓ.ም ማለዳ ላይ ከሱዳን ድንበር በኩል በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ልዩ ስሙ ቲሃ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ አዲስ ጥቃት ከፍቶ በጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ጥምር ኃይላችን ጥቃቱ የተመከተ ሲሆን ፣ ቡድኑ ከፍተኛ ኪሳራ አስተናግዶ ተመልሷል፡፡ አብን ለድርድር እና ለሰላም አማራጮች ቅድሚያ የሚሰጥ እና ያልተቆጠበ ድጋፍ የሚያደርግ ንቅናቄ ሲሆን አለመግባባቶች ሁሉ በሰላም መፈታት አለባቸው የሚል ጽኑ አቋም አለው:: ከዚህ ጽኑ አቋሙ በመነሳት ጦርነቱ በሰላማዊ መንገድ በድርድር እና በሽምግልና እንዲፈታ ልባዊ ጥረት ለሚያደርጉ አካላት ሁሉ አድናቆቱን እና አክብሮቱን መገለጽ ይወዳል:: ነገር ግን አሸባሪው እና ተስፋፊው የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር የድርድር እና የሰላም አማራጮችን የጦርነት ማራመጃ እና የሽብር ማሳለጫ መሳሪያ የሚያደርግበትን አግባብ በጽኑ ያወግዛል ፣ ይቃወማል ፣ ይታገላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያ በመጪው ጊዜዎችዋ ከባድ ደመናን ያዘለ የርስ በርስ መጠፋፋት ዝናብ እንዳጃበባት አንድ ጥናት አመለከተ

የሽብር ቡድኑ በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ እና በአማራ ሕዝብ መቃብር ላይ “ታላቋን” ትግራይ ማቆም በሚል ቅዥት የሚባክን ፍሽስታዊ ድርጅት ሲሆን ፣ ሰይጣናዊ ዓላማውን አሳካለሁ በሚል በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ያልፈጸመው እና ያላስፈጸመው ወንጀል የለም፡፡ ቡድኑ በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ ድርድር እና ሰላማዊ አማራጮች የጥፋት አላማውን ሊያሳካ እንደማይችል ስለሚያውቅ ለአምስት አስር ዓመታት በዘለቀው የውንብድና እና የሽብር ታሪኩ ፣ ድርድር እና ሰላማዊ አማራጮችን ለበጎ የተጠቀመበት አጋጣሚ ኖሮት አያውቅም፡፡ የሽብር ቡድኑ የማደናገሪያ የ”ሰላም ጥሪ” መግለጫውን ከማውጣቱ በፊት ባወጣቸው ተከታታይ መግለጫዎች እና ለሽብር ቡድኑ ሚዲያዎች በሰጣቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች የተኩስ አቁሙ መፍረሱን ፣ የሰላም በር መዘጋቱን እና ፍላጎቱን በኃይል እንደሚያስፈጽም አረጋግጦ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ የከፈተ ሲሆን ፣ ከሽብር ቡድኑ እና ስፖንሰሮቹ ግምት ውጭ ከፍተኛ ወታደራዊ ሽንፈት በመከናነቡ እና ወታደራዊ መዘናፍ በማስተናገዱ ፣ ሲያራክሰው እና ሲዘባበትበት የነበረውን በአፍሪካ ሕብረት የሚመራውን የሰላም ጥረት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተቀብያለሁ በማለት ጊዜ ለመግዛት እና የዲፕሎማሲ ትርፍ ለማጋበስ ጥረት አድርጓል፡፡

የሽብር ቡድኑ ከማደናገሪያ መግለጫው ጎን ለጎን ጦርነቱን አፋፍሞ የቀጠለ ፣ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች በሚገኙ ንጹሃን ዜጎች ላይ ጭፍጨፋን ጨምሮ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በሲቪልና ሕዝባዊ ተቋማት ላይ ውድመት እና ዝርፊያ እያደረሰ ሲሆን ፣ ይህ መግለጫ በሚጻፍበት ሰዓት እንኳ የተለመደውን የሰው መዓበል አስከትሎ በቆቦ ግንባር ሌላ ዙር ጦርነት ለመክፈት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ የሽብር ቡድኑ ቁሜለታለሁ የሚለውን የጥፋት ዓላማ ለማሳካት ሰብዓዊ እርዳታን እንደ ስንቅ እና ትጥቅ ማሟያ ፣ ድርድር እና የሰላም አማራጮችን እንደ ጊዜ መግዣ እና ማወናበጃ ፣ ክህደት እና ማጭበርበርን እንደ ሁነኛ የትግል ስልት የሚጠቀም የለየለት ፋሽስታዊ ቡድን ነው፡፡ ፓርቲያችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የሀገራችን ኢትዮጵያ እና የመላው ኢትዮጵያውያንን ዘላቂ ሰላም ፣ ጥቅም እና ኅልውና ማረጋገጥ የሚቻለው የሽብር ቡድኑ ኅልውና የሚከስምበትን የጦር ፣ የኮሚኒኬሽን፣ የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ ስልቶች በተሟላ ሁኔታ ስራ ላይ በማዋል ብቻ ነው ብሎ ያምናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: ዶ/ር አክሎግ ቢራራ እና የአረናው አምዶም ገ/ሥላሴ ልዩ ቃለምልልስ ስለምርጫው * አገዛዙ የሕዝቡን ድምጽ ወደጎን አድርጎ ለራሱ የሰጠውን የምርጫ ውጤት ይፋ ለማድረግ ተዘጋጅቷል * በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ተማሪዎች የሕዝብ ድምፅ እንዲከበር መጠየቅ ጀምረዋል * በአዲስ አበባ የ17 ዓመቷን ወጣት ሃና ሌላንጎን የደፈሩት ከ17 ዓመት እስከ እድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸውና ሌሎችም

የሽብር ቡድኑ ስሪት ፣ ባህሪ እና ታሪክ በማናቸውም ሁኔታ ለድርድር እና ሰላማዊ አማራጭ እውነተኛ ዝግጁነት እንዲኖረው የማያስችለው በመሆኑ ፣ ቡድኑ ኅልውናውን እስከቀጠለ ድረስ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማኅበራዊ እረፍት የማያገኝ እና ቡድኑ ቁሜለታለሁ የሚለውን የትግራይ ሕዝብም ቡድኑ እያደረሰበት ካለው ሰቆቃ መታደግ የሚቻል አይሆንም፡፡ ስለሆነም ፥

፩. መላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የሽብር ቡድኑ ባወጣው የማደናገሪያ መግለጫ ሳትዘናጉ ፣ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ለጥምር ጦሩ እያደረጋችሁ ያላችሁትን የማቴርያል እና የሞራል ድጋፍ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

፪. የፌዴራሉ መንግስት ከሽብር ቡድኑ ጋር ሰላም ለማውረድ በሚል በሶስተኛ ወገኖች በኩል ወይም በቀጥታ በሚያደርገው ጥረት ፣ የሽብር ቡድኑን ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ከማስፈታት ያነሰ ግብ እንዳይዝ እና የሽብር ቡድኑን ኅልውና ለማክሰም የሚያስችሉ ሁሉንም አማራጮች አሟጦ እንዲጠቀም ጥሪያችንን እያስተላለፍን ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አባላት ፣ ደጋፊዎች እና በየደረጃው ያለን አመራሮች የሽብር ቡድኑን ኅልውና ለማክሰም ለሚደረግ ማናቸውም ጥረት ሙሉ ድጋፋችንን የምንሰጥ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

፫.. በዚህ አጋጣሚ ፓርቲያችን አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፣ መመዘኛውን ለሚያሟሉ መላው የአማራ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውን ወጣቶች በሙሉ ፣ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ያወጣውን የምልመላ ጥሪ በመቀበል ሠራዊቱን እንድትቀላቀሉ ጥሪውን ያስተላልፋል፡:

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)

አዲስ አበባ ፣ ሸዋ ፣ ኢትዮጵያ

መስከረም 3 ቀን 2015 ዓ.ም

1 Comment

  1. Don’t you really know that you’re good playing cards of the two factions of the same deadly criminal political system ( The Mekele TPLF snd the Arat kilo Prosperity? Is it not your political stupidity and moral bankruptcy that is causing a very painful situation in the country ? Absolutely it is !

    You became good friends of evil- minded and evil- guided ruling elites and you did nothing as far as making people’s dreams for a true democratic system is concerned . Don’t you have a common sense of shame and dishonesty when you just keep blaming TPLF only while you are sitting with the so called people’s representatives who are playing a very deadly political game of more than three decades ?
    I am sorry to say but I have to say that you’re one of the allies of the so called Prosperity Party that has directly or indirectly murdered thousands of innocent people and forced millions to face unbearable situation .
    Get out of the very bloody political game you’re playing with and do what is right for a real meaning of democracy and development !
    I hate to say but I have to say that the very rhetoric of eliminating TPLF or any other evil – products of an evil political system but not the Arat Kilo EPRDF is absolutely nonsensical! It will make you foolish victims of an endless or vicious cycle of war and no war an no peace type of situation .
    Do you remember when you formed yourself as a Movement ? You said that you were committed to making a fundamental democratic change , not seeing a cynical political game of reforming EPRDF ! That sounded great! Sadly enough. you became a very good guys of it and caused unbearably horrible situation in the country .
    Now ,You re left with two decisive choices : either you help the people to defeat this stupid war and getting rid of the criminal political system of EPRDF/Prosperity all together and move forward with the concerted effort of making democracy a reality , or else you keep going with the criminal political system and be responsible for all horrible and bloody behavior and act you’re languishing in ! There is no any other legitimate and effective way out at all!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.