የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ለአቶ ሠማ ጥሩነህ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተሠማ

የፍትሕ ቢሮው ለአቶ ሠማ ጥሩነህ ማስጠንቀቂያውን የሠጠው የኢትዮ 360 ሚዲያ ቅዳሜ መስከረም 8/2015 የአቶ ሠማን የትምህርት ማስረጃ ማጭበርበር አስመልክቶ በሠጠው ጥቆማ መነሻነት ተመስርቶ መሆኑ ተሰምቷል።
የፍትህ ቢሮው የሙስና ወንጀሉን ማጣራት ከመጀመሩ በፊት አቶ ሰማ ተምሮበታል ከተባለው የቻይና ዩንቨርስቲ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኤንድ ኢኮኖሚክስ ተምሮ የተሠጠው የ(PHD) የምስክር ወረቀት ካለ በኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የአቻ ግምቱን በማሠራት እስከ መስከረም 12/01/2015 ዓ/ም ማስረጃውን ለሶስት ተቋማት እንዲያስገባ አዝዟል።
በዚህም አንደኛ ለክልሉ ፍትሕ ቢሮው፣ ሁለተኛ ለክልሉ ሲቪል ሠርቪስ ኮሚሽን፣ ሦስተኛ ለክልሉ የብልፅግና ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ማረጃውን የማያቀርብ ከሆነ ምርመራ ማጣራት እንደሚጀምር ማስታወቁ ተሠምቷል።
ይህንን የሠሙ የትምህርት ማስረጃ ያጭበረበሩ ሌሎች ባለ ስልጣናት ጭምር ጭንቅ ውስጥ መግባታቸው ታውቋል።

ለገ ግዮን

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: ሜክሲኮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በነጻ ቪዛ ወደ አሜሪካ እንዲገቡ አደረገች | የፕ/ት ትራምፕን ስደተኞች እንዳይገቡ የሚያግደው ውሳኔ በከፊል በአገሪቱ የፌዴራል ፍርድ ቤት ታገደ

1 Comment

  1. እንዴት ያለ አደጋ ገጠመው ወይ ወዳጄ ነገሩ ዘለግ ብሎ ወደ ብርሃኑም፤አረጋዊም፤ዶ/ር አብይ እንኳን ለጊዜው ይዝለላቸው ተረብሸው ግብጽን ያስገባሉ፡፡ እንዴት ነው እሱስ ማስተር አይበቃውም ነበር እንዴት ያለ ጭካኔ ነው ዶክተር ይሻለኛል ብሎ ማስመረጥ፡፡ እንደው አይበለው እንጅ ዩኒቨርስቲው እንዲህ ያለ ሰው አላውቅም ቢል ቅጣቱ ምን ይሆን? አይ ቲክ ቶክ ይሰሩብሃል እንግዲህ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.