ዕዉር ከመሪዉ ይጣላል  ፤ ለማኝ አኩፋዳዉን ይጣላል  

በአገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት አምሳ  ዐመታት ሆነዉ እና እየሆነ ላለዉ  ሁሉ  ተጠያቂዉ  እና የችግሩ ምንጭ ከዉስጥ ሆኖ ወደ ዉጭ ማላከክ በህዝቦች የዘመናት መከራ እና ግፍ እንደማላገጥ ነዉ ፡፡

በተለይም የፖለቲካ ክንፍ እና ህዝብ  እንወክላለን ለሚሉት ነገር ግን በተደጋጋሚ በአገር እና በሚወክሉት ህዝብ ላይ  ክህደት ለሚፈፅሙት የረሱት ነገር ቢኖር በቁም መሞታቸዉን እና ያለምንም  ስራ ከክፉ ስራቸዉ ጋር ቤተሰባቸዉን እና ህዝባቸዉን አጋም እና ቀጋ አድርገዉ ወደ ማይቀረዉ እንደሚሄዱ  ከታሪክ እና ከቀደመዉ  ማንነታቸዉን  ሊማሩ አለመቻላቸዉ  ፡፡

በኢትዮጵያ የመንግስታት ታሪክ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን በክህደት የገደላት ኢህአዴግ  መሆኑን ካለፉት የግማሽ ክ/ዘመን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር አሳልፎ የመስጠት፣ ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረግ፣ የዓማራን ህዝብ ያገለለ ህገ-ስርዓት ማንበር፣ የዓማራን ህዝብ በሁሉ ማግለል፤ መግደል ፣ መበደል ፣ ማንነት ተኮር የዘር ጭፍጨፋ የተደረገዉ  እና እየሆነ ያለዉ ፣ የኢትዮጵያን አንድነት እና ጥንተ መሰረት ለማዛባት በክልል አደረጃጀት ጥንታዊ እና ታሪካዊ ዳር ድንበር ማፍረስ ፣ በፀረ-ኢትዮያ ኃይሎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሽፋን መስጠት እና ማጎብደድ መኖሩን ከትናንት አስከ ዛሬ የተሰሩትን ማየት በቂ ነዉ ፡፡

የኢህዴግን ክህደት እና በመንግስት ስርዓት  ዉስጥ እያለ በራሱ ህዝብ እና አገር ክህደት  እና ሽብር መፍጠሩን ከሶስት ዓመታት በፊት ኢህአዴግ በሞት ጣር በነበረበት በራሱ አረጋጧል ፡፡ ዳሩ ግን ጠያቂ እና ኃላፊነት የሚሰማዉ አካል እና ህዝብን የሚያስተባበር ባለመኖሩ የተነሳ ወንጀለኞች እና ጥፋተኞች ተጠያቂዉ  ሳይጠየቅ ዛሬም የኢህአዴግ ክህደት እና ጥፋት እንደ ሰደድ ዕሳት አገሪቷን እና ህዝቧን እየበላ ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በአፍሪካ የአደና ጉዞ ላይ (ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)

ለዚህ ሁሉ በኢህአዴግ ከበረኃ  ትግል አስካሁን  ሽፋን በመስጠት  ትልቁን ሚና የሚጫወተዉ  የጥንቱ  ኢህአዴን  የዛሬዉ ብአዴን መሆኑን ከማንም በላይ የኢትዮጵያዉያን  ታሪካዊ ጠላቶች ሳይቀሩ የሚያዉቀት እና የሚተማመኑበት ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያ የቀደመ ታላቅነቷን እንድታጣ፣  የባህር በር አልባ ስትሆን ፣ የኢትዮጵያዉያን እና ዓማራ ግዛት አሳልፎ ለትህነግ እና ሱዳን የሰጠ፣ የዓማራን ህዝብ በመላ አገሪቷ የዓማራን ህዝብ ማዋረድ ፣ ማሳደድ …ኢትዮጵያዉያን  በፖለቲካ ፣ በማህበራዊ ፣ ኢሰባዊ እና ቁሳዊ  ችግር መዳረግ ሁሉ ተጠያቂዉ የትናንቱ ኢህዴን እና የዛሬዉ ብአዴን  ከታሪክ መማር የማይችል  ከራሱ እና ከመሪዉ የሚጣላ መሆኑን መቶ ጊዜ መሳሳት ሳይሆን ሽ  ጊዜ አገር መክዳት መሆኑን   በቁም ወደ በድን  ደጋግሞ  ማሳያ  ነዉ ፡፡

በዓለም ላይ በአንድ ህዝብ እና አገር ላይ በራሱ  ተወላጂ ከፍተኛ ክህደት የተፈፀመበት  ህዝብ ቢኖር  የኢትዮጵያ ህዝብ እና ዓማራ ህዝብ መሆኑን የሚክድ ቢኖር ሰይጣን እና ፀረ-ህዝብ፤ ፀረ-ኢትዮጵያ ብቻ ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያ አገሬ ፤ እኔም ኢትዮጵያ ነኝ የሚል ከህዝብ ጋር አይን  እና ናጫ በመሆን  ዕዉር ከመሪዉ እንደሚጣላ ፤ ለማኝ አኩፋዳዉን እንደሚጥል ሁሉ ብአዴን ከህዝብ እና ከአገር ጋር ጥል፤ ከዉስጥ እና ከዉጭ  ጠብቆ የሚታደገዉን ህዝብ መካድ ወይም መጣል መደጋገም ያሳዝናል ፡፡

“ሞት ለኢትዮጵያ ጠላት !”

“አንድነት ኃይል ነዉ ”

 

NEILOOSS-Amber

Leave a Reply

Your email address will not be published.