እኔዎች (እኔያት) – በላቸው ገላሁን

እኔዎች (እኔያት)

አንዱ እኔ ሲጠራኝ

አንዱ እኔ ሲልከኝ

ሌላው እኔ ሲጥለኝ

አንዱ እኔ ሲያነሳኝ፣

አንዱ ወደ ግራ

ያአንዱ ባለጋራ

አንዱ ወደ ደጅ

የሌላው ወዳጅ፣

ሌላኛው ወደ ቀኝ

ሌሎቹን እንዲዳኝ

አንደኛው ወደ ታች

ለራሱ ሊያመቻች፣

አንዱ ወደ ላይ

ሊነካ ሰማይ

አንደኛው ወደ ፊት

ሌሎቹ እንዳይቀድሙት

አንዱ ወደ ኋላ

ሊያጣራ ሊያብላላ፤

አቤት የእኔ መዓት የራሴ ብዛቱ

ለየቱ እንቢ ብዬ ልታዘዝ ለየቱ?

እኒህ ሁሉ እኔዎች ውስጤ ተከምረው

ሁሌ እየተጣሉ አልስማማ ብለው

አንድ እኔ ባተለ ፍዳውን ቆጠረ

ሌላው ኔ ደስ ብሎት ተኝቶ እያደረ።

                 በላቸው ገላሁን (ነሓሴ 1998)

                 (USA)

ተጨማሪ ያንብቡ:  መሞት ካልቀረልን* - አሁንገና ዓለማየሁ

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.