Comments on: በኢትዮጵያ ተፋላሚ ኃይሎች መካከል ይደረጋል ተብሎ ስለሚጠበቀው ድርድር የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመር ምን አሉ https://amharic-zehabesha.com/archives/177112 ዘ-ሐበሻ | Ethiopian News | የዕለቱ ዜና | ሰበር ዜና, ትኩስ የዕለቱ ዜና በአማርኛ, የኢትዮጵያ ዜና | ዜና ፖለቲካ ፣ አይቲ ዘ-ሐበሻ ሰበር ዜና ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ ሌሎች ብዙ አዳዲስ ዜናዎች| Fri, 23 Sep 2022 13:45:58 +0000 hourly 1 https://wordpress.org/?v=6.0.2 By: Tesfa https://amharic-zehabesha.com/archives/177112#comment-202218 Fri, 23 Sep 2022 13:45:58 +0000 https://amharic-zehabesha.com/?p=177112#comment-202218 ጦርነት የኋላ ቀርነት ምልክት ነው። ሰው ገድሎ አካኪ ዘራፍ በማለት የሚጨፍር የሰው እንስሳ የራሱን ሞት የረሳ ነው። አሁን በሰሜን ኢትዮጵያ ለተቀሰቀሰው ችግር ዋናው መንስኤ እኛው ነን። ሌላው ሁሉ አጨብጫቢና እሳት አቀባይ በሁለት ቢለዋ የሚበላ ራስ ተኮር የሆነ የውጭ ሃይል ስብስብ ነው። ትግራይ ትግራይ የሚሉት የዲያስፓራና ሃገር ውስጥ ያሉ የክፍለ ሃገሩ ተወላጆች ማየት ያለባቸው የትውልድን ማለቅ አብሮ መተላለቅ እንጂ ይህን ያህል ገደልን ያን ያህል ማረክን የሚባለውን የፈጠራ ወሬ መሆን የለበትም። መቼ ነው በትግራይ መሬት ጥይት የማይጮኸው? መቼ ነው የትግራይ እናቶች የወለዷቸውን ልጆች አሳድገው አስተምረው ለቁም ነገር ሲበቁ የሚያዪት? አይበቃም የ 50 እብደት? እንዴት ሰው በ 21 ኛው ዘመን ዘር ጠል የሆነ ሽኩቻ ውስጥ ገብቶ ደም ይፋሰሳል? ግን የባሩድ ሽታ ለሚናፍቃቸው የሩቅ አዋጊዎች አሁን እየሆነ ያለው ትውልድ ጨራሽ መሆኑ አልገባቸውም።
በቅርቡ ራሺያ ያለ የሌላትን ሰራዊት ለጦርነት ስትጠራ አባቱ ወደ ጦር ግንባር የሚሄድበት ህጻን አባ አባ እያለ እያለቀሰ ሲከተል ማየት መፈጠርን ያስጠላል። ስንቶች ናቸው በትግራይ መሬት፤ በአማራና በአፋር አባ አባ እማ እያሉ ያለቀሱት? የእነርሱን ለቅሶ ማን ይስማላቸው? አሁን የአሜሪካ ልኡካን መመላለስና በፊት ከነበራቸው የወያኔ ቋሚ ተወካይነት ለዘብ ማለት መልካም ቢሆንም በጭራሽ የአሜሪካን የውጭ ፓሊሲ እንዳለ መሰልቀጥ ቆይቶ ማወራረጃ ለማጣት ብቻ ነው። እልፍ ህዝብ ሲገደል፤ እልፍ ሃብት ሲዘረፍ ለ 27 ዓመ ት ጸጥ ያሉትና ኤርትራን ሰንገው የያዙት እነዚህ ሃይሎች አሁን ምን ታይቷቸው ነው አቋማቸው የተለሳለሰው? በምንስ ሂሳብ ነው ወደ አዲስ አበባ የሚመላለሱት? ሰላምን ፍለጋ? አይ ሰላም ሰላም ሁሉ ስሟን ይጠራል እንጂ እሷ በልባቸው የለችም። ያ ባይሆን እማ ለዪክሬን እልፍ መሳሪያ እያቀበሉ በሉ አይሉም ነበር። ግን አለም እንዲህ ነው። 1ኛና 2ኛው ጦርነት አሰላለፍንና ፍጻሜ ለተመለከተ አሁን እየሆነ ካለው ብዙ አይለይም። ባጭሩ የአሜሪካ ለሰላም መጣር የማይታመን ዝናብ የሌለው ደመና ነው።
መፍትሄው ያለው ከእኛ ከራሳችን ነው። መገዳደል ማቆም አስፈላጊ የሚሆነው ህዝብን ከከፋ መከራ ለማዳን ነው። ወያኔ ክረምትና አዲስ አመትን እየጠበቀ ጦርነት መክፈቱ የአውሬነቱን ባህሪ ያሳያል። ሰው እንዴት በሚያርስበት ጊዜ ለጦርነት ማገዶ ይሆናል። ግን ወያኔ ከጅምሩ ጀምሮ እውነተኛ የትግራይ ልጆችን አፈር ያለበሰ ድርጅት ነው። ለዚህም ነው የማፊያ ድርጅት ነው የምንለው። ግራም ነፈሰ ቀኝ የአሜሪካን የውጭ ፓሊሲ በፊት ለፊት የሚያደርገውና በጓዳ የሚፈጽመው የተለያዬ እንደሆነ ሰው ሊገባው ይገባል። በቃኝ!

]]>
By: ዳሹሬ https://amharic-zehabesha.com/archives/177112#comment-202214 Wed, 21 Sep 2022 21:05:08 +0000 https://amharic-zehabesha.com/?p=177112#comment-202214 የአምባሳደሩን ጥያቄና መልስ አዳምጨዋለሁ። በግሌ የአምባሳደሩ መልሶች ያልጠበኳቸውና የተገረምኩባቸው ናቸው። አሜሪካ የፖሊሲ ቅልበሳ አደረገች? ወይስ እኛ ዲፕሎማሲ እና እንግሊዝኛቸው በፊትም አልገባንም ነበር? ወይስ እነሱ የኛ እንግሊዝኛ አልገባቸውም ነበር? ብዬም አስብኩ። የአሜሪካ ፖሊሲ እሳቸው እንዳሉት ከሆነ ምን የሚያጣላ ነገር አለ? አሜሪካም በዚሁ ያዝልቃት፣ የኛ ሚዲያዎችም ፉከራችውን ገደብ ያብጁለት፤ ወያኔን በግልጽ ታውግዝልን ብለንም አንጠብቅ። በ60ዎቹ “ኢምፔሪያሊዝም ይውደም” ብለን ያላቅማችን ተንጠራርተን ነበር። የሚገርመው የብዙዎቻቺን መጨረሻ እነሱው ጋ ሆኖ አረፈው። በነገራችን ላይ በዲፕሎማሲው እንድንበለጥ ከሚያደርጉን ነገሮች አንዱ የባለስልጣኖቻችን/አምባሳደሮቻችን/ምሁራኖቻችን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ማነስ ነው ብዪ አምናለሁ። አይጋ ኒውስ ፎረም ላይ የሚወጡትን የእንግሊዝኛ ጽሁፎች ይዘታቸውን ማጣጣል ይቻላል፣ ዉበታቸውን አለማድነቅ ግን አይቻልም። አስባችሁታል? አንድ የጌታቸው ረዳን ያህል እንኳ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ያለው ሰው ቢኖረን፤ ወይም ደግሞ ወያኔ ጌቾ ባይኖራት ኖሮ ……..

]]>
By: sololboni https://amharic-zehabesha.com/archives/177112#comment-202213 Wed, 21 Sep 2022 19:40:34 +0000 https://amharic-zehabesha.com/?p=177112#comment-202213 አረ ኢትዮጵያዉያን ዝም አትበሉ ይሄ ሰውዬ ስራ የለውም እንዴ ምን አገባው? ወይስ ኢትዮጵያ የአሜሪካ 52ኛ ስቴት ሁናለች አሁንስ ቅጥ አጡ መንግስት ምነው ዞር በሉ ማለት አቃተው እንዲህ ያለ ነገር ከዚህ በፊት ታይቶ አይታወቅም ዶ/ር አብይን በጣም ናቁት፡፡

]]>