ጀ/ል ስብሃት ኤፍሬም ፤ የአሁኑስ ፕሮፓጋንዳ  ” ለትግሉ ውጤታማነት ሲባል — ” ቢሆንስ? (ፊልጶስ)

የቀድሞው የኤሪትሪያ መከላከያ የአሁኑ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር ጀ/ል ስብሃት ኤፍሬም   በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተናገሩት የተባለው የብዙሃን መገናኛ  የሰሞኑ ወሬ ነበር። የንግግራቸው ዋና ነጥብ የሚከተለው መልዕክታቸው ነው።

”—-ከጥንት ጀምሮ በኢትዮዽያ መቀጠል የማያወላውል አቋም አለው’ ተብሎ ከሚታመንባቸው ብሔሮች መካከል ግንባር ቀደሙ «የአማራ» ብሔር ነው። ከነፃነት ኤርትራ በፊት በትጥቅ ትግሉ ወቅት ‘’የአማራ’’ ብሄር አባል የሆነ ወይም በእናቱ ወይም በአባቱ የአማራ ዘር ያለበት ኤርትራዊ ሳይቀር የኤርትራን ከኢትዮዽያ መለየት ፈፅሞ የማይቀበለው መሆኑን ስለተገነዘብን ለትግሉ ውጤታማነት ሲባል በአማራ ህዝብ ላይ ብዙ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ሰርተናል። በወቅቱ ትግሉን ውጤታማ ከደረጉልን ቁልፍ ስልቶች መካከል አንዱ ነበር።”

ጀ/ል ስብሃት ኤፍሬም   እስቲ ልጠይቀዎት፤ “የአሁንስ ፕሮፓጋንዳዎት ለትግሉ ውጤታማነት ሲባል  አይደለምን?” በማንኛውም ህዝብ ላይ በማንንቱ ላይ የሚደረግ የሃሰት ፓሮፓጋንዳም ሆነ የጥላቻ  ቅስቀሰ እንደ ዘር ማጥፋት ወንጀል  እንደሚቆጠር ዘንግተውት ነውን?

የ’ናንተ የሃሰት ፓሮፓጋንዳ እኮ ነው ዛሬ አገራችን ካለችበት የህልውና ጥያቄ ውስጥ የከተታት። ችግሩ ”የቆፈራችሁት ጉድጓድ ” እናንተም ልትገቡበት መሆኑ ነው::

የጀ/ል ስብሃት ኤፍሬም   ንግግር አዲስ አይደለም።  ከዚህ በፊትም  ፕ/ር በረከት ሃብተ ሥላሴ የተባሉ  ሻአቢያን በተባበሩት መንግሥታት ወከለውና በተለያየ ከፍተኛ የሥልጣና ‘ርከን ውስጥ ሲገለግሉ ቆይተው፣ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተኳርፍው በአሁኑ ሰዓት  በጦረታ ላይ  ይገኛሉ። ታዲያ ‘’ሪዮት’’ የተባላ  የግዜው የወያኔ የውስጥ  ሚዲያ ከአራት ዓመት በፊት ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸው ነበር። ሰውየው  ኤርትራ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ ይወለዱ እንጅ ፤ ከልጅነታቸው ጀምሮ  በመሃል አገር የኖሩ ናቸው። የኃይለሥላሴ መንግሥት  ወደ ሎንደን ልኮ ያስተማራቸው ሲሆን ፣ በዓጼው ዘመን ከፍርድ ሚኒስተርነት እስከ  የኢትዮጵያ ጠቅላይ አቃቢ- ህግ ሊቀ-መንበርነት ያገለገሉና የተከበሩ ነበሩ።  ደርግ ወደ ሥልጣን ሲወጣ 1967  ሻአቢያን ተቀላቀሉ። ‘’ሪዮት ‘’ ሚዲያ የጠየቃቸው ” ‘ርስዎ ከልጅነት እስከ እውቀት በኢትዮጵያ ምድር የተማሩና የኖሩ፤ ስልጣንንም ከንጉሱ በታች የሆነውን ሁሉ እያፈራረቁ ይዘው የነብሩ ሰው፤  እንዴት ኢትዮጵያዊነተዎትን ክደው፤ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ብለው ለኤርትራ መገንጠል አስከ ”ርጅናዎ ድረስ ሰሩ?  በርግጥ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ማለት ይቻለዎታል ወይ? ምንም ይሁን ምንም ፤ ኤርትራስ የኢትዮጵ አካል አይደልችም ወይ?” የሚል ነበር።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Video: ኢትዮጵያን ዛሬም ያለቅሳሉ

የፕ/ር በረከት መልስ አንደ አሁኑ እንደ ጀ/ል ስብሃት ኤፍሬም   ንግግር  ሁሉ ” ኤርትራን ለመገንጠል ኢትዮጵያዊነቴን  መካድ ነበረብኝ፡ ኤርትራንም የኢትዮጵያ አካል አይደለችም ማለት ነበረብን።” ነበር ያሉት።

ኢትዮጵያን ለማደካምም ሆነ ለማፍረስና የባህር በር ለማሳጣት የሃሰት ፓሮፓጋንዳው  በ’ርግጥ ራስን በመካድ ”ኢትዮጵያዊ አይደለንም” ከሚል  ጀምሮ  የሃሰት ክህደቱ አይሰፋና ስር እየሰደደ ”እኛም ኢትዮጵያዊነታችን ክደናልና እናንተም ካዱ”   ተብሎ፤ ይኽን ለመስፈጸም ደግሞ ” አማራ” የተባለውን ህዝብ  ማጥፋት ለወያኔ ብሎም ለኦነግ  (ለኦሮሞ ነጻነት ግንባር) ያስተማረው ማን ሆነና?  ወያኔስ  የ’ናንተን የሻቢያዎችን ፓሮፓጋንዳ ተቀብሎ ‘ ታላቋን ትግራይ ” ለመመስረት  ለኦህዴድና ደቡብ ህዝብ ብሎም ኢህዲን (የኢትዮጵያ ህዝባዊ  ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ)  የሚባል ድርጅት ፈጥሮ  በአማራ ህዝብ ላይ ብሎም በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ  እስከ ዚች ሰዓት ድርስ የመከራ ኑሮ እንዲገፋና ከጦርነት አዙሪት እንዳይወጣ ያደረገው ማነው?

‘ርግጥ ነው፤  ለእናንተ ሻአቢያዎችም ቢሆን ” በአማራ” ህዝብ ላይ የጥላቻና  ኢትዮጵያን የማጥፋት ሴራ  ያስተማራችሁ  የእውነተኛ አባቶቻችሁ ” ኢትዮጵያ ወይና ሞት” ብለው የተጋደሉትን አባቶቻችሁን ያስከዳችሁ፡ የጣሊያንና እንግሊዝ አስተምሮትና ሴራ  ነው።  ኤርትራን መገንጠልም ሆነ ኢትዮጵያን ማፍረስ የ’ናንተ ሃሳብና ፍላጎት  እንዳልነበር፤  አሁንም  በተግባር  የከበቡን የጋራ ጠላቶቻችንና የምናካሄደው ጦርነት ምስክር ናቸው።  ለዚህም ነበር መሬቱ ይቅለለውና ደራሲ በዓሉ ግርማ ” ሻአቢያ ጭቅላቱ ውጭ ፣ እግሩ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።” ያለው ።

ለቀባሪ ማርዳት ባይሆንብኝ ግራዚያን ለሙሰለኒ የጻፈውን ደብዳቤ  ላስታውስ፤ …

” ለእኛ ለጣሊያኖች  ኢትዮጵያን እዳንገዛ የሚዋጉንና አሻፈረኝ ያሉ ፣

1/ ምሁራን —— ልብ ካለን፤ እንደ አሁኑ ምሁር ዘር የለውም፡፡ እንደ አሁኑ በገንዝብ የተሸመተ የምስክር ወረቀት የለውም። እንደ አሁኑ በጎሳ ኮታ ዮኒቨርስቲ የሚገባ አይደለም።

2/አማራ —–ልብ ካለን፤ ወያኔ  ኢትዮጵያን ለመበታተንና ርስ- በርስ  አባልቶ ታላቋን ትግራይ ለመመስረት  የፈጠረውን  ስምን ክልል ሳንቀበል ፣ በዘመኑ  አልገዛም ያለና  መንግሥታዊ አስተዳደር ላይ ያለው ሁሉ ዜጋ አማራ ነው።

3/ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት—– ልብ አናድርግ፤ አንድ ሰው ምንም ዓይነት ዕምነት ቢኖርው  በኢትዮጵያዊነቱና በአንድነቱ  የማይደራደር ከሆነ  ”ኦርቶዶክሳዊ” ይባላል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የመስቀል በዓል በጉራጌዎች ዘንድ - ከቅዱስ ሃብት በላቸው (ከአውስትራሊያ) [ጋዜጠኛ]

ታዲያ ከላይ ግራዚያን  በጠላትነት የፈረጃቸውን፣ ጣሊያን ያልተሳካለትን፤ በመጀመሪያ በተግባር ያዋለውና ያሳካከው፤  ሻአቢያ ኤርትራን በመገንጠል  ሲሆን፤  አሁንም የኢትዮጵያን ህዝብ ቁም ስቅል እያሳየና  እየተተገበረ  ያለው በበኩር ልጁ  ወያኔ፣ ቀጥሎም  ኦነግና ተረኛው ኦህዲዳዊ -ብልጽግና እየተፈራረቁ ነው።

አሁንም  እንደተለመደው በኢትዮጵያ ህዝብ መካከል  የመከፋፈልና የክህደት ስራ እየተሰራ ነው። እኛም ለምንና እንዴት ብለን ሳንጠይቅ  በብዙሃን መገናኛ እየተቀባበልን እናራግበዋለን።

አማራ ብቻ የኤርትራን መገንጠል እንደ ማይደግፍ  ተደርጎ የሚነዛው ፤ የተለመደው የጣሊያኖችና የእንግሊዞች መርዛማ ከፋፍለህ ግዛው አስተም’ሮ  ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ ከኤርትራዊ ወገኑን እንዳይለያይ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ፡ ከመሃል እስከ ዳር ያለው ሁሉ፡ ጎሳና ሃይማኖት ሳይለየው መሰዋትነት ክፍሏል።  ‘ጅልም እንባል የዋህ—” አሁንም የኔ ብጤዎች   በገዥዎቻችን እንጂ፤ በኤርትራና በኢትዮጵያ ህዝብ መሃከል ልዮነት የለንም። አንድ ቀንም አንደ አንድ ህዝብና እንደ አንድ አገር በአንድነት የምንቆምበት ቀን ይመጣል። ማን ያውቃል? የትላንት አያቶቻችንና አባቶቻችን አንድነትን በተግባር  አሳይተውናል።

”ኢሳያስ አፈውርቂ እ’ኮ ኢትዮጵያን ይወዳል ፤ አንድነቷንም ይፈልጋል፤ ወያኔ ነው እንጅ፡” የምትለዋ ፓሮፓጋንዳ የመጣችው በወያኔ ዘመን ”ግንቦት ሰባት” አሰመራ በከተመበት ግዜ ፤ በኢሳት ጋዜጦኞች  የተነዛ ወሬ ነው። አንድነት በተግባር እንጅ በወሬ አለመሆኑን በዚያ ሰዓት እንኳን በኤርትራ ምድር ወያኔን ሳይሆን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የመገንጠል አጅንዳ  አንግበው የሚታገሉ  እንደ ኦነግ፣ ኦጋዴን ነጻ አውጭ ፣ የጋምቤላ ነጻ አውጭ ፣ ወዘት በሻአቢያ መንግሥት የሚረዱና የሚታጠቁ ነበሩ። ወያኔና ሻአቢያ ኦኮ ጦርነት የገቡትና ለዚህ የበቁት  ”ሌባ ሲከፋፈል እንጅ፣ ሲሰርቅ አይጣላም።” እንደሚባለው ሆኖ እንጂ፤  እንደምንሰማው በጫጉላ ግዜያቸው ” በአንድ ሳንባ  እንዳንተነፍስ ያደረገን አማራ ነበር” እያሉ  ሲመጻዳቁ  ተሰምተውል። ”ለኢትዮጵያዊያንም የመቶ ዓመት የቤት ሥራ ሰተናቸዋል እንደተባለው፤ ይኽው አሁንም ”የቤት ሥራውን እየሰራን ነው

‘’ኤርትራ  አገር ሆና እታውቅም፤  ህዝቡም  የኢትዮጵያ አካል ነው። ከሁሉም በላይ  የህዝቡ እጣ-ፋንታ  እንደ ትላንቱ ሁሉ ዛሬም ሆነ ወደፊት የተሳሰረ ነውና፤ ላለፈው ይቅር ተባበለን  በአንድነት (‘’የፈረሰው ፌደሬሽን  በመመለስ’’) ልንኖርበት የምንችልበትን ሥርዓት እንመስርት።”’ ስንል እንኳን የሚሰጠን መልስ 30 ዓመት ተዋግተናል የሚል ነው። አንዳንዴም እኛ ያለ ኤርትራ ወግኖቻችን መኖር እንደማንችል ተቆጥሮ እንደ ጅል” እንታያለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወደለውጥ የማያመራው የትግላችን ጉዞ መሰናክሎች!

አኣምሮ ላለው ግን ኢትዮጵያዊያን ከኤርትራዊ ወግኖቻችን  ጋር ለአለፋት ሺ ኣመታት የቀይባህርን ጠረፍን  የህዝቡን ደህንነት ለማስጠበቅና  ለማስከበር፤ ምን አልባትም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ  ዜጎቻችን ደማቸውን   በጋራ  አፍሰሰዋል፤ አጥታቸውን  በጋራ ከስክሰውል።

ሃኒሽና በአካባቢዋ ያሉ ደሴቶች ለየመን ሲሰጡ፤  ከሻአቢያዊን የበለጠ ብዙዎቻችን አዝነናል። ልባችን ደምቷል፡ ምክንያቱ  ደሴቶቹን ለማስጠብቅ ዘመናት ሙሉ ኢትዮጵያዊያኖች ብዙ መሰዋት ከፍለውባታልና። የወገኖቻችን አጥትና ደም በነዚያ  ደሴቶች ላይ አለና።

በዚህ ጹሁፋ ”የማትደሰቱ ወይም አሁን ግዜው አይደለም ” የምትሉ ልትኖሩ  ትችላላችሁ። ይሁን እንጅ  ትላንትም ሆነ ዛሬ፤  የሚማር ጠፍቶ እንጅ ታሪክ የሚያስተምረን፤ የራሱ መርህና ግብ የሌለው ጥገኛ ትግል የትም አይደረስም። አሁንም  የሚከፈለው መሰዋአትነት ለድል የሚበቃውና ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን መታደግ የምንችለው፤ ከመንደርተኝነትና ከጎሰኝነት ወ’ተን  በራስ በመተማመንና  ኢትዮጵያዊ መሪ ድርጅት በመፈጠር፣ ራስን በመሆን፣ ብሎም ትክክለኛውን የውስጥና የውጭ  ጠላት መለየት ሲቻልና  ህዝብን በአንድነት አሰባስቦ ታግሎ-ማታገል ከተቻለ ብቻ  ነው።

በ’ርግጥ አሁንም የሻአቢያ ገዥዎች በየግዜው እየተነሱ ” ለትግሉ ውጤታማነት ሲባል በአማራ ህዝብ ላይ ብዙ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ሰርተናል።” ከማለት ይልቅ፤  በእውነት – ለእውነት ቅንንቱና ፍላጎቱ ካለ ፤ የህዝብ፣ ስደት፡ ድህነትና ብስቁልና፤ ብሎም ወጣቱ በየግዜው በጦርነት እየተማገደ ከሚያልቅ፤  የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ ‘ተለያይቶ -የማይለያይ” ነውና፤  ወደ አንድነት የሚመጣበትን፤ ተከባብሮ  በጋራ  ሊያግባባውና ሊበልጽግ  የሚችልበትን ሥርዓት-መንግስት  በሚመሰርትበት ላይ ቢሰራ፤ ሁሉም ተጠቃሚ መሆን ይችላል።  አሁን  ኢትዮጵያ ያለችበት የወያኔ ጦርነትም ሆነ ኤርትራ የተደቀነባት ችግር ግልጽ ያደረገው ነገር ቢኖር፤ ” ”ኢትዮጵያ ስትስል፤ ኤርትራ ማነጠሷን፡ ኤርትራ ስትስል፣ ኢትዮጵያ ማነጠሷን” እና ግማዳችን የተሳሰር ብቻ ሳይሆን፤  ከአሰፈሰፋትም የውጭ ጠላቶች መንግጋ መውጣት  የምንችለው በአንድነት  ስንቆምና ስንታገላቸው ብቻ ነው።

እግዚአብሔር ለገዥዎቻችን ልቦና ሰጥቶና በአገራችን  ሰላም ወርዶ በአንድነት ለመኖር ያብቃን።

 

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!!

——//—–ፊልጶስ

E-mail: [email protected]

መስከረም -2015

 

3 Comments

  1. The writer of this comment is the TPLF agent or supporter because he tries to inject divisive poison. The TPLF does everything to sabotage and undermine the improved relations between Ethiopia and Eritrea. As of late Eritrea has been the propaganda target of the TPLF. In clear contradiction to the TPLF, the Eritreans have apologized. The TPLF still targets the Amhara people as its sworn in enemies and killing them.

  2. STOP this old nonsense!
    Eritrea is an Independent and Sovereign Nation and a UN member State.
    Contrary to the old fake propaganda, ERITREA is slso one of the RICHEST countries under the Sun
    Gen Sibhat Efrem is back on active Duty as the Minister of Energy?
    I wush.
    Insh’Allah

  3. What happen you muddled head Eritreans. Is that how u understand independence? Afeworki is pure Tegrea and u r fully conolized by tegreas. Simply accept your subjugation, if it was to your need u would have kicked away Afeworki and replaced him by Eritreans, sadly the tegreas didnt allow that to happen.

Leave a Reply

Your email address will not be published.