Comments on: ከስሜታዊና ከሆይሆታ  “ትግል” እንውጣ!!! – ፊልጶስ https://amharic-zehabesha.com/archives/177138 ዘ-ሐበሻ | Ethiopian News | የዕለቱ ዜና | ሰበር ዜና, ትኩስ የዕለቱ ዜና በአማርኛ, የኢትዮጵያ ዜና | ዜና ፖለቲካ ፣ አይቲ ዘ-ሐበሻ ሰበር ዜና ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ ሌሎች ብዙ አዳዲስ ዜናዎች| Sat, 24 Sep 2022 14:41:31 +0000 hourly 1 https://wordpress.org/?v=6.0.2 By: Tesfa https://amharic-zehabesha.com/archives/177138#comment-202221 Sat, 24 Sep 2022 14:41:31 +0000 https://amharic-zehabesha.com/?p=177138#comment-202221 ችግሩ ለምድሪቱ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ የሰው ሃይል ማጣት አይደለም። ግን እኛ እየሞትን እነማን እየኖሩ ነው? በእኛ ደም ላይ ማን በለጠገና ተመነደገ ለሚሉት ጥያቄዎች መፍትሄ መጥፋቱ ነው። ዘንተ ዓለም በሃገርና በአንድነት ስም እልፍ የሃገሪቱ ልጆች ረግፈዋል። ዛሬም እየረገፉ ነው። በዚህ ሳቢያ ወላጅ አጥተው መንገድ የወደቁ ቤተሰቦች እልፍ ናቸው። እርግጥ ነው ስሜታዊ ሆኖ እውነትን ማየት አይቻልም። ለነገሩ ረጋ ተብሎም በእኛ ሃገር እውነትን ፍለጋ የተሰማሩ ጦማሪዎች፤ ጋዜጠኞችና ከያኔዎች ከዘብጥያ እስከ መሰወር ከዚያም ባለፈ እስከ ሞት ተዳርገዋል? ለመሆኑ የምድሪቱ ሰው በአማካኝ የሚኖረው እድሜ ስንት ሆነና ነው ሁሌ የምንራኮተው? ግን አውራ ጣት ከአመልካች እጣት ትበልጣለች ብሎ ለሚከራከር የዘርና የጎሳ እንዲሁም የቋንቋ ሰካራም ዶክተር ሆነ ፕሮፌሰር እውነትን ማሳየት አይቻልም። ረጋ ብሎ ላሰበ የሃበሻው ፓለቲካ ማጥ ውስጥ እንደ ተወሸቀ የመኪና ጎማ ሊወጣ በተሽከረከረ ቁጥር የራሱን ጉድጓድ እየቆፈረና በዙሪያው ሊያወጡት የሚታገሉትን ሰዎች ጭቃ እየቀባ እንደሚዘቅጥ አይነት ነው። መላቢስ፤ ጥላየለሽ፤ ሁሉን ቀርጣፊ ፓለቲካ! አታድርስ ነው። ዛሬ የሚርመሰመሱት የፓለቲካ ጊዜ ሰጦች ሳያስቡት ይቀነጠሳሉ፤ ሰካራም እንደ ረገጠው ጣሳ ይጨራመታሉ። በታሪክ ያየነው ይህን ነው። ሌላው የተራበና ጊዜ ያነሳው ይሰባሰብና ማታለያና መላሾ ይዞ መሰሉን እያስከተለ በተራው ደግሞ ዘርፎና ገድሎ ይከስማል። ታሪካችን ባጭሩ ይህን ይመስላል። በፊውዳሉ ዘመን ስለሆነው ጉዳይ ለመረዳት የዳኛቸው ወርቁ አደፍርስን፤ የአቤ ጉበኛን አልወለድም መጽሃፍቶች ማገላበጡ ጊዜው ልክ እንደዛሬው ግፍ አይፈሬ መሆኑን ያሳያል። የደርጉን ለቋሚ እስከ አሁንም ከነጠባሳቸው ላሉ የዘመኑ የፈተላ ፓለቲከኞች እተወዋለሁ። ከዚያ በህዋላ በወያኔ የሆነው በሃገሪቱ ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ የአውሬ ሥራ በመሆኑና እየሆነም ስለሆነ አይን ያለው ያያል፤ ጀሮ ያለው ይሰማል። ባጭሩ ፓለቲካችን የመገዳደል ፓለቲካ ነው። አሁን እምናየው እንዘጥ እንዘጥም ቢረግብ ወይም ቢገታ ሌላ የሚያፋጀን ፈልገን መፋለማችን አይቀሬ ነው። የምድሪቱ ችግር እትየ ለሌ ነው። በመግደል፤ በማሰር፤ በማፈን የሚያምን መንግስት ቢዘገይም በሰፈረበት መስፈሪያ መሰፈሩ አይቀርም።
አሁን እንሆ የራሻው መሪ የኒኩለር መሳሪያ ሳይቀር እጠቀማለሁ እስከ ማለት ደርሷል፡ አይሆንም አይደረግም አያደርጉትም የምትሉ ሁሉ ሂሮሽማና ናካሳኪ ላይ የተደረገውን የማታውቁ ናችሁ። ግን በእርግ የራሺያው መሪ እንዲያ ካደረገ ጀርመን፤ ጃፓን በሁለተኛው ዓለም ማለቂያ ላይ የገቡትን ቃል በመጣስ እነርሱም በጥቂት ወራታት ውስጥ ኒኩለየር ይታጠቃሉ። ይህ ክስተት ደግሞ ሌሎችን ያነቃቃል ዛሬም ጅራት ለሆነው የአፍሪቃ አሃጉር ደግሞ ሌላ ስጋትን ይጭራል። የዳግም ቀኝ ተገዥነትን መከራ!
ስለዚህ በትግራይና በአፋር፤ በወለጋና በሌሎችም የሃበሻ ምድር ወንድምና እህቱን እያረደ ዘራፍ የሚለው የእንስሳ ጥርቅም ሁሉ እንደ ቄራ ከብት በየተራ የሚታረድ እንጂ አንድ ተረግጦና ተዘርፎ ሌላው በእፎይታ የሚኖርበት ምንም አይነት ሂሳብ አይኖርም። በውጭና በሃገር ውስጥ የኢንተርኔት የፈጠራ ወሬ በመንዛት የሳንቲም ሽርፍራፊ የሚለቃቅሙት ሁሉ በግንባር እጅን አንስቶ ማሩኝ የሚለውን ከሚረሽኑት ጨካኝ ሰዎች ተለይተው መታየት የለባቸውም። እንዴት ሰው በውሸት በወንድምና በእህቱ ሞት እልል እያለ ሳንቲም ይሰበስባል? በዚህ የተገኘው እንጀራስ ጤና ይሆናል? ግን ደንዝዘናል። ዘርፎ፤ አታሎ፤ ገድሎ መኖር መኖር እየመሰለን ተላምደነዋል። ስናሳዝን። የማያስቧርቀው ሲያስቧርቀን እድሜአችን የሃሰት ካባ እንደለበሰ አፈር ሆኖ አፈር መመለስ። ክራራይሶ ያሰኛል የሚሰማ ካለ። በቃኝ!

]]>