የብአዴን ጉዶች – መስፍን አረጋ

ያማራ ሕጻናት ቶሌ እየታረዱ
የብአዴን ጉዶች ቦሌ ሲቀልዱ፣
አማራ ካለፈ ዐይቶ አንዳላየ
ከሞቱት ሕጻናት በምኑ ተለየ?

ያማራ እናቶች ደረት እየመቱ
ደመቀና ግርማ ሻምፓኝ ከፈቱ፡፡
እንዲህ ያለ ውርደት እያዩ እየሰሙ
ኑሬያሉ ከማለት ሞት በስንት ጣሙ?

ባለፈው በወያኔ ዘመን መለስ ዜናዊ የብአዴን አባሎችን ይመለምል የነበረው በስም ብቻ ኣማራ የሆኑትን ወይም ደግሞ እሱ ራሱ አማራዊ ስም የሰጣቸውንየአማራ ጥላቻቸው ከራሱ ከመለስ ዜናዊ በላይ የሆነውን ጉዶች ሥራየ ብሎ በማሾ እየፈለገ ነበር፡፡  ለዚህ ደግሞ አዲሱ ለገሰተፈራ ዋልዋና ከበዴ ጫኔ ተጠቃሽ ምሳሌወች ናቸው፡፡

ባሁኑ በኦነግ ዘመን ደግሞ ጭራቅ አሕመድ ያስተማሪውን የመለስ ዜናዊን ተግባር ከመለስ ዜናዊ በበለጠ ሁኔታ እየተገበረው ይገኛል፣ ከመምሕሩ ደቀመዝሙሩ እንዲሉ፡፡  ባሁኑ በኦነግ ዘመን ጭራቅ አሕመድ ስልጣን የሚሰጣቸው ደመቀ መኮንንንተመስገን ጡሩነህን፣ ሰማ ጥሩነህን፣ አበባው ታደሰን፣ ግርማ የሽጥላንና እነሱን የመሳሰሉትን ቆንጆ አማራዊ ስም ቢኖራቸውም የአማራ ጥላቻቸው ግን ከራሱ ከጭራቅ አሕመድ የባሰውን ጉዶች ነው፡፡

መለስ ዜናዊን እንቅልፍ ይነሳው የነበረው የኦሮሞ ብሔርተኝነት ሳይሆን የአማራ ብሔርተኝነት ነበር፡፡  ማናቸውም የኦፒዲኦ አባል የፈለገውን ያህል ኦነጋዊ ቢሆንም መለስ ዜናዊ ግን ኦነጋዊነቱን ዐይቶ እንዳላየ ያልፍለት ነበር፡፡  ለዚህ ደግሞ አፒዲኦ ሲገልጡት ኦነግ ነው በማለት በይፋ መናገሩ በቂ ምስክር ነው፡፡ በሌላ በኩል ግን ማናቸውም የብአዴን አባል የሰናፍጭ ቅንጣት የምታህል አማራዊነት የሚሰማው ሆኖ ሲያገኘው ሳይውል ሳያድር ያስገድለው ነበር፡፡ የብአዴኑን ሙሉዓለምን ያስገደለውም በዚሁ ቋሚ መመርያው መሠረት ነበር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለአማራ አይመጥንም ዘፋኞች ሆይ! ለአማራ እማይመጥነው በአገሩ እንደ ደን መጨፍጨፍና ስደተኛ መሆን ነው!

ጭራቅ አሕመድንም ልክ እንደ ጡት አባቱ እንደ መለስ ዜናዊ እንቅልፍ እየነሳው ያለው የትግሬ ብሔርተኝነት ሳይሆን የአማራ ብሔርተኝነት ነው፡፡  የትግሬ ብሔርተኛው ባይቶና የጠነክረውን ያህል ቢጠነክር፣ ወታደራዊ ክንፉ ሳምሪ ደግሞ እስካፍንጫው ቢታጠቅ ለጭራቅ አሕመድ ግድ ስለማይሰጠው ስማቸውን እንኳን አንስቶ አያውቅም፡፡  በሌላ በኩል ግን በቅጥረኛው በቀለጠ ሞላ አማካኝነት አብንን የኦነግ ቅጥቅጥ ለማድረግ፣ በብአዴናዊ አስመሳይ ፋኖወች አካማኝነት ደግሞ እውነተኛውን ፋኖን ለማጥፋት የማይቆፍረው ዲንጋ የለም፡፡

መለስ ዜናዊ አማራዊነት ስሜት ይሰማቸው የነበሩትን የብአዴን አባሎች እያፈነፈነ በማግኘት፣ ይቺ ባቄላ ካደረች እትቆረጠምም በሚል ስሜት ወዲያውኑ ያስገደላቸው እንደነበረ ሁሉ፣ ጭራቅ አሕመድም እነ ዶክተር አምባቸውንና ጀነራል አሳምነውን የገደላቸው በዚሁ መሠረት ነበር፡፡  መለስ ዜናዊን ቀጥ አድርጎ ይዞት የነበረው ወያኔ ሳይሆን በአዲሱ ለገሰ ይመራ የነበረው ብአዴን የሚባለው የጉዶች ስብስብ እንደነበረ ሁሉ፣ ጭራቅ አሕመድንም ቀጥ አድርጎ የያዘው ኦነግ ሳይሆን በደመቀ መኮንን የሚመራው ይሄው የጉዶች ስብስብ ነው፡፡

ጭራቅ አሕመድ የአማራን ሥጋ በልቶ የማይጠረቃ ኦነጋዊ አውሬ ቢሆንም፣ የአማራን ሥጋ የሚዘነጣጥልባቸው ጥርሶቹ ግን ሙሉ በሙሉ ብአዴኖች ናቸው፡፡  በተለይም ደግሞ የጭራቅ አሕመድ ክራንቻወች (ማለትም ረዝመው ያገጠጡት ሁለቱ የፊት ጥርሶቹ፣ canines) ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጡሩነህ ናቸው፡፡  በመሆናቸውም፣ ጭራቅ አሕመድ የአማራን ሕዝብ መብላት አቅቶት፣ የሰው ሥጋ ጠኔ ናላውን አዙሮት፣ ራሱን ስቶ እንዲወድቅ ብአዴናዊ ጥርሶቹን ማርገፍ የግድ ነው፡፡  ይልቁንም ደግሞ መንጋጋወቹን እነ ግርማ የሽጥላን እና ሰማ ጡሩነህን መንቀል፣ ክራንቻወቹን ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጡሩነህን መመንገል ይዋል ይደር የማይባል ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይህ ስርዓት በፍጹም አይድንም

የየቀበሌው የደመላሽ ፋኖ ዋና ሚና መሆን ያለበት ደግሞ በየራሱ ቀበሌ ላይ የተተከሉትን የጭራቅ አሕመድን ብአዴናዊ ጥርሶች መንቀል፣ መመንገል፣ ማፍለስ ማወላለቅ ነው፡፡  የዘመነ ካሴ አረጋዊ እናት ሙሾ እያወረዱ፣ የደመቀ መኮንን ቤተሰቦች ውስኪ ሊቀዱ አይገባም፡፡  ነውር፣ የነውር ነውር ነው፡፡  ይህን ነውር አይቶ እንዳላየ የሚያልፍ አማራ ደግሞ ከደመቀ ቤተሰቦች በላይ ነውረኛ ነው፡፡

የአማራ ሕዝብ ደመቀ መኮንንንተመስገን ጡሩነህን፣ ሰማ ጡሩነህንግርማ የሽጥላን፣ አበባው ታደሰንና የመሳሰሉትን የበላኤ አማራውን የጭራቅ አሕመድን ብአዴናዊ ጥርሶች በማወላለቅ ጭራቅ አሕመድን ጨርቅ ካደረገ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡

መስፍን አረጋ

[email protected]

 

1 Comment

 1. አብይ አህመድኮ በአማራው ላይ የተከላቸውን የአማራ ሆዳም ምርኩዞቹን አማራው ከያሉበትት ነቃቅሎ ቢያስወግዳቸው ጭራቁ የኦሮሙማው ቁንጮ አብይ አህመድ አሊ ምርኩዝ አይኖረውም፡፡ ከዚያ በኋላ ጭራቁ አብይ አህመድ አማራ ክልል ውስጥ እንደፈለገ እያዘዘና “ግደሉ፣ እሰሩ” እያለ የሚያሽከረክራቸው ምርኩዞች ስለማይኖሩት አማራው እነዚህን የጭራቁን ምርኩዞች ከክልሉ ጠራርጎ ማስወገዱ ለነጻነቱ የሚያካሂደውን የትግል ጉዞ የሰመረ ያደርግለታል፡፡ አማራው አንዴ ክልሉን ከሆዳሞች ነጻ ካደረገ ራሱን በራሱ እያደራጀና ራሱን በራሱ እያስተዳደረ ለአገር አቀፉ እውነተኛ ፌደራላዊ ስርአት መመስረት የራሱን ድርሻ መወጣት ቻለ ማለትም ነው፡፡
  እንድገመው፡፡ ለዚህ ሁሉ ስኬት መጀመሪያ አማራው በአሁኑ ስአት እጅግ አስችኳይና አንገብጋቢ የሆነውን ክልሉን ከአብይ አህመድ ምስለኔወች ማጽዳቱ ነው፡፡
  በፌደራል ደረጃ ላይ ተሰቅለው ያሉትን ሆዳሞች ማስወገዱ ለምሳሌ ያህል ደመቀ መኮንን፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ አኘኘሁ ተሻገር፣በለጠ ሞላ ወዘተ ለጊዜው አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፤ ከክልሉ አስተዳዳሪ ተብየው ጀምሮ በክልሉ ውስጥ ያሉትን እንደ ግርማ የሽጥላ የመሳሰሉትን ነቀርሳውችንና የአብይ አህመድ ምሰለኔወችን በያሉበት እያደቡና ምላጭ እየሳቡ ማስወገዱና መቀጣጫ ማድረጉ ግን በአማራው እጅ ያለና አማራው ሊያደርገው የሚችለው ጉዳይ ነው፡፡
  ለዚህ የሚያስፈልገው በየጎበዝ አለቃ በምስጢር መደራጀት፣ መታጠቅና በህቡእ ህዝቡን ውስጥ ውስጡን ቀድሞ ማንቃት ብቻ ነው፡፤ ከ40ና 50 አመታት በላይ በአማራ ላይ የተሰራው አማራን ዳፍንት አድርጎ ያቆየው አገዛዝ ከዚህ በኋላ መቆም አለበት፡፡ በእርግጥ አንድ የማይካድ እውነታ አለ፡፡ አማራው አሁንም የበሰለ አመራርና አደረጃጀት ስልትና ስታርቴጅ በአማራነት የተቃኘ የፖለቲካ የአስተሳሰብና የራእይ ችግር አለበት፡፡ይህ ችግር መልስ የሚያገኝበት ወቅት ደግሞ አሁን ነው፡፡ ይህንኑ ለመቅረፍም የሚያግዝ ሰፊ ስራ አሁን ተጀምሯል፡፡
  የነ ጀኔራል ስምነው ጽጌ አስተሳሰቦችና ራሱ የጄኤራሉ መስዋትነት በቅርቡ ደግሞ በአርበኛ ዘመነ ካሴ ላይ የተሰራው “ድራማ” ብዙውን አማራ አንቅቶታል፣ አስተምሮታል፣ አነሳስቶታልም፡፡ ይህ ትኩስ እንቅስቃሴ ፋኖን በመሰሉ በትክክልና በሀቀኛ አማራ ሀይሎች እየታገዘ በበሰለ “አዲስ” አማራዊ የፖለቲካ ”ቅኝት” ከተቃኘ እንደቋያ በመላው አማራ ክልል በመሰራጨት ምስለኔወቹን ከመንቀሉ ጎን ለጎን ትግሉን ወደ ነጻ የህዝብ አመጽ በቀላሉ ማሸጋገር ይቻላል፡፡
  በጥቅሉ የትግሉን መነሻ ሆዳሞቹን ማስወገድን “ሀ” ብለን ልንጠራው እንችላለን፡፡ ታሪክን ማስመለስን “ለ” ብለን ለይተን ልንጠራው የምንችል ሲሆን አማራው በኢትዮጵያ ውስጥ የትም ቦታ በአማራነቱ ኮርቶ ማንነቱን አስክከብሮ በነጻነት መኖር እንዲችል ማድረግና ከለሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በእኩልነትና በመከባበር እንዲኖር ማስቻልን ዋና አላማው ያደረገ ወስኝ የፖለቲካ ግብ አድርገን ልንይዘው እንችላለን፡፡
  እንድገመው፡፡ለዚህ ሁሉ መሳካት አማራው አሁን ውስጡ ሆኖ የሚያስገድሉትን የአማራ ምስለኔወች ስብስብ ማስወገድ የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው ግድ ይለዋል፡፡
  ይህ ጉዳይ ለአማራው የመሆን ወይንም ያለመሆን፣ የመሞት ወይንም ያለመሞት፣ የመተንፈስ መቻል ወይንም መተንፈስ ያለመቻል የወቅቱና የዛሬ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡ (TO BE OR NOT TO BE) ይሉታል ፈረንጆቹ፡፡
  አማራው ከሌሎች ተለይቶ እንድያልቅ እየተደረገበት ያለውን የአሁኑን እልቂት ካሰቆመ በኋላና ይህንኑም በአስተማማኝ እውን ካደረገ በኋላ ስለአንዲትና ለተከበረች ጠንካራ ኢትዮጵያ መኖር ከሚሰሩና ክሚጨነቁ አጋር ሀይሎች ጋር ስለኢትዮጵያ ሊያስብም ተግቶ ሊሰራም ግድ ይለዋል፡፡
  አማራው ሆዳም የአማራ ምስለኔወችን በያሉበት ከየሰፈሩ ጀምሮ በመንደር፣ በከተማ፣ በወረዳ፣ በዞንና በክልል ደረጃ ያሉትን ለይቶ ያውቃቸዋል፡፡ከእነዚሁ ውስጥ ህዝቡን በይፋ ይቅርታ ጠይቀው ወደህዝቡ ትግል በተግባር የማይቀላቀሉትን እየለየ ያለ ምህረትና ያለርህራሄ አስተማሪ በሆነ መንገድ ነገ ሳይሆን ዛሬዉኑ ማስወገድ አለበት፡፡ አማራው ቆርጦ ይህንን ማድረግ ካልጀመረ አማራ ነጻ አይወጣም ብቻ ሳይሆን በየቀኑ በሽህወች ቁጥሮች መታረዱ ይቀጥላል፡፡ ክልል የለሽ ብቻ ሳይሆን አገር የለሽም ሆኖ ባክኖ ነብር ሆኖ፣ታሪክ ሆኖ ይቀራል፡፡
  ስለዚህ መፍትሄው አንድ ብቻ ነው፡፡ ይህንኑ መፍትሄ የመተግበርያው ጊዜውና ወቅቱም አሁን ነው፡፤
  አማራ ሆይ፦ ሆዳሞችን የአብይ አህመድ ምርኩዞች፣ ሰላዮች፣ ምስለኔወች፣ በውስጥህ ያሉትን የወያኔና የኦሮሙማ ተከፋዮችን፣ ጆሮ ጠቢወችን ወዘተ ጭምር በየሰፈርህ እያነቅህ አስወግዳቸው፡፡ ይህንን ካደረግህ መጪው ጊዜህ ብሩህ ነጽነትህም እውን ይሆንልሀል፡፡
  ብሎም ክልልህን ነጻ አውጥተህ አገርህንም ልታድን ትችላለህ፡፡ ያኔ የወያኔም ሆነ የኦሮሙማ በአማራ ላይ ችግር ፈጣሪነት በራሱ በንኖ ይቀራል፡፡ ምክንያቱም ሆዳሞቹን ከውስጥህ ስላስወገድክ ያኔ የምትቆመው በራስህ እግር ስለሆነና የምትዘምተው በራስህ ልጆች አዛዥነት ስለሆነ የሚባክን ምስጢርና በአንተ ላይ ከጀርባ የሚሾረብ ሴራ አይኖርምና ነው፡፡
  ስለዚህ ጠላቶችህ እፊትህ ሊቆሙ በጭራሽ አይችሉም፡፡ ሁሉም አማራነትህን፣ ነፍጠኛነትህን የማያወላውል ኢትዮጵያዊነትህንና የአንተን የማይታጠፍ ክንድ በሚገባ ያውቁታልና!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.