የአማራ እጣ ፈንታ በራሱ ወኪሎች እንጂ በሌሎች አይወሰንም!! – የአማራ ኅብረት በሙኒክ (ጀርመን)

የአማራ ኅብረት በሙኒክ (ጀርመን)
Amhara Union in München (Deutschland)
የአቋም መግለጫ

የሕወኃት ዘረኛ ቡድን በኦነግ አጃቢነት መንበረ ሥልጣኑን ከተቆጣጠረብት ጊዜ አንስቶ የአማራ ሕብረተሰብ በጠላትነት ተፈርጆ እንደ ዜጋም ሆነ እንደ ብሔር እውቅናን አጥቶ ራሱን የማስተዳደር መብት ተነፍጎ በሞግዚት አስተዳደር የሚገዛ ሕዝብ ነው ።

አማራ በማንኛውም ነገር ከሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች አነስተኛ ሆኖ ሳይሆን በ30 ዓመቱ የዘር ፖለቲካ እንደ ማንኛውም ራሱን ያደራጀና ውክልና ያለው ሆኖ አለመገኘቱ ጥቅሙን ብቻ ሳይሆን ህልውናውን ጭምር ለአደጋ ዳርጎታል ። በመሆኑም በሰሜን በትግራይ ወራሪ ኃይልና በደቡብ በመንግሥታዊ መዋቅር የሚታገዘው የኦነግ ሰራዊት ማንነትንና ዘርን መሠረት አድርጎ የሚፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የአማራ ህዝብ ወኪል ነኝ የሚለው ብአዴን/ብልጽግና አማራውን ከዘር ፍጅቱ ሊከላከለው ይቅርና መቃወም አልቻለም።

በተደጋጋሚ በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ሲፈፀም በአማራ ክልል ም/ቤትም ሆነ በፌደራል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ወንጀሉን በሥሙ ጠርተው የዘር ማጥፋት (Genocide) ወንጀል መፈፀሙን ተቀብለው አቋም ሊወስዱ ይቅርና ብሔራዊ የሀዘን ቀን እንኳን ማወጅ አልቻሉም። በአጭሩ የአማራ ብልጽግና እመራዋለሁ ለሚለው ህዝብ ፍላጎት ፣ ጥቅምና ደህንነት መቆም አልቻለም። በመሆኑም አሁንም እንደዚህ ቀደሙ በኦነጋዊና ህዋሃታዊ ሴራ ድርድሩ የሚያመጣው “ሰላም” የአማራን ሽንፈትና ቀጣይ መካራ የሚያመጣ እንዳይሆን ስጋት ስላለን የአማራ ህብረት ሙኒክ ጀርመን:-

1ኛ. በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት እየተካሄደ ያለውን የሰላም ውይይት በስልጣን ሽኩቻ ጦርነት ከፍተው የአማራንና የአፋርን ክልል የጦር ሜዳ ያደረጉት ትህነግና የኦሮሞ ብልጽግና አማራን ወክለው ጥቅሙን ያስጠብቁለታል የሚል እምነት ስለሌለን አማራ በራሱ ወኪሎች ቢደራደር ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንድሚያመጡ እርግጠኞች ነን ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ

2ኛ. የጦርነቱ መንስኤዎች ሥልጣን የጨበጠው የኦህዴድ ብልጽግናና ሥልጣኑን የተቀማው ትህነግ እንጂ የሶስቱ ክልል ወዳጅ ሕዝቦች ባለመሆናቸው ተወያይተው ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት የሚችሉት ገለልተኛ ተወካዮቻቸውን በማሳተፍ መሆኑን የምናምንበትና የአማራ ማህበር በአሜሪካ ለአወያዮች ያቀረበውን የመወክል ጥያቄና ያቀረባቸውን አራት ተወካዮች የሚያምናቸውና የሚቀበላቸው መሆኑን የአማራ ሕብረት በሙኒክ (ጀርመን) ያረጋግጣል ፤

3ኛ. የአማራን ሕዝብ ለማዳከምና ረፍት ለመንሳት ሆን ብለው ያለ ወንጀላቸው ወንጀል እየፈበረኩ ያሰሩትን ዘመነ ካሴን ፣ የአማራ ፋኖዎችን እና የህሊና እስረኞችን በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፤

4ኛ. በኦሮሚያ ክልል በአማራው ላይ የሚካሄደውን የዘር ማጥፋት ወንጀል መንግሥት ኃላፊነቱን ወስዶ እንዲያስቆምና ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርብ ጥሪ እናቀርባለን ፤

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ

የአማራ ማህበር ሙኒክ (ጀርመን)

23.10.2022

Stadtsparkasse München IBAN:DE ____________________________BIC: SSKMDEMM ______

Leave a Reply

Your email address will not be published.