አሪሂቡ አፍሪካ – በስንታየሁ ግርማ አይታገድ

በስንታየሁ ግርማ አይታገድ (0900065962)

ሕይወቴን በቡና ስኒ ለካሁ። – ቲ.ኤስ.ኤል የዘፈነዉ ነዉ፡፤

በአለም አስደናቂው የ ኢትዮፕያ መለያ የሆነዉ ቡና በዘጠነኛዉ ክፍለ ዘመን በሀገራችን ተገኘ፡፡ከዛም ወደ አረቡ አለም ተሸገረ፡፡በመቀጠል በባሪያ ንግድ እና በቅኝ ገዢወች አማካኝነት በሶስተኛዉ አለም እየተመረተ አወሮጳ እየተላከ የቡና መጠጣት ባህል ተፈጠረ፡፡ቡና የምዕራቡ አለምን ከመጠጥ ሲሰኝነት በማላቀቅ ባለዉለታ ነዉ   ፡፡ለምሳሌ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን በእንግሊዝ መጠጥ ከቁርስ ጋር ሳይቀር እየቀረበ በየአመቱ በአማካኝ እስከ 70 ጋሎኖች ይጠጡ እንደነበረ መረጃወች ያሳያሉ፡፡ይሂንና ቡና መጥቶ እንግሊዝን  ጨዋ እና ነጫ ሀገር አደረጋት፡፡

ከቅርብ አመታት ወዲህ የቡና ባህል በአፍሪካ እያደገ ነው፡፡ ምንም እንኳ አፍሪካ ለአለም ከሚቀርበው 13 በመቶ ብታበረክትም እና የቡና መገኛ አህጉር ብትሆንም ከሌላው ዓለም ጋር ሲወዳደር የአፍሪካውያን ቡና የመጠጣት ባህል የተፈለገውን ያህል አይደለም፡፡ ከኢትዮጵያ በስተቀር፡፡ አፍሪካውያን ከሚያመርቱት ምርት አብዛናውን ለአለም ገበያ የምታቀርብ ፍጆታዋ በጣም ትንሽ ነበር፡፡ አሁን ግን በመጠኑም ቢሆን ሁኔታዎች እየተለወጡ ነው፡፡

የአፍሪካ መንግስታት የሀገር ውስጥ የቡና ፍጆታን እያበረታቱ ነው፡፡ ለምሳሌ ካሜሩን «የቡና ፌስቲቫል» የሚል ሁነት በማዘጋጀት በሁሉም የመንግስት መ/ቤቶች ቡና መጠጣትን እያስተዋወቀች ነው፡፡

በደቡብ አፍሪካም ትኩስና ተሎ የሚደርሱ እና ወደ ቤት ተወስደው ከሚጠቀሙበት መጠጦች ውስጥ በየአመቱ በአማካይ 2.8ቱ የቡና ሱቆች ይሸፍናሉ፡፡ የቡና ኢንዱስትሪውም በአመት በአማካይ በ7.1 በመቶ እያደገ ነው፡፡ የቡና መጠጣት አብዮት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ነው ይላሉ ተንታኞች፡፡

በናይጄሪያም ውስጥ የመካከለኛው ህብረተሰብ ክፍል እያደገ በመምጣቱ እ.ኤ.አ በ2010 እና 2015 በናይጄሪያ ቡና መጠጣት 20 በመቶ እያደገ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኮሜዲያን መስከረም በቀለ ከኤርፖርት በጸጥታ ኃይሎች ታፈነ

ጥናቶች እንደሚያሳዩት እ.ኤ.አ በ2020 ናይጄሪያውያን 1000 ቶን ቡና ይጠጣሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህንን ፍጆታ ደግሞ የናይጄሪያ የቡና ምርት አይሸፍንም፡፡ ይህንን እድል ኢትዮጵያ ልትጠቀምበት ትችላለች፡፡ የአሜሪካ የግብርና ምርት መምሪያ እንደገመተው ኢትዮጵያ በ2022 /2023 በኢትዮጵያ 495ሺህ ሜትሪክ ቶን ቡና በማምረት ሪከርድ የሆነ ምርት በማምረት ኤክስፖርቱም ሪከርድ እንደሚሆን ተንብይዋል፡፡

ከአፍሪካ አብዛኛው የሮብስታ  ቡና አምራች አገራት የሆነችውም ዩጋንዳ የአገር ውስጥ ፍጆታዋን በ20 በመቶ በአማካይ በማሳደግ ኢኮኖሚዋን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ትችላለች፡፡ ዩጋንዳም የቡና ባለስልጣን የሀገር ውስጥ ፍጆታን ለማበረታታት ንቅናቄ ጀምሯል፡፡ ይህም በሳምንት ውስጥ 20ሺህ ስኒቡና  በነፃ ማቅረብ ያካትታል፡፡

በጎረቤታችን ኬንያም መካከለኛው ህብረተሰብ እያደገ በመምጣቱ የኬንያውያን ቡና የመጠጣት ባህል ለማሳደግ እና ከሻይ ይልቅ ቡናን እንዲጠጡ ለማበረታታት የቡና ሱቆች በማስፋፋትና በማበረታታት የሸማቹን እምነት ለማሳደግ እየጣረች ነው፡፡

ይሁንና እነዚህ ጥረቶች ሁሉ በቂ ሆነው አልተገኙም፡፡ ከዚህ በመነሳት ከዳበረው የኢትዮጵያ ቡና የመጠጣት ባህል ልምድ ለመውሰድ አፍሪካውያን ከኢትዮጵያ የቡና ባህል ልምድ በመቅሰም እና ወደ ራሳቸው ለመውሰድ በአዲስ አበባ መክረዋል፡፡

ምክንያቱ ደግሞ ኢትዮጵያ የቡና መገኛ አገር ብቻ ሳትሆን ለዘመኑ የዳበረ የቡና ባህል ያላት አገር በመሆኗ ነው፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ኢትዮጵያ በአማካይ ከምታመርተው የቡና ምርት ከግማሽ በላይ ለአገር ውስጥ ፍጆታ ታውለዋለች፡፡ ይህ ልምድ የኢትዮጵያን ቡና ቀጣይነት ከማረጋገጥ አኳያ መልካም እድል ነው፡፡

በአፍሪካ ከከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ ቡና የመጠጣት ባህል በተለይም በመጠኑ እየጨመረ ነው፡፡ በከተሞች የቡና ሱቆች እየተስፋፉ ነው፡፡ የመካከለኛው ህብረተሰብ ክፍልም እያደገ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ቡና ኤክስፖረት ማደግ ከፍተኛ እድል ነው፡፡ የአለም የቡና ገበያ ዋጋ ወሰኖች ባደጉ አገሮች ትንሽ ቡና ቆዪዎች እና ድንበር ተሸጋሪ ኮርፖሬሽን ናቸው፡፡ ዋጋውን የሚወስኑት እነሱ በመሆናቸው የአለም አነስተኛ ቡና አብቃይ አርሶ አደሮች ገቢ የምርት ወጪውን እንኳን የሚሸፍን አይደለም፡፡ ይሁንና የኢትዮጵያን ቡና ይህንን ስጋት የመቋቋም እድሎች አሉት፡፡ እነሱም፤

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘብ ተበድረው አልከፈሉም የተባሉ የውጭ ዜጎች በ25 ዓመት እስራት ተቀጡ

ኢትዮጵያ ብዛት ያላቸው ልዩ ቡና / Speciality Coffeee ባለቤት በመሆኗ 2/3ኛውን ኢትዮጵያ ቡና ልዩ ቡና ተብሎ የመመደብ ብቃት አለው፡፡ ሸማቾች ደግሞ ለልዩ ቡና የተሸለ ክፍያ የመክፈል ልምድ እያዳበሩ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ቡና ከ90 በመቶ በላይ ኦርጋኒክ ተብሎ የሚፈረጅ መሆኑ ከሸማቾች ጤንነት ጋር ተያይዞ ተጨማሪ እየሆነ መምጣቱ እና የተሸለ ክፍያ እያደገ መምጣቱ፤

« ፍትሀዊ ንግድ  »   የሚደረግ ንቅናቄ እያደገ መምጣቱ የቡና ቀጣይነት በአለም በተዛባው የንግድ ስርዓት ምክንያት አነስተኛ ቡና አብቃይ አርሶ አደሮች እየተጎዱ በመሆኑ ፍትሀዊ ንግድ ንቅናቄ አቀንቃኞች አነስተኛ አምራች አ/አደሮች የምርት ወጪያቸውን ለመሸፈን የሚያስችል እና ኑሯቸውን ለመግፋት የሚያስችል ሲስተም እንዲኖር አየጣሩ ነው፡፡ በሸማቹም ተቀባይነት እያገኘ ነው ቡና ጠጪዎች ቡናው የት እንደተመረተ፣ እንዴት እንደተዘጋጀ እና እንደታሸገ በማወቅ የተሻለ ዋጋ ለመክፈል ፍላጎት እያሳዩ ነው፡፡

ከቡና ምርት ጀርባ ያለው አካባቢያዊ፣ ማህበራዊና የአካባቢ ጉዳዮችን ቡና ጠጪዎች በማወቅ የተሻለ ክፍያ ለመክፈል ፍላጎት እያሳዩ ነው፡፡ በድርጊትም እየገለጹ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ ይህንን ስለምታሟላ ለአ/አደሮቻቸው ምርጥ እድል ነው፡፡ ለዚህም ነው የሚቀጥለው አመት የቡና ጣዕም ውድድር ሀገራችን የምታስተናግደው፡፡

የአፍሪካ ኢኮኖሚ ማደግ በአለም ላይ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት አገሮች አብዛኛዎቹ ከአፍሪካ ናቸው፡፡ በአፍሪካ ወጣቱ እና መካከለኛው የህብረተሰብ ክፍል በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ነው፡፡ ቡና መጠጣት በአሁኑ ሰዓት የሞደርናይዜሽንና ስልጣኔ ምልክት እየሆነ ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በቀን ከሁለት ስኒ ቡና በላይ መጠጣት የእድሜ ጣሪያን በ15 አመታት እንደሚጨምር ተረጋግጧል፡፡ እድሜ ጣሪያ ደግሞ ከፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል (HDI) አንዱ ነው፡፡ እያደገ የሚመጣውን የአፍሪካ ቡና ፍጆታ ደግሞ ሊሸፍን የሚችለው የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው የኢትዮጵያ ቡና ምርት ነው፡፡ ስለዚህ ፊታችንን ወደ አፍሪካ ማዞር አለብን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ተካበ ዘውዴ የእናንተን እርዳታ ይፈልጋል

የኢትዮጵያ ቡና መገኛ አገር በመሆኗ ጥሩ ገጽታ እና መልካም ስም አዳብሯል፡፡ ሸማቾች ደግሞ ከምርቱ በላይ ዋጋ የሚከፍሉት ለመልካም ስም ነው፡፡ስለዚህ የአፍሪካን ወጣት የበለጠ ቡና መጠጣት በማስተዋወቅ ለምሳሌ ከፕርሚርይር ሊግ ከለቦች አንዱን ስፖነሰር በማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡

ለምሳሌ ኢትዮጵያ ቡና፣ሲዳማ ቡና ወ.ዘ.ተ

Leave a Reply

Your email address will not be published.