ደመቀ መኮንንና ተመስገን ጡሩነህ፤ የኢትዮጵያ ተደራዳሪወች ወይስ የወያኔና የኦነግ አስታራቂወች? – መስፍን አረጋ

በምዕራባውያን አጋፋሪነት ደቡብ አፍሪቃ፣ ፕሪቶሪያ ላይ የሚካሄደው ዱለታ በኦነግ የበላይነት የወያኔን ሎሌነት በማስቀጠል የአማራን ሕዝብ ቴሳ ለማጥፋት ሁለቱ የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላቶች ከአማራ ሕዝብ ጀርባ የሚስማሙት ስምምነት መሆኑን የማይረዳ ሕፃን ወይም ሕጹጽ ብቻ ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ ዋና የሕልውና ጠላት የሆነው ጭራቅ አሕመድ ደግሞ፣ ጅል፣ ጅላጅልና ጅላንፎ እያለ የሚሳለቅበትን የአማራን ሕዝብ የሚመለከተው የማስታወስ ችሎታ የሌለው (short memmory) ሕጹጽ አድርጎ ነው፡፡  የደቡብ አፍሪቃው ጉዳይ የአማራን ሕዝብ የማይመለከት የኦነግና የወያኔ ጉዳይ ነው ሲባል፣ ከደመቀ መኮንን ወዲያ አማራ ላሳር በማለት ያሾፈውም በዚሁ ምክኒያት ነው፡፡  ስለዚህም፣ መሠረታዊው ጥያቄ “እውን ደመቀ መኮንን የአማራ ሕመም የሚያመው አማራ ነው?” የሚለው ነው፡፡

ደመቀ መኮንን በትምህርቱ ብዙም ያልገፋ ከመሆኑም በላይ ራሱን በራሱ የሚያስተምር ዓይነት ሰው አይደለም፡፡  በዚያ ላይ ደግሞ የሚያውቃትን በደንብ መግለጽ የማይችል አንደበተ ግድር (challenged) ከመሆኑም በላይ በራስ መተማመን የሚባል ነገር ምናምኒትም እንደሌለው በግልጽ ያስታውቅበታል፡፡  ይባስ ብሎ ደግሞ ኃላፊነት መውሰድን እንደ ጦር የሚፈራ የጃግሬነት ሰብዕና (follower mentality) በጽኑ የተጠናወተው፣ ለጀሌነት እንጅ ለመሪነት ያልተፈጠረ ጃግሬ ግለሰብ ነው፡፡  ደመቀ መኮንን ጠቅላይ ሚኒስትር ሁን ቢባል በቤተመንግሥት አጥር ዘሎ ድራሹ ይጠፋል የሚባለውም በዚሁ ምክኒያት ነው፡፡

ይህን በእውቀትና በመንፈስ ደካማ የሆነ የምድረገነት (ከሚሴ) ግለሰብ፣ ላኮመልዛ (ወሎ) የኦሮሞ ነው በሚለው የኦነጋውያን የፈጠራ ትርክት አጭበርብሮ ወደ ቀንደኛ ኦነጋዊነት ለመቀየር፣ ላጭበርባሪው ለጭራቅ አሕመድ እጅግ በጣም ቀላል ነው፡፡  የደመቀ መኮንን ተግባር በግልጽ የሚያመለክተው ደግሞ ግለሰቡ በጭራቅ አሕመድ ኦነጋዊ ስብከት ታውሮ፣ ከወያኔነት ወደ ኦነጋዊነት ተቀይሮ፣ ከለማመበት የተጋባበት ወይም ከመምህሩ ደቀመዝሙሩ እንዲሉ ከራሱ ከጭራቅ አሕመድ በላይ ጽንፈኛ ኦነጋዊ ሁኖ፣ የኦነጋውያንን ፀራማራ አጀንዳ ከጭራቅ አሕመድ በላይ እያራመደ መሆኑን ነው፡፡  በመሆኑም ደመቀ መኮንን አማራ ሳይሆን የአማራ ለምድ የለበሰ ኦነጋዊ ተኩላ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የእናት አገር አድን ጥሪ - የመጨረሻው ምክር - ሰማችሁ አልሰማችሁ - ከአባዊርቱ

ደመቀ መኮንን የአማራ ሕዝብ መሪ ነኝ እያለ፣ አማራ ሕዝብ በኦነግ ሲጨፈጨፍ ዝንብ የሞተ ሳይመስለው ድመጹን አጥፍቶ የተቀመጠው የአማራን ለምድ የለበሰ ኦነጋዊ ተኩላ በመሆኑ ብቻ ነው፡፡  ባጭሩ ለመናገር ደመቀ መኮንን የወለጋንና የመተከልን አማሮች ቀርቶ የገዛ ልጆቹን ለጭራቅ አሕመድ ጭዳ አድርግ ቢባል፣ ለእርድ ለማቅረብ ቅንጣት የማይቃማማ፣ ለጭራቅ አሕመድ ፍጹም ታማኝ የሆነ የጭራቅ አሕመድ ፍጹም ሎሌ ነው፡፡

የሰኔ አስራምስቱ የባሕርዳር ጭፍጨፋ ሚስጥር ቁልፉ ያለው ደመቀ መኮንን የአማራን ለምድ የለበሰ ኦነጋዊ ተኩላ መሆኑን በመረዳትና በጭፍጨፋው ወቅት ቦሌ አየር ወደብ ውስጥ ጃኖች መንፈላሰሻ  (vip lounge) ተቀምጦ ምን ሲያደርግ እንደነበር አጥብቆ በመጠየቅ ነው የሚባለውም በዚሁ ምክኒያት ነው፡፡  ደመቀ መኮንን በራስ መተማመን  እጥረት የሚሰቃይ ሰው ስለሆነ፣ እነከሌ በማንነትህና በምንነትህ ይንቁሃል ብሎ በመስበክ ለበቀል እንዲነሳሳ ማድረግ ለሐሳዊ ተዋኙ (con artist) ለጭራቅ አሕመድ የሕጻን ጨዋታ ያህል ቀላል ነው፡፡  የፈሪ ብትር ሆድ ይቀትር እንዲሉ፣ እንደ ደመቀ ዓይነት፣ ውሃ ውስጥ የሚያልበው ቱርቂ ደግሞ ለበቀል ከተነሳሳ ብትሩ በጣም አሰቃቂ ነው፡፡  ጭራቅ አሕመድ ደመቀ መኮንንን በበቀል ስሜት አነሳስቶ ባሕርዳር ላይ ለፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል ግብራበሩ ካደረገው ደግሞ፣ ወንጀለኛነቱን እንደ ማስፈራርያ በመጠቀም ሲጠራው ወዴት፣ ሲልከው አቤት፣ ዝቀጥ ሲለው እስከየት የሚል፣ አፋሽ አጎንባሽ ሎሌው ያደርገዋል፣ አድርጎታልም፡፡

ተመስገን ጡሩነህ ደግሞ ጭራቅ አሕመድን ለማስደሰት እንጦረንጦስ ለመውረድ ዝግጁ የሆነ፣ በጭራቅ አሕመድ ስም ምሎ የሚገዘት፣ የጭራቅ አሕመድ ባልደረባ ሳይሆን ጃንደረባ ነው፡፡  ተመስገን ጡሩነህ ሲፈጠር ጀምሮ አማራዊነት የሌለው ወይም ደግሞ አማራዊነቱን በጭራቅ አሕመድ የተሰለበ የጭራቅ አሕመድ ስልብደንገጡር ወይም የጭን ገረድ ነው፡፡  ተመስገን ጡሩነህ ለሰኔ አስራምስቱ የባሕርዳር ጭፍጨፋ ከጭራቅ አሕመድና ከደመቀ መኮንን ቀጥሎ ዋናው ተጠያቂ ወንጀለኛ ነው፡፡  ተመስገን ጡሩነህ ልክ እንደ ደመቀ መኮንን ከኦነጋውያን በላይ ኦነጋዊነት የሚሰማው የአማራ ለምድ የለበሰ ኦነጋዊ ተኩላ ነው፡፡  ተመስገን ጡሩነህ  የአማራ ጥላቸው ከውስጡ እየገነፈለ ግንባሩ ላይ ተንጨፍጭፎ እፊቱ ላይ በመከልበስ በግልጽ የሚነበብበት፣ አማራን የሚጨፈጭፉትንና የሚያስጨፈጭፉትን ለማመስገንና ለመሸለም የሚሽቀዳደም ወደር የሌለው አማራጠል ነው፡፡  ተመስገን ጡሩነህ ፋኖን ሳያጠፋ ላያንቀላፋ በጌታው በጭራቅ አሕመድ ስም ምሎ የተገዘተ ፀረፋኖ ነው፡፡  ተመስገን ጡሩነህ እመራዋለሁ የሚለውን የአማራን ሕዝብ ‹‹ወንጀለኞችን የሚያወድስ ማሕበረሰብ›› በማለት ሸንጎ ላይ በይፋ በመሳደብ የአለምነው መኮንንንየሽመልስ አብዲሳንና የታየ ደንድኣን ስድብ የደገመ፣ በአማራ ሕዝብ ላይ ጭራቅ አሕመድ የጫነው ትልቅ መርገምት ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አሜሪካ የበለጠ ትናገር! (ከጸጋዬ ገብረመድህን አርአያ)

የትም ይወለዱ የትም፣ ደመቀ መኮንንንና ተመስገን ጥሩነህን የመሳሰሉ አማራዊነት የሌላቸው የብአዴን ፀራማራ ተኩላወች ያላቸው ቋሚ ባሕሪ አንድና አንድ ብቻ ሲሆን፣ እሱም እጅግ የከረረ የአማራ ጥላቻ ነው፡፡  ስለዚህም ፀራማራ የሆነን ማናቸውንም ቡድን በሎሌነት ለማገልገል ሙሉ ፈቃደኞች ብቻ ሳይሆኑ፣ ሙሉ ደስተኞችም ናቸው፡፡  በመለስ ዜናዊ ዘመን የወያኔ ታማኝ ሎሌወች እንደነበሩ ሁሉ፣ በጭራቅ አሕመድ ዘመን ደግሞ የኦነግ ታማኝ ሎሌወች ሁነዋል፡፡  ከወያኔ ሎሌነት ወደ ኦነግ ሎሌነት በቀጥታ መሻገራቸው ደግሞ ለሌላ ሰው እንጅ ለነሱ ምንም ተቃርኖ የለውም፡፡  ለነሱ የሚታያቸው ፀራማራነት ብቻ ስለሆነ፣ በነሱ ዕይታ መሠረት በወያኔና በኦነግ መካከል አንዱ የትግሬ ሌላው የኦሮሞ ፀራማራ ከመሆኑ በስተቀር ሌላ ልዩነት የለም፡፡  ስለዚህም እነዚህን የብአዴን ተኩላወች ይበልጥ የሚያረካቸው ሁለቱ ፀራማራወች (ማለትም ወያኔና ኦነግ) ባንድነት ተባብረው አማራን ይበልጥ ቢያጠቁላቸው ከቻሉ ደግሞ ሕልውናውን ቢያጠፉላቸው ነው፡፡

ስለዚህም ደመቀ መኮንንና ተመስገን ጡሩነህ የፕሪቶሪያውን ድርድር እንዲመሩ በጭራቅ አሕመድ የተመረጡት፣ ወያኔንና ኦነግን አስታርቀው ለፀራማራ ዓላማቸው እንዲተባበሩና የአማራን ሕልውና ክስመት እንዲያፋጥኑ ያደርጉ ዘንድ ብቻና ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም፣ የአማራ ሕልውና የሚያሳስባቸው የአማራ ልሂቃን ሁሉ፣ በደመቀ መኮንንና በተመስገን ጡሩነህ መሪነት በወያኔና በኦነግ መካከል የሚካሄደውን ድርድርንም ሆነ ውጤቱን በፍጹም እንደማይቀበሉት ማወቅ ለሚገባው ሁሉ፣ በተለይም ደግሞ ለባለጉዳዩ ለአማራ ሕዝብ በደንብ ማሳወቅ አለባቸው፡፡  የወያኔና የኦነግ ሕገመንግሥት አማራን እንደማይመለከት ሁሉ፣ የወያኔና የኦነግ ድርድርም አማራን አይመለከትም፡፡

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

 

4 Comments

 1. ፕሮፍ እናመሰግናለን እነሱስ እንዲህ እየተዋረዱ ከሚኖሩ በቃን ቢሉ? ከዚህ በአማራው ብሄረተኛ ጥምብ እርኩሳቸው ይወጣል ከፍ ሲል ደግሞ የኦሮሞ ባለስልጣኖችን ቀና ብሎ የማየት ድፍረታቸውን ተነጥቀዋል። ስብሰባ ሲኖርም ወንበር አስተካክሉ ይሏቸዋል። ምን ያህል ሊኖሩ ነው ቆረጥ አድርገው ያለፈው ይበቃናል ህዝባችን ጋር እንቆማለን ብለው ቢወስኑ። ከበረቱም በአሳምነው ጽጌ መንገድ ቢሄዱ። አሳምነው እኮ በሞቱ በለጣቸው። እንዴት ነው በህዝባቸው ተንቀው በቀጣሪያቸው ተንቀው። አብይ ወደ ጎንደር ሲሄድ ያገኘሁ ተሻገርን ሁኔታ ያየ የጤንነት ነው? በእሱ እድሜ እንዴት ሰው እራሱን ትዝብት ላይ ይጥላል?ባለፈው ትግሬዎች ምነው ከፋህ እያሉ በጥፊ ይመቷቸው እንደነበረ ይነገራል። ልብ ይስጣቸው አይባል እድሜያቸው ገፍቷል ሆዳቸውን ይቀንሰው ነው ማለትም ከተቻለ። በክፋት አትዩብኝ ቤተሰብ አታጡም የናንተ ውርደት የነሱ ውርደት ነው ብዬ ነው።

 2. As a matter of the political fact of the country for more than three decades (27+5), the so-called peace talk is between the very stupid and brutal factions of the same terribly criminal political system (EPRDF), not between two different parties of politics at all!

  Sadly enough, all this deeply horrifying situation has continued because of an unbelievable absence of well-informed, well-organized and well-coordinated peoples’ movement which is of course the very result of a section of the society that claims itself as educated and intellectual but as a matter of the reality on the ground victim of ignorance worse than the majority of the population that had and has no educational opportunities! Is this not horrifying! Absolutely it is!!!

 3. ልጅህን ገድሎ ሀብትህን አውድሞና ዘርፎ ድርድር ምን የሚሉት ነው?ሁሉን የሚወክለውን የሀገር መከላከያ ያውም እሱን ከጥፋት ለመታደግ በተኛበት ያረደ ከሀዲ ስብስብ ጋር በምን ሞራል ሰው ወደ ድርድር ይገባል? ትግሬዎች ምን የሚያነሱትስ ይኖራቸዋል? አያያዙን አይተህ እንደተባለው መንግስት ተብዬ የተቀመጠው እንኩቶና ለነሱ አላማ የተቀመጠ በመሆኑ ሳይሸማቀቁ ለመደራደር ሳይሆን ለመቀማትና ነገሩን በነሱ ቅኝት ለማሳለጥ ተቀምጠዋል። በዘረፋና በቅሚያ የወሰዱት ሁሉ ይመለስላቸዋል በመጠየቅ የሚወዳደራቸው አይኖርም ብዙ ብዙ ይጠይቃሉ። ቀሪው የተደነባበረውን መንግስት ዳግም አደነባብረው ኢሳይያስን ያስወግዳሉ ከዚያም ኢትዮጵያ ዳግም የአርማጌዲዎን ዘመን ታሳልፋለች ትግሬ ተፈጥሮው እንዲህ ነው።

 4. One Shegitu Dadi, A Very Forward Looking Oromo Woman Has The Following To Say On Confederation. I’m Copying And Pasting Her Write-Up Without Her Authorization Hoping That She’ll Not Mind.

  “Here Is How To Save Amharas, Oromos And The Country.

  Once Again In Our Recent History, Amharas Have Emerged As The Holders Of The MASTER Key To Solve Ethiopia’s Multifaceted Problems . How? By Opting For Confederation.

  Amharas Have No Choice But To Move For Confederation Simply Because Federation In The Ethiopian Context Does Not Work.

  As A Polirized Multi-Ethnic Country, Ethiopia Will Not Have A Fair And Free Election Without The Opression Of One Or Another Ethnic Group. Hence, Democracy Is An Illusion That Cannot Be Realized. The Way Oromo Rose To Power And Now Control The Entire Country Through Proxy Regional Governments Is The Proof. Tigreans Did It For The Last Thirty Years And Oromos Have Stepped In Tigreans Shoes To Impose Similar One Ethnic Group Rule. With Their Number And Size Of Their Region, Oromo Opressive Rule Will Be Much Worse Than Tigrean`S. Give Another Ten Years To Oromo Rule, Ethiopia Will Be The Tail Of The World By All Standards Of Measure.

  So, It Is Time For Amharas To Exercise Their Constitutional Right To Self-Determnation And Vote On Confederation. If They Adopt Conederation, It Will Give Them The Opportunity To Attract Direct Foreign Investment Since Confederation Will Enable Them To Have Economic Diplomats And Even Have Embasies Abroad Cutting The Oromo Controlled Foreign Ministry Diverting Foreign Investment To Oromia And Other Favoured Regions. Amharas Can Also Have A Defense Force Which Will Protect Them From Foreign Invaders Including Ethnic Oromo Organizations.

  The Belgian Model Of Confederation Which Appears To Hep Advance Amhara Interests Is Something To Explore.

  In Any Event, Ethiopia Needs Vast Decentralization Resembling Confederation Since The Federalism The Country Has Adopted Is Notheing Other Than Unitarism In Disguise. Controlled From The Centre, It Has Miserably Failed To Develop The Country Let Alone Prosper And Ensure Safety And Security Of Its Citizens. The Chaos We See In The Country Right Now Has Much To Do With Lack Of Development (In All Sectors) And Security. Both Have Proven Beyond The Capacity Of The Federal Government To Provide.Change Of Government At Federal Level Is Not The Answer For These Problems.

  Tigreans Have Floated The Idea Of Confederation, Amharas Must Follow. Tigreans Know That They Will Not Be Fairly Treated Under Oromo Rule; As A Result, Their Choice Of Confederation Appears Just. Amharas Must Seize The Opportunity To Decide Their Destiny Via Self-Determination As Well Without Wasting Another Decade Under Incompetent Oromo Rule. Despite All The Atrocities They Have Committed, Tigreans Are Being Heard And Embraced By The Oromo Rule Since Oromos Now Feel Tobe The Savours Of Ethiopia.

  Folks! Don’`T Be Fooled!. Oromos Pretend To Be “Savours” Only If They Rule The Entire Country As One Piece. Like Any Other Ethnic Group That Aspire To Oppress And Dominate , They Are After Resources. If Amharas Want To Be Heard And Embraced As Tigreans, They Have To Go For Confederation. If Confederation Does Not Work, They Have To Say Good Bye To The Ethiopian State.

  It Is Outdated For Amharas To Hang On “Mama Ethiopia” Cry Since Nobody In The Country Is Interested In It Any More. What Amharas Got From This Cry Is Atrocotoes, Redicule And Shame. All These On Amhara Because They Gave Oromos And Other Ethnic Groups A Country Which They Are Not Ready And Willing To Let Go. If Amhara Insist On Confederation, Oromos Might Call The Army On It To Protect The Unity Of The Country! That Will Make Them A Laghing Stock Since They Were In The Forefront To Weaken The Unity Of The Country. Now They Cannot Be Alllowed To Reverse Gear.

  Amhara! Wake Up And Smell The Coffee. Tell Oromos That You Want Confederation – If Not Confederation Then Separation. Oromo Crack Down Will Soften Even Disappear As It Did For Tigreans If Amara Opt For Confederation. But The Idea Is Not To See Oromo Softening On Amhara, It Is To Seek Real Confederation As A Wayout From Decades Long Quagmire. Oromo Softeneing Does Not Take Amharas Anywhere.

  Try It! It Will Work And Catapult Amhara Development And Growth To The Sky And Ensure Their Security. It Will Eventually Liberate Oromos Too From Their Bloody Distructive Path Poised To Takie Everybody Else Down With Them.

  For Us, Oromos, Conederation Is Also The Answer. ”

  GREAT!

Leave a Reply

Your email address will not be published.