የኢትዮጵያ ዋነኛ ያለመረጋጋት ሰበብ የቋንቋ ርዕዮት ነው ፡፡ ድርድሩ ከዚህ አኳያ መቃኘት አለበት

እኛ  የእነሱ ”  የቋንቋ መደብ  በኢትዮጵያ ብቻ  ፤ ወደ 32ኛ ዓመቱ እየተጓዘ ያለ ነው ።

 መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

“የመደብ ትግል የማያቋርጥ በመሆኑ ፣ በሰው ለሰው ግንኙነት ና በመደቦች መካከል ግጭት አያቋርጥም ፡፡ ተጨቋኝና ጨቋኝ መደብ እሰካለ ጊዜ ድረስም ግጭት የማያቋርጥ የዕለት ዕለት ክስተት ነው ፡፡”   ( ካርል ማርክስ )

ካርል ሔንሪክ ማርክስ (ከግንቦት  5, 1818 እስከ መጋቢት 14, 1883 የኖረ ) ጀርመናዊ ፈላስፋ እና የፖለቲካ ተመራማሪ ነው ። በኖረበት ዘመንም ሰው ልጅን የሚጠቅሙ ፅሑፎችን አበርክቷል ። የካርል ማርክስ ፅሑፎችም  በኢኮኖሚ እና የሃይል ፖለቲካ ላይ ያተኮሩ ናቸው ።  ካርል ፤ ″   ክፍያ ጠባቂ  ጉልበት በዝቶ  በተትረፈበት  የጉልበት ብዝበዛ ይኖራል ።  ይህ ደግሞ የመደብ ትግል እንዲኖር ያሥገድዳል  ። ″  ይለናል ። ″ ይህ የመደብ ትግልም የሚደመደመው በላብአደሩ ( በሠራተኛው መደብ ) አሸናፊነት ነው ። “ ብሎ የምናል ።

ከካርል ማርክስ መጻሕፍት ውስጥ “ ኮሚዩኒስት ማኒፌስቶ “ የተሰኘው መጽሃፉ በጣም የተወደደለትና የተነበበለት መፅሐፍ ነው ፡፡  ይህን መጽሐፍ በመፃፍ የፍሬድሪክ ኤንግልስ አስተዋጾ ቀላል አልነበረም ።  በ1840 ዓ.ም.  ነበር ይህ መጽሐፍ ለንባብ የበቃው ። መጽሐፉ የኮሚዩኒዝምን ሃሳቦችና አላማወች በግልፅ አስቀምጧል። ይህንን የካርል ማርክስን ሃሰብ የሚያረመረዱ  ማርክሲስት በመባል ይታወቃሉ።

በሌላ ጎን ካርል ማርክስ ከደረሳቸው መጻሕፍት “ ዳስ ካፒታል “ የሚሰኘው ፣ እንደ ዋና ስራው ተደርጎ ይወሰዳል። የዚህ መጽሐፉ ሦስት ክፍሎችን ለመፃፍ ካርል ከባድ የህይወት መሰዋትነት ከፍሏል ። “ዳስ  ካፒታል “ እንዴት ካፒታሊዝም እንደሚሰራ ሲገልጽ በዚያው ልክ ካፒታሊዝም የሚፈጥራቸውን ችግሮች በጥልቀት ያብራራል ። የማርክስ ርዕዮተ አለም ለሶሻሊዝም መነሳትና ለሩሲያ አብዮት መንስኤ እንደሆነ በብዙዎች የታመነ ነው። የማርክስ ታዋቂ ርዕዮት የተመሠረተው  ሞላዋን ዓለም በቁስ አካል በመፈረጅ እና  ሃይማኖት፣ ሥነ ምግባር እና ማህበረሰባዊ መዋቅሮች በሙሉ መሰረታቸው ኢኮኖሚ ነው። “  ብሎ በማመን ነው ።

ብዙ ሰዎች እስካሁን ደረስ የማርክስን ሃሳብ ይከተላሉ፣ እንዲሁም በማሳደግ ሲያዳብሩት ይታያሉ። በአንዳንድ አገሮች ርስት ሁሉ ከግል ተወስዶ  የመንግሥት መሆኑ ፤   የካርል ማርክስ ፍልስፍና የወለደው ሶሻሊዝም ና ኮሚኒዝም  ውጤት ነው ። በተጨማሪ ማርክስ በመፀሐፎቹ  የሃይማኖት ወዳጅ ያለመሆኑንን አሥረግጦ በመናገሩ ፣ በግልፅም ሆነ በህቡ ፣ በማርክሲስም-ሌኒኒዝም ርዕዮት በሚመሩ አገራት በሙሉ  የሃይማኖት ነጻነት  በወጉ አይከበረም ።

እናም ዛሬም ፣   “መደብ ብሎ ነገር የለም ፡፡ ጨቋኝና ተጨቋኝ መደብ ብሎ ነገር የሉም።የማርክስ ትወራ  ተርት ተረት ነው ፡፡”  የሚል የተቃውሞ ሃሰብ ያላቸው ልሂቃን  እና ዓለም በመደብ የተከፋፈለች ናት ።”የገበሬው፣የላብ አደሩ፣ ፣የንዑሥ ከበርቴው ና የከበርቴው መደብ ዛሬም አለ ። ” የሚሉ ፣  አዛና አዚህ “እሰጥ አግባ “ቢሉም ፤የካርል ማርክስ አስተሳሰቦች ፣በእያንዳንዱ ማህበረሰብ ወስጥ እያንዳንዱ ግለሰብ ና ቡድን  የሚታወቅበትን  ትወራ ተመርኩዘው ፣በወቅቱ ጥልቀት ባለው ምልከታ የቀረቡና ቅቡል እንደነበሩ ይታወቃል።እነዚህ ሃሰቦች  ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ ፣  የምናጣጥላቸውና  “አይረቡም ፡፡”ብለንም በማንቋሸሽ ፣እውነታቸውን ለመሸፋፈን ከቶም አንችልም። ይልቁንስ   ዛሬም በቅጡ መጠናት የሚገባቸው  እንደሆኑ መገንዘብ ተገቢ ይመስለኛል።ምንም እንኳን በካርል ማርክስ ሃሳብ ውስጥ ሴጣኑ አለ ብለን ብናሥብም…

ተጨማሪ ያንብቡ:  ታዋቂው የሙዚቃ ሰው ቴዲ ምትኩ በጠና ታሞ ሆስፒታል ገባ

በካርል  ማርክሥ ትወራ ውሥጥ ፣ “ሴጣኑ” ቢኖር እንኳ ፣”ሴጣኑን ” ከውሥጡ አውጥቶ በማሳየት እውነታውን በተጨባጭ ማሥረዳት እና ቀና ህሊና ያለው ወደጥፋት እንዳይሄድ ማሳወቅ እንጂ ፣ዝም ብሎ በደምሳሳው” ሴጣናዊ  ሃሳብ  በትወራው ውሥጥ  አለ ። አትጠጉት ! “ ብሎ ማስፈራርቾ ማብዛት ተገቢና አስፈላጊ አይደለም ።

ዛሬ በሃያንደኛው ክፍለ ዘመን “ሥለመደብ “ ባይወራም ( ″ታዲያ ስለአልጋ ነው የሚወራው ? ″ የምትሉ ቀልደኞች በቅኔአችን መንገድ ልክ ናችሁ ፡፡ ) የማህበረሰብን መታወቂያ በትወራ መልክ የሚተነትኑ፣መደብን በቡድን እና በጎሳ  ቀይረው ፣”የእኔ ማነኝ ጥያቄን”  አሉታዊ ና አወንታዊ ጎን በጥናታዊ ጽሑፋቸው የሚያቀርቡ ምሁራን ብዙ ናቸው።

ለምሳሌ ስለ  ማህበረሰብ መታወቂያ ትወራ   ( social identity theory ) እንዲህ የሚል ሃሰብ በጥናታዊ ፅሑፋቸው ያቀረቡ አሉ።  “social identity theory states that the in-group will discriminate against the out group to enhance their self-image.” -Henri tajfel and John turner (social psychologist)

“የሄ የማህበረሰብ መታወቂያ ትወራ ሃሰብ የሚያነጣጥረው  በአንድ ቡድን ውስጥ ባለና በቡድኑ ውስጥ በሌለ  ላይ ነው ፡ በቡድኑ ውስጥ ያለ በቡድን ውስጥ ያላከተተውን የሌላኛውን  ጥቅም በማሰጣት የራሱን ቡድን ጥቅም ለማብዛት የሚጣጣርበት ሁኔታ በዚህ ትወራ ይገለፃል፡፡” በሌላ በኩል ሌለኞቹ  የማህበረሰብን ሥነ ልቦና የሚያጠኑ ምሁራን  ደግሞ  ፣ “…a social identity is a person’s knowledge that he or she belongs to a social category or group.”

“ የማህበረሰብ መታወቂያ ማለት ፤እንደ ግለሰቡ ዕውቀት የሚወሰን ሲሆን፣እርሷና እርሱ በመረጡት ማህበረሰብ ውስጥ በንፅፅር  በጉልህ ሊታወቁ እና በሌላውም ቡድን እወቅናን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡” ይሉናል፡፡ (ማይክል  ኤ ሆግ እና ዶምኒክ አበርሃም) ለምሳሌ  ሰው ፤በቤተሰቡ፤ በኃይማኖቱ፣በፍቅር ግንኙነቱ ወይም ባፈቀራት ሴት፣በግል ፍቅሩ ወይም ሆቢው ፣በሙያው ወይም በቡድን ሙያዊ ሥራው፣ባለው ሥልጣን እና ቦታ፣ በታዋቂነቱ ፣በከፍተኛ  ትምህርት ተማሪነቱና ተሳትፎው፤በልዩ ልዩ የስራ ዘርፉ (ገበሬ፣ነጋዴ፣ወቶአደር ወዘተ፡፡) ማለት ነው ።

የመጀመርያው ትወራ ውጉዝና ዘረኝነትን አንፀባራቂ በመሆኑ የሚወገዝ ነው ፡፡ ሁለተኛው ተፈጥሯዊ በመሆኑ የምንኖርበት ህይወት ነው። ከዚህ አንፃር በእኛ ሀገር የመጀመርያው ″ የእነሱና የእኛ ″ የሚል ያውም በዘርና በጎሣ ላይ የተመሰረተ አመለካከትና አስተሳሰብ ፣ዛሬም ድረስ መርዛማ ፍሬው አልተወገደም 27 ሲደመር …. ፡፡

ዛሬም ድረስ ጥቂት የማይባሉ ግለሰቦች እና ስብስቦቻቸው  “ በቡድን ስም “ አውዳሚ  የዘረኝነት ፣የጎሣና የቋንቋ መደብ ፈጥረዋል ፡፡ በዚህም ይታወቃሉ ፡  ልዩ መታወቂያቸውም  የእኛ  የ ባላል ፡፡  (ማንነት የምትል ማነህ ?  በሬ በሬ ነው ። ላምም ላም ናት ። የበሬም ሆነ  የላም ማንነት ብሎ ነገር የለም ። የበሬም ሆነ የላም መታወቂያ  “የጋማ ከብት” ነው ፡፡ የፈንረጅ ይሁን የአበሻ ፡፡ ከብት ከብት ነው ።”ጉርጥ አደፈጠም ዘለለም ያው ጉርጥ ነው ።” ገባህ ፡፡ በቀቀናዊ አመለካከትን ከሚፀየፉ መካከል አንዱ ለመሆን ብቸኛው መንገድ፣በማንበብ ሁለገብ ዕውቀትን ማግኘት ። ከልብ  ማዳመጥ ና በራስ መንገድ  ማሰብ መሆኑንም ተገንዘብ።  )

ተጨማሪ ያንብቡ:  አወጋን በወልቃይት ጎሮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የአማራ ልጆች እንዳይማሩ መከልከላቸውን ገለጸ

ለመሆኑ ቋንቋ ምንድነው ? የመግባብያ መሳርያ አይደለም እንዴ? ቋንቋ መግባቢያ ነው ። ቋንቋውን ለፈለሰፈው  ማህበረሰብም ባህል ነው ። ከዛ ማህበረሰብ ጋር  ተደማምጦ ለመሥማማትም ሆነ ላለመሥማማት ቋንቋውን ማወቅ ያሥፈልጋል ።ሰው በምድር ቆይታው  ሃሳብም ሆነ ሌሎች ነገሮችን ከሌሎች ለማግኘት ፤ ለመግዛትና ለመሸጥም ጭምር ቋንቋን ማወቅ  ግዴታው ነው ።…

ሰዎች በየዕለቱ የተለያየ ቋንቋ ከሚናገሩ ሰዎች ጋር በኑሮ እና በሥራ አስገዳጅነት በየትም ሥፍራ በሚገኙበት ጊዜ፣ “ጉዳያቸውን ለመተኮስ” የሚግባቡበት  ቋንቋ ያስፈልጋቸዋል። አንድ ግለሰብ ፣ ለራሱ ጉዳይም  ሆነ ለራሱ ላልሆነ  ጉዳይ ቋንቋውን ወደማያውቀው አካባቢ ወይም አገር ቢሄድ የሚሄድበትን አካባቢ እና ሀገር ሰው ቋንቋ ካላወቀ ፣ጉዳዩን በቀላሉ ለመከወን ይቸግረዋል።

ለምሳሌ አንድ የትግሪኛ ቋንቋን ህሊናው መተርጎም የማይችል  (በአንዳንድ ስብሰባዎች “ይህንን ቋንቋ የማትሰሙ እጃችሁን አውጡ ።” ሲባል እሰማለሁ ። ሰው ጆሮው እስካልታመመ ወይም ሲወለድ የማይሰማ ሆኖ እስካልተወለደ ድረስ እንዴት “የማይሰሙ” ተብሎ ይጠየቃል? )   የአማርኛ ቋንቋ  ተናጋሪ ፣ የትግሪኛ ተናገሪዎች ብቻ ባሉበት ቢገኝ፣ የሚፈልገውን ነገር በቀላሉ ለማግኘት ይከብደዋል ።ትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪውም እንዲህ ዓይነቱ ችግር በአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ  ገጠር ቀበሌዎች ቢሄድ ተመሳሳይ ችግር ያገጥመዋል ። በተቃራኒው አያት፣ምጅላቶቹ ኦሮሞዎች የሆኑ ህፃን፣ትግሪኛ ተናጋሪዎች ጋር ካደገ በኋላ  ፣” ጆሮህን ልንቆርጥህ ነው ። ”ብለው በኦሮምኛ እየተናገሩ ያለመልክት ቃንቋ ቢያሥፈራሩት  በአንጎሉ ተርጉሞ  ምን እንዳሉ መረዳት አይችልምና በንግግራቸው ሊሥቅ ይችላል ። ሌላውም ቋንቋ ተናጋሪ በተመሳሳይ መልኩ ቢያድግ እንዲሁ ነው።

በአጭሩ ፣ቋንቋን በመወለድ አናገኘውም ። በደም ፣በጅን (በዘር) አይወረስም። እንዲሁም ቋንቋ ከመግባቢያነት የዘለለ ትልቅ ፋይዳ የለውም ።አንዱ ቋንቋም ከሌላ ቋንቋ አያንስም ። አይበልጥም ። ሁሉም ቋንቋ ተወራራሽ ብቻ ሳይሆን፣ የሚፈጠር፣ የሚያድግ፣የሚጎለምስ፣ ዓለም አቀፍዊ ሊሆን የሚችል ነው ።አንዳንዱ ቋንቋ የሚቀጭጭ እና እየሠለለ  የሚሞት ነው ። የሞተ ቋንቋ አንድ ጥቀስ ብባል ጋፋትኛን እጠቅሳለሁ ። በመላ ኢትዮጵያ መግባብያ ለመሆን የበቀ ኢትዮጵያዊ ፊደል ያለው ቋንቋ ጥቀስ ብባል ደግሞ አማርኛ እላለሁ።  ዛሬ ፣  የአማርኛ ቋንቋ በብዙ ነገር ያደገ እና ያልታወጀለት   ብሔራዊ ቋንቋ ሆኗል። በብቸኝነት ግን ራሱን አላሳደገም ። በውስጡ ከሀገር ውሥጥም ሆነ ከውጪ  ቋንቋዎች የወረሳቸው ቃላቶች በጣም ብዙ ናቸው።

የትግሪኛ ቋንቋ ፊደላት በአማርኛ ፊደል ዝርዝር ውስጥ የተካተተ ነው ። አማርኛ ቋንቋ ዲቃለ ቋንቋ ነው ።በውስጡ ብዝሃነትን ያቀፈ ነው ። የተዳቀለ ነው ። አንዳንድ” አለአሳቢያን “ ግን ሁሉንም ነገር ወደ ዘር የመውሰድ አባዜ ሥላላቸው ቋንቋውን ለአንድ አማራ ለተባለ ጎሣ ሰጥተውታል ።ይሄ ደግሞ አለማወቅ የፈጠረው ነውና ለማወቅ ቢተጉና ስለቋንቋ ሰፊ ምርምር ያደረጉትን በመጠየቅ ቢማሩ መልካም ነው ። እንጊሊዘኛን እንግሊዞች ቢፈጥሩትም የአሜሪካኖቹም ቋን ነው ። ደሞም የዓለም ሁሉ መግባብያ እየሆነ ነው ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አርቲስት በኃይሉ መንገሻ አረፈ

የእነሱ ና የእኛ በሚል የዘረኝነት መደብ ላይ የተመሰረተ  የቋንቋ ምልከታ፣ከፋፋይና አውዳሚ ነው። የምለው ከዚህ እውነት ተነስቼ ነው ። ሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች   የኢትዮጵያ  ዜጎች ሀብት ናቸው ።ሊያውቃቸው የሚችልበት መንገድ ቢፈጠርለት ተጠቃሚ እንጂ ተጎጂ አይሆንም ። “ በቋንቋ የነገሡ ” የሀገሬ  ፖለቲከኞች ግን ፣ ይህ እውነት ፈፅሞ አይዋጥላቸውም ። ”ወደሥልጣን መምጫ እና ሳይለፉና ሳይደክሙ የአገርን ሀብት በመመዝበር በአጭር ጊዜ የመበልጸጊያው ብቸኛው መንገድ  ቋንቋ   በመሆኑ ፣  አንዳንድ የዋህና ከራስ በላይ ነፋስ ብለው የሚያስቡ ምሁራን ሳይቀሩ  ቋንቋን   ለሆዳዊ  ዓላማቸው ማስፈፀሚያ  ሲያውሉት ይስተዋላሉ። “በእነሱ እና በእኛ ።” ትወራ የአንድ አገርን ዜጋ በመከፋፈል በቋንቋ በመከፋፈል  ክልልን በአንድ ቋንቋ ብቻ ለማስተዳደር ይጥራሉ ። …

ወዳጄ እስካወቅኸው ድረስ በዓለም ላይ ያለ ቋንቋ ሁሉ የሰው ቋንቋ ነው ። ሁሉም  ቋንቋ መግባብያ  ነውና ገንዘብህ ብታደርገው ይጠቅምሃል ። ቋንቋ የአንድ ጎሣ ሀብት ብቻ አይደለም ። በሥምምነት እገሌ የሚባል  መታወቅያ (idntity ) ሊሰጠው    አይገባም። ሁሉም ጎሣ ፣የሁሉንም ጎሣ መግባብያ ቋንቋ መናገር ባይችልም፣ ሲወራ ወደ ቋንቋው ከተተረጎመለት መረዳት አያቅተውም ። …የአማርኛ  ቋንቋን ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁላ ካወቀና በቋንቋው እሥከተግባባ ግዜ ድረሥ ፣ አማርኛ የእሱም ቋንቋው ነው ። ሌላውንም አገርኛ ቋንቋ እንዲሁ ። ( ኦሮሚኛን ፣ ትግሪኛን ሱማሊኛን ወዘተ አንድ ሰው በትምህርት ቢያውቅ ምን ችግር አለው ? )

እንግሊዘኛ በአብዘኛው የዓለም ህዝብ ሥላወቀው ዓለማቀፋዊ ቋንቋ እንደሆነ አሥተውሉ ። (በአፍሪካም ጥቂት  በማይባሉ አገራት ብሔራዊ ቋንቋቸው እንጊሊዝኛ ነው ።  ) ፈረንሳይኛ ና አረብኛም እንዲሁ ። ታዲያ የእኛ የኢትዮጵያውያን ብቻ የሆነውን ልንኮራበት የሚገባንን ቋንቋ ለምን እንጠላለን??? አማርኛን በሔራዊ  ቋንቋችን አልፎም አፍሪካዊ ቋንቋ  ለማድረግስ  ለምን ቀና ልብ አጣን ? ከላይ በጠቀሥኩት” የእነሱ ና የእኛ” በሚል ኩንን  ምክንያት  እና መልካምና ጠቃሚ ሃሣብን ከሌሎች ወንድሞቻችን መቀበል ሞት መሥሎ ሥለሚታየን እውነትን መቀበል ስለሚያዳግተን አይደለምን???።

እውነትን መቀበል ካዳገተንና  ሆዳችን  ከሀገር ተረካቢው ትውልድ ከበለጠብን ፣ ለምን አንድ ፊቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ አረብኛ ይሁን አንልም?? አለቃ ለማ (የአብዬ መንግሥቱ ለማ አባት) ያሉትን ነው የደገምኩት።(እሳቸው ናቸው ጥራዝ ነጠቆች አማርኛ አልደረጀም፣እንደእንግሊዘኛና ላቲን አልሆነም እናም መቀየር አለበት ብለው ሲያስቸግሩ እና በሤራ ቋንቋውን ሊያጠፉ ሲሞክሩ፣ “የአማርኛን ፊደል ከጠላችሁ …ለምን አረብኛ  ፊደል አይተካውም  ያሉት ። ” አንብቡ ዝርዝሩን ልጃቸው አብዬ መንግስቱ ለማ ፤ “ በትዝታ ዘአለቃ ለማ “ በተሰኘ መፀሐፋቸው ፅፈውታል።)

እናንተ ሰዎች ፣ የነገ አፈሮች ፣ አትሳቱ  ፤ ቋንቋ አያስፈራችሁ ። የነሱ ና የእኛ በማለት ልዩነትን አትዘምሩ ። ቋንቋ ሰው ከሰው ጋር የሚግባባበት የሰው ዘር በሙሉ ሀብት ነው ። “ የእኛ  ና የእነሱ የሚል “ የዘረኝነት መደብ ” ወይም መታወቂያ የለውም ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.