ትናንት ዱቄት ያሉን ዛሬ አለት ለሚሉን !

ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ሲባል እንዲሁ የአንድ ዘመን ገጠመኝ ይመስለን ነበር ፡፡ ሆኖም ላለፉት አራት አመታት ኢትዮጵያ በዘመኗ ያላየችዉ ወይም ያልገጠማት አንዲያዉም መስከረም ሳይጠባ ሳይሆን መሽቶ እስኪጠባ  ሶስት ጊዜ ጉድ መስማት ተለምዷል፡፡

ይህም ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም የሚለዉን በኢትዮጵያ ሰማይ  ስር ሳይነጋ የተነገረ ሳይረፍድ እንደጤዛ ሲጠፋ ማየት  ዛሬ በኢትዮጵያ ጉድ ሳይሰማ መሽቶ አይነጋም ቢባል ቢያንስ እንጂ አይበዛም ፡፡

ኢህአዴግ ከስሟል ፤ የኢህአዴግ ግንባር ድርጂቶች ወይም ጉልቾች  ከስመዋል  በኢህአዴግ መተዳደሪያ ህግ -ህገ-አህአዴግ መሠረት ያልተካሄደ ምርጫ በሚል በትህነግ እና በብልፅግና መካከል በህግ የበላይነት ማስከበር እና መከበር ስም ፍጥጫ ዉስጥ ተገባ ፡፡ በዚህም በሽብርተኝነት የተመዘገበዉ ትህነግ ወደ ጦር አምጣ ህልም ገባ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ  የርኩስ መዉጊያ በማድረግ በተለይም በብዙኃኑ የዓማራ ህዝብ ላይ የመጀመሪያ እና የመጨረሻ የትህነግ  ጠላት ሆኖ ለዘመናት የሚፈረጀዉ እና የመከራ ቀንበር ተሸካሚ ሆኖ እንዲቀጥል ሆኗል፡፡

ለግማሽ ክ/ዘመናት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እና የዓማራ ህዝብ በኢትዮጵያዊነት የደረሰበትን ዕንግልት ፣ስደት እና ሞት ዕልባት ባልተሰጠበት የሞተዉን ትቶ የገደለዉን አንስቶ ምን አይነት ዘላቂ መፍትሄ ሊያስገኝ አይችልም ፡፡

ለኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፣ሉዓላዊነት እና የኢትዮጵያዉን  በተለይም ኢትዮጵያን እንደ ድሪቶ ለመቀራመት ለረጂም ዓመታት ለሚያሴሩት አፍራሽ ኃይሎች  የማይታኘክ  አጥንት የሆነዉን የዓማራ ህዝብ ተሳትፎ አለመኖር ከዕዉነትነቱ እና ገቢራዊነቱ አጠያያቂ ነዉ ፡፡

በመላ አገሪቱ በኗሪነቱ እና በዜግነቱ ለዘመናት በግፍ  የተገፋዉ የዓማራ ህዝብ ዳግም በነዚህ ሁለት መሰረታዊ የዜግነት መብቶች የአመታት የመከራ ጅረት በሚወርዱበት ሆኖ ሳለ ዛሬም ጥቃቱን እና ሞቱን በማቅለል ዛሬም ለዳግም በደል የሚዳርግ ዳር ዳርታ ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይድረስ ለወዳጄ....

የበነነ ዱቄት አለት ከሆነ  የተታደፈነ ዕሳት እንደነበር ከዓመታት በፊት የተባለዉ የበነነ ዱቄት መባሉ ስህተት እና ዳግም ታሪካዊ ክስተት ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያዉያን በተለይም ብዙኃን ዓማራ ቀድሞም በፀረ-ኢትዮጵያ አፍራሽ ኃይሎች ከመቀሌ አስከ ቦሌ በግንባር ቀደም ጠላት በማድረግ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ዓማራን በደም እና በአጥነቱ መስርቶ ፣በጥበብ አስማምቶ  ፣ በህይወት መስዋዕትነት አቅንቶ ዕትብቱ በተቀበረባት እናት አገር ኢትዮጵያ ባይተዋር፣ ሟች እና ስደተኛ ሆኖ በሚገኝበት እንዲሁም የህልዉና እና የሉዓላዊነት ትግል እያደረገ ባለበት ዱቄት አለት አድርጎ ዕሳቱን አመድ በማድረግ ዕዉነተኛ እና ዘላቂ ብሄራዊ አንድነት እና ሉዓላዊነት ይጠበቃል ማለት ዘበት ነዉ ፡፡

ትናንት ዱቄት ያሉን ዛሬ አለት ለሚሉን እንዴት መተማመን ሊኖር እንደሚችል ማሳያ ባይኖርም ገዳይ ከሟች ጋር ባልተደረገ ስምምነት እና ዕርቅ ብሄራዊ መግባባት ይሰፍናል ማለት አሽሙር ነዉ  ፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛ ብሄራዊ ክህደት እና ወንጀል የፈፀሙት ብሄራዊ እና ታሪካዊ ጠላቶች ከመጠየቅ እና ከመከሰስ ይልቅ ባለፍርድ ማድረግ ሟቹን እና ተበዳዩን ብዙኃን ኢትዮጵያዉያንን እና ኢትዮጵያን መርሳት ብሎም ሁሉም ለአገራቸዉ እና ለህዝባዉ ሉዓላዊነት እና ህልዉና የሚተጉት በስደት ፣ በሞት እና በዕስራት በሚማቀቁባት አገር እነኝህን አካላት የሚያሳትፍ ዕርቅ ሳይኖር የሚታለፍ ቢሆን ይህ ልባዊ ዕርቅ ሳይሆን የትዉልድ የሠላም እና አብሮ መኖር ጠንቅ እንዳይሆን ሁሉም ይመለከታኛል ባይ ልብ ሊለዉ ይገባል ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ !

Allen Amber!

1 Comment

  1. ጎበዝ እኔ ለብርሀኑ ጁላ አዘንኩ በድርድር ስም ትላንት እያባረረ የገረፈው ታደሰ ወረደ ፊት ለፊት ቁጭ ብሎ ዛሬም በድርድሩ ታደሰ በፈለገው መልኩ ውይይቱ ሲቋጭ። ሲጀመር የአንድ ቀበሌ ሽፍታ የአንድን ሉዋላዊ አገር ኤታማዦር ሹም ቡእኩልነት በአንድ ጠረቤዛ ላይ ቁጭ ብሎ ስራዊቱን እምሽክ አድርጎ ከበላ ድርጅት ጋር መደራደር የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት ሞራል ምን ያህል እንደሚጎዳ እነ ብርሀኑ ጁላ የተረዱ አይመስልም። የፖለቲካ ክፍሉ ሞራል የሌለው ቀማኛና ለተቀማጠለ ኑሮው የሚሰራ እንጅ ለሀገር ዋጋ የማይሰጥ ስብስብ ነውና ሲጀመር ለሶስተኛ ዙር ሲፈነጭብን የመከላከያ ሚንስትር የትህነጉ አብረሀ በላይ ነበር የጉድ ሀገር። ለኢትዮጵያ ሰራዊት የሞት ሞት የመከላከያ ሰራዊቱን ያረዱ ትግሬዎች ዛሬም የመከላከያ ሰራዊቱ አባል እንዲሆኑ ስምምነቱ ያስገድዳል። ጎበዝ ኢትዮጵያ መሪ አላትን?

Leave a Reply

Your email address will not be published.