ለዘላቂ ሰላም ትክክለኛ የዐማራ ሕዝብ ወኪል ተደራዳሪ ሆኖ እንዲቀርብ ማመቻቸት ግድ ይላል!

ብልፅግና ከሕወሓት ጋር በሚያደርገው ድርደር ዐማራን በመወከል በተደራዳሪነት የተመረጡትና በግለሰብ ደረጃ ራሳቸውን የወከሉት አቶ ቴዎድሮስ ትርፌ፣ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ፣ ጀኔራል ተፈራ ማሞና ዶክተር ወንድወሰን አሰፋ ተደራዳሪ ሆነው ለመቅረብ ፍቃደኛ በመሆናቸው ጥሩ ጅምርና መበረታታት ያለበት እንደሆነ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ያምናል።

ሕወሓት በ1983 ዓ.ም. ሥልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ በፈላጭና ቆራጭነት የዐማራ ርስቶችን ወልቃይትና ራያን ከጎንደርና ከወሎ “ትግራይ” ብሎ ለሰየመው አዲስ ክልል ዘርፎ ሲወስድ፣ መተከልን ጎጃም ዘርፎ አዲስ ለፈጠረውና ለወደፊት ወደትግራይ ሊስበው ላሰበው “ቤኒሻንጉል ጉሙዝ” ሲመድብ፣ እንዲሁም ከ80 % በላይ ዐማራ የሚኖርበትን ደራን ከሽዋ “ኦሮሚያ ክልል” ወዳለው ክልል እንዲካተት ማድረጉ አይዘነጋም።

መዘንጋት የሌለበት፣ ትናንት ለወያኔ አድሮ የወያኔን አከላለልና በዐማራ ሕዝብ ላይ የሚሰነዘረውን የጥላቻ ትርክት ከነግሳንግሱ ተቀብሎ ሲያስፈፅም የነበረው ብአዴን/አዴፓ ዛሬም ለአዲሱ ጌታ ለኦሮሙማ ብልፅግና አድሮ ጉዳይ አስፈፅሚ ሆኖ እየሰራ ነው። በመሆኑም የአዴፓ ተወካዮች የድርድር ቡድኑ አባል በመሆናቸው መፍትሔ ያመጣል ብሎ የዐማራ ሕዝብ አያምንም። ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅትም በሕወሓትና በብልፅግና ድርድር ብቻ እውነተኛ የዐማራ ውክልና ሳይኖር፣ ጦርነቱ ቁሞ ዘላቂ ሰላም ይገኛል ብሎ አይጠብቅም።

በትግራይ ወያኔ እና በኦሮሚማ/ብልጽግና መካከል ያለው ጦርነት መሰረቱ የመርህና የአገር ጥቅምን ለማስጠበቅ በሚኖር ልዩነት የተፈጠረ አይደለም። የኢትዮጵያን ህዝብ የከፋፈለ፣ ሰላም ያሳጣ፣ ሁለንተናዊ የአገር እድገትን ያቀጨጨ፣ እና ህዝብ በአንድነት ቆሞ ካላስወገደው ወደፊትም ወገንን ከወገኑ እያፋጀ የሚቀጥለው የአፓርታይድ ህግመንግስት ፈጣሪና ጠበቃዎቹ የሆኑትን ወያኔና ኦነጋውያንን ጦርነት የከተታጨው ሥልጣን ብቻ ነው። አሁንም በድቡብ አፍሪካ ተደረገ በተባለው የትግራይ ወይኔና የኦሮሚማ/ብልጽግና መንግስት በዋናነት የተስማሙበት ይኸው የአፓርታይድ ህገመንግስትና ሙሉ በሙሉ ማስከበር ላይ ነው። በነዚህ ሁለት የዘር አጥፊ ፋሽስታዊ ድርጅቶች መሀከል በተደረገ የሥልጣን ጦርነት ዋንኛ ተጎጂዎች የሆኑት የዐማራና የአፋር እውነተኛ እና ህዝባዊ ወኪሎች ያልተገኙበት ድርድር ዘላቂ መፍትሄ አያመጣም። የድርድሮችን ጭብጦች ለመረመረ ወያኔ “ዶቄት” ሆኖ ከመጥፋት የፖለቲካ ኃይልነቱን ማስቀጠሉ ብቻ ሳይሆን የሥልጣን ተካፋይ የመሆን እድል አግኝቷል፤ አብይ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የውስጥ ስደተኞች በላይ፣ በሺዎች በቀያቸው፣ በቤተ እምነታቸው፣ በቤታቸው ውስጥ ከሚጨፈጨፉት በላይ፣ በአጠቃላይ የህዝብ ሰላምን እና የአገር ዳንድንበር ከማስጠበቅ በላይ የሚሳሳለትን ስልጣኑን እውቅና የሚሰጥ ወያኔን አግኝቷል። ከዚህ በፊት ከአንድ አመት በፊት (Sep 26, 2021) ባወጣው መግለጫው የሚከተሉትን ነጥቦች አካቶ ነበር።

  • ወያኔ በወረራ ከያዛቸው ግዛቶች በሞላ በድል ተሸንፎ ወይንም በራሱ ፈቃድ ለቆ ከ እ ኤ አ 1970 ዎቹ በፊት ወደነበረው የትግሬ ክፍለ ሀገር ሳይመለስ፣ ይህም ማለት፣ ወያኔ በስልጣን ዘመኑ በወረራ ከወሰደው የአማራ ርስት ከወልቃይትና ከራያ ወጥቶ ለቆ ከተከዜ መልስ ሳይሰበሰብ አንዳችም ድርድር መደረግ የለበትም፤ እንላለን።

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  አገር አውዳሚውና ከፋፋዩ የኢህአዴግ/ብልፅግና አገዛዝ ሀገሩንና ወገኑን ከጥፋት ከሚታደገው ፋኖ ላይ አይኑንም እጁንም ያንሳ!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥቅምት ፬፣ ፪ሺ ፲፭ ዓ.ም. (Oct. 4, 2022) ቅጽ  ቁጥር

 

  • በወረራው ምክንያት በዐማራው ላይ ለደረሱ ግድያዎች፣ መፈናቀሎች፣ የንብረት ውድመት ሁሉ ተጠያቂው ሙሉ በሙሉ ወያኔ በመሆኑ በኢትዮጵያ ያሉ ንብረቶቹ – ኤፈርት፣ ባንኮች፣ ኢንሹራንሶች፣ የመጓጓዣ ተቋሞችና ሌሎችም ድርጅቶች ተወርሰው ለዐማራው ካሳ ክፍያ እንዲውሉ በጥብቅ እንጠይቃለን። ይህ እስኪፈጸም ድረስ በተቀዳሚ በዐማራነት የተደራጁ ድርጅቶች ጉዳዩን ወደ ግብ እንዲያደርሱ ጥሪ እናቀርባለን።

 

  • ወያኔ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ድርጅት ማክተም ይኖርበታል። እንዲሁም አጋሩ ኦነግ በጋርዮሽ በዐማራው ላይ እይፈጸሙ ያሉት ኢሰብአዊና እጅግ ሰቅጣጭ ወንጀሎች የኢትዮጵያ ሕዝብ ተጠያቂ እንዲያደርጋቸውና በታሪክ ለመፋረድ እርምጃ መወሰድ አለበት እንላለን። ወያኔና ኦነግ በአሸባሪነት በሚንቀሳቀሱባት ኢትዮጵያ ዜጎች ህልውና እና ሰላም ሊያገኙ ስለማይችሉ፣ እነዚህ ድርጅቶች በአፋጣኝ እርምጃ እንዲወገዱ እንጠይቃለን።

 

  • ዐማራው ጠላቶቹ እንማን እንደሆኑ የለየ ቢሆንም፣ ዛሬ እሱን የሚወክለውና ህልውናውን ሊታደገው የሚችል ኃይል አለመፍጠሩ እያስጠቃው ነው። ዐማራው የወገኖቹ ደም፣ ደመከልብ ሆኖ እንዳይቀር ብሎም ህልውናውም እንዳይጠፋ በብሔር ማንነቱ ተደራጅቶ መፋለም ይኖርበታል። በመሆኑም የዐማራ ሕዝብ ከወራሪዎችና ከጽንፈኞች ራሱን ሊታደግ የሚችለው ቀደም ሲል እንዳስደመጥነው ጥሪ በጎበዝ አለቅና በፋኖዎች ታቅፎ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ሲችል ብቻ ነውና ተደራጅቶ በቁርጠኝነት መፋለም ይኖርበታል።

በኢትዮጵያ ፍትህን ከማውረድ፣ በጦርነቱ የተጎዱ ወገኖችን ከማቋቋም፣ ባጠቃላይ ዘላቂ ሰላምን ከማስፈን በተጻረረ መልኩ ወያኔን ከመጥፋት ማትረፍ፤ ወያኔ አገርን በማራቆት በ27 አመታት ያግበሰበሰውን ሀብት ወያኔ በቀሰቀሰው ጦርነት ለተጎዱት ማቋቋምያ ሳይሆን የወያኔ መሪዎች እንደፈለጉ የሚሆኑበትና በፈለጉ ግዜ አገርና ወገንን የሚያደሙበት እንዲሆን መፍቀድ፤ እንደነ ስብሐት ነጋ አይነት የሀገር ክህደት የፈጸሙ የጦር ወንጀለኞች ተንፈላሰው እቤታቸው እያደሩ እንደነ ፋኖ ዘመነ ካሴ አይነት ሀገርና ወገንን የታደጉ በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ የፋኖና የአማራ ልዩ ኃይል አባሎች እየተሳደዱ ወይም በእሥርቤት እንዲማቅቁ አድርጎ ማሰቃየት፤ የአብይን ሥልጣንናን የኦሮሚማን የበላይነት ማረጋገጥ እና ባጠቃላይ በኢትዮጵያ ላለፉት ሦስት አስርት አመታት በላይ ላየነው የቁልቁለት ጉዞ መሰረት የሆነውን፣ በተለይም አማራን በጠላትነት ፈርጆ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀለቾ ሰለባ ያደረገውን የአፓርታይድ ህገመንግስት ቀጣይነትን ማረጋገጥ፤ የወያኔ እና የአብይ/ኦርሚማ አገዛዝ የደቡብ አፍሪካ የድርድር ውጤትና ግብ ነው። ይህ ደግሞ በምንም መንገድ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን አያመጣም። በተለይም አማራውም ህልውናው እስኪረጋገጥለት ድርስ ትግሉን መቀተሉ ታሪካዊ ሀቅ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ላለው የዘር ማጥፋት ወንጀል (Genocide) መንግስት ሙሉ ኃላፊነቱን ሊወስድ ይገባል!!! (መኢአድ)

ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘላቂ ሰላምን ማስፈንን በተመለከተ የአማራው ጉልህ ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑ ሊታመንበት ይገባል። ለዚህም ሁሉም በዐማራ ጉዳይ ባለድርሻ አካላትነት የተደራጁና ተቀባይነት ያላቸው የሲቪክ ማኅበራት፣ በዐማራ ህዝብ ጥቅምና ህልውና የማይደራደሩ ታዋቂ ግለሰቦችና ምሁራን፣ በአጠቃላይ በውጪም በውስጥም ያሉት በጋራ በመምከር እነዚህን አራት ለመደራደር ፍቃደኛ የሆኑ ግለሰቦች የሚደግፍ፣ አቅጣጫ የሚያሳይና ለውጤት እንዲበቁ የሚያደርግ ግብረ ኃይል እንዲቋቋም እንመክራለን። በዚህ አጋጣሚ ዐማራ ተሰባስቦ በአንድ እንዲመክር ይህ አጋጣሚ ከተፈጠረ፣ ለመቀራረብ ስለሚረዳ፣ ተቀራርበን በአንድ ልብ አስበን ከተንቀሳቀስን፤ ዐማራው ከሚወርድበት መከራና ከፈፅሞ ጥቃት ለመታደግ እንችላለን ብለን ስለምናምን በአስቸኳይ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ስራው እንዲጀመር ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ይመክራል። አሁን ያለንበት ሁኔታ የአማራውን አለመደራጀት አጉልቶ ያሳየ ሲሆን በመርህ ላይ የቆሙና በህዝብ የሚታመነ የአማራ ፖለቲካ ኃይል ኃይሎች መፍጠሩ ለነገ የሚባል አለመሆኑን ነው።

ትክክለኛና ዘላለማዊ ሰላም በቀጠናው እንዲሰፍን ካስፈለገ ደግሞ ጦርነቱ በአስቸኳይ ቆሞ፣ ወንጀለኞች ለፍርድ ቀርበውና የሕወሓት ፅንፈኛና ፋሽስታዊ ርዕዮተ ዓለም የእኔ ለሚለው የትግራይ ሕዝብ ጥላቻን እየጋተ የዐማራና የትግራይን ሕዝብ ቢያናቁርም፣ ሕወሓት የትግራይን ሕዝብ አይወክልምና የትግራይና የዐማራ ሕዝብ ለዘመናት በሃይማኖት፣ በሥነ ልቦናና በጋብቻ የተዋሀደና የተሳሰረ በመሆኑ፣ የትግራይና የአማራ ሕዝብ እንደቀደመው ሁሉ ሰላሙን አውርዶ ከዘረኝነት በፀዳ እንደልብ ተንቀሳቅሶ የሚኖርበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።

 

ኢትዮጵያ አገራችን በተባበሩ ልጆቿ ትግል፣ በአገር ጠሎቹ የተደቀነባትን አደጋ ትሻገራለች!

1 Comment

  1. I Mognu

    ሳስበው ሳስበው የአማሮች ነገር ይገርመኛል። አልፎ ተርፎም ያሳዝነኛል። ለምን ይገርመኛል ፧ ለምን ያሳዝነኛል፧ ላስረዳ። እስኪ T.G. የጻፈውን ኣስተያየት ተመልከቱ፤ አማራው ከትህነግና ከኦሆዴድ ብልጽግና የሚያገኘው ነገር የለም ይለንና መፍትሄ ስንጠብቅ ስጋቱን አካፍሎን ውልቅ ይላል። ሰውየው አማራ መሰለኝ። አማሮች በሙሉ አማሮች የአማራን የመረረ ስቃይ አሳምረው ከተነተኑ በኋላ የመፍትሄ ነገር ሲጠየቁ የለንበትም ወደማለት ያልፋሉ። ምክንያቱም በቁርጥ አማራ ክኦሮሞ መገላገል የሚችለው ራሱን በነጻነት ሲያስተዳድር ብቻ ነው ማለት ሃገሪቱን መክዳት ይመስላቸዋል። አማራ የራሱ የመከላከያ ሃይል ኖሮት ኣማሮችን ክኦሮሞና ሌሎች መጠበቅ ካልቻለና የኢኮኖሚ ነጻነቱን ከኦሮሞ መቀማት ካልቻለ በሰላም መኖርም ሆነ ማደግ አይቻለውም። T.G ይህን ሃሰት የምትል ከሆን ሃስብህን አካፍለኝ። አንድ ወዳጄ ከቀናት በፊት ይህን ጽፎ ነበር። ” ይህ የአማራ ህዝብ የኮንፌደሬሽን ጥያቄ ወሳኝ መሰለኝ። በኦሮሞ አስተዳደር ስር የአማራ ህዝብ የተሟላ ሰላምና ደህንነት አንዲሁም የኢኮኖሚ እድገት ሊረጋገጥ አይችልም። በኮንፌደሬሽን በነጻነት መሪዎቹን መምረጥ፥ ሰላምና ደህንነቱን ማስጠበቅ በኢኮኖሚ ማደግ ይቻለዋል። እስከኣሁን እንደታየው ከሆነ መሪዎች ተብዬዎቹ ኦሮሞዎች ሲጠሩዋቸው (አቤት) ሲልዃቸው (ወዴት) ባይ ናቸው። ከኦሮሞ ቁጥጥር ውጭ የሆነ አመራር የአማራን ህዝብ ሊያስመነድገው ይችላል። ከኦሮሞ ቁጥጥር ውጭ የሆነ አመራር ባለው የብሔር ፌደራሊዝም ተግባራዊ ሊሆን አይችልም። ያለፉት ሰላሳ አምስት ዓመታት ያረጋገጡት ይህንኑ ነው። የብሔር ፌደራሊዝም ይቆይ ቢባል እንኴ የተሻለ የሚሰራው በፕሬዚዳንታዊ ስርዓት እንጂ አሁን ባለው ፓርላሜንታዊ ስርዓት አይደለም የሚልው ክርከር አሳማኝ ነው። ለማንኛውም የአማራ ህዝብ መጪ እድል የሃገሪቱን መጪ እድል ይወስናል። ለዘለቄታው ከትግራይ ፣ ከኤርትራ፣ ክአፋርና ብንቫንጉል ጋር በኮንፌደሬሽን ታሳስሮ ወደፊት የሚራመድበት ኦሮሞ ደቡብን ይዞ የሚያነክስበት ጎዳና ይታየኛል።” ወዳጄ ባለው በሙሉ ባልስማማም አማራ ከኦሮሞ ቁጥጥር ነጻ አስካልወጣ ድረስ ስቃዩ አይቆምም፣ እድገትም አይኖረውም ባይ ነኝ። በጀመረው ሂደት ኦሮሞም ራሱ ክጨቋኝነት ወጥቶ ነጻ ሊሆን አይችልም። እና ለሁላችንም ነጻነት የአማራው ነጻነት ቁልፍ ነው የሚባለው ለዚህ ነው። በዚህ መንገድ ሄዳችሁ ሁላችንንም ነጻ አድርጉን። አሁን መገረሜና ማዘኔ ገባህ?

Leave a Reply

Your email address will not be published.