መንግሥት ያለጥበብ አይቆምም፤ ሀብትም ያለጥበብ አይቆይም!!! ተረት ታሪክን አያሸንፍም!!! (ፂዮን ዘማርያም)

ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)

የጫካው ጦርነት ፕሮጀክት ምስጢር ሲገለጥ፤ አንድ ሚሊዮን ወጣቶች ህይወታቸውን አጥተዋል………!እንዲሁም አንድ ትሪለየን አምስት መቶ ቢሊዮን ብር  የመሠረተ-ልማት ውድመት በሁለቱ ዓመት ጦርነት ተመዝግቦል፡፡

ኢትዮጵያ የአረመኔዎች እስር ቤት ሆናለች!!!

ግልፅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

‹‹ወገኞቼ! ነገሬን አድምጡኝ፤ እኔ ጥበብን እሻለሁ፤ (አንስ እፈቅድ ጥበብ) ልቤም እውቀትን ትፈልጋለች፤ (ወልብየኒ ተኅሥሣ ለአእምሮ፤በጥበብም ፍቅር ተነድፌአለሁ፤ (እስመ ተነደፍኩ በፍቅረ ጥበብ፤) በጥበብ ገመዶችም ተይዣለሁ፤ (ወተሰሕብኩ በአሕባለ አእምሮ፡) ጥበብ ከወርቅና ከብር መዛግብት (ሣጥኖች?) ትሻላለች፤ ጥበብ  በምድር ከተፈጠሩት ሁሉ ትበልጣለች፤ ጥበብን ከሰማይ በታች በምን ይመስሏታል? ከማር ትጣፍጣለች፤ ከወይን ታስደስታለች፤ ከጸሐይ ታበራለች፤ ከጣፈጡ  ምግቦች  ይበልጥ ታጠግባለች፤ ለልብ አስደሳች ለዓይኖች መብራት፤ ለእግር ቅልጥፍና ለደረት ጥሩር፤ ለራስ አክሊል፤ ለአንገት የወርቅ ማርዳ፤ ለወገብ መታጠቂያ፤ ለጆሮ ማዳመጫ፤ ለልብ ብልሃት ለምሁራን ትምህርት፤ ለልበኞች መጽናኛና ለሚፈልጉ ክብር ሰጪ ናት፡፡ መንግሥት ያለጥበብ አይቆምም፤ ሀብትም ያለጥበብ አይጠበቅም (አይቆይም)፤ እግርምያለጥበብ በቆመበት አይጸናም፤ ልሳንም ያለጥበብ የተናገረው አይወደድም፡፡

ጥበብ ከንብረት ሁሉ ትሻላለች፤ ወርቅና ብር የሰበሰበ ያለጥበብ አይጠቅመውም፤ ጥበብን የሰበሰበ ከአእምሮው ማንም አይቀማውም፤ ሰነፎች የሰበሰቡትን ጠቢቦች ይበሉበታል፤  በበደለኞቹ ክፋት ቅኖች ይመሰገናሉ፤ በሰነፎች ስሕተት ጠቢቦች ይወደዳሉ፡፡

ጥበብ ልዕልትና (ሀብታም) ነች፤ እንደእናት እወዳታለሁ፤ እሷም እንደሕጻንዋ ታቅፈኛለጭ፤….  ›› …………..(1)

የኢትዮጵያ ገጽታ ጦርነት፣ ርሃብ፣ በሽታና ስደት በአንድ በኩል፣ ሌላዋ ገጽታዋ ደግሞ ፓርኮች፣ ፋውንቴኖች፣ ስው ሰራስ ሐይቆችና ግድቦች፣ ቤተመንግሥት፣ ወንዞችና የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት፣ ስማርት ሲቲ የጫካ ፕሮጀክት፣

ተጨማሪ ያንብቡ:  አጽማቸውን የፈለሰው መላከ ብርሃን አድማሱ  ከአምስቱ ዘመን  ተጋድሎ በኋላ   ክፍል አንድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዘመን  ከ2022እኤአ የእርቁ ስምምነት ከተፈረመ በኃላ የተገለፀ የጫካው ፕሮጀክት ምስጢር ሲገለጥ፤ አንድ ትሪሊየን ብር ወጪ  ሚገነባ ስማርት ከተማና ቤተ-መንግሥት፣ 3700 ሔክታር የግንባታ ቦታ ያካትታል፤ በዚህ ፕሮጀክት ሁለት ቢሊዮኝ ደላር በዓመት ይገኛል፡፡ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ወደፊት በሙሉ አቅሙ ሰርቶ ኤሌትሪክ ወደ ጎረቤት ሃገሮች ተሸጦ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስገኝ የዓለም ባንክ መረጃ ገልፆል፡፡

የኢትዮጵያና ትግራይ የጫካው ጦርነት ፕሮጀክት ምስጢር ሲገለጥ ደግሞ፤ አንድ ሚሊዮን ወጣቶች ህይወታቸውን አጥተዋል…! የመሠረተ ልማቶች ቁሳዊ ውድመት ደግሞ አንድ ትሪለየን አምስት መቶ ቢሊዮን ብር ኪሳራ በሃገሪቱ ላይ ደርሷል፡፡ ወያኔ ኢህአዴግ በኢፈርት ስም በሃያ ሰባት ዓመት አንባገነናዊ አገዛዙ ዘመን ከኢትዮጵያ ህዝብ እየዘረፈ የገነባው ኢፈርት የግል ኃብቱ ኃብትና ንብረት ወደመ፡፡ የአብይ የአራት አመት መንግሥት ኦነግ ኦህዴድ ብልጽግና   አረመኔዊ ሰው አራጂ ስርዓት ዘረፋ ደግሞ ከወያኔ ዘረፍ አስር እጅ አስከንዱቷል፡፡ ከወያኔ ብልፅግና መማር እንዴት ተሳነው!!! ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት መውደሙ በዓይናችን አይተናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በብዙ ሽህ አመታት ታሪክ ያላት ሃገራችን ህዝብ በእኩልነት ያለአድሎ እንዲያስተዳድሩ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ በእጆ መዳፍ ሥር ይገኛል ቁሳዊ ልማት ግንባታዎ  ለጉድ ነው ፓርኮች፣ ፋውንቴኖች፣ ስው ሰራስ ሐይቆችና ግድቦች፣ ቤተመንግሥት፣ ወንዞችና የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት፣ ስማርት ሲቲ የጫካ ፕሮጀክት አስደሳች ነው…አማላይ ነው!…ላንቲካ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የስብዓዊ ልማት ግንባታዎ ግን አናሳ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የአረመኔዎች እስር ቤት ሆናለች!!! ስው የሚታረድበት፣ ሰው በህይወቱ  የሚቃጠልበት፣ ሰው ተዘቅዝቆ የሚሰቀልበት፣ ሴቶች የሚደፈሩበት፣ ህፃናቶች የሚገደሉበት፣ የጦር ወንጀለኞች የሚፎልሉበት፣ የዘር ፈጆች የሚያቅራሩበት፣ እናት ደፋሪዎች፣ የተማሩ የዘር ጋንግስተሮች መንጋውን እየመሩ ሰው ይገላሉ፣ አገር ያቃጥላሉ፤ ላንባው ተነቃነ!  ህግ የለም፣ ሥርዓት የለም፣ ወታደርና ፓሊስ የለም፣  መንግሥት የለም!!!ከቁሳዊ ልማት በፊት ስብዓዊ ልማት ይቅደም፣ ከመገንባታችን በፊት  እንስማማ!!! በፊት ሳንስማማ እየገነባን ማፍረስ የእንቦይ ካብ፣ የእንቦይ ካብ ሆነ የኢኮኖሚ እድገታችን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትንሽ ስለ ጀዋር መሓመድ - በአብርሃ ደስታ

መንግሥት ያለጥበብ አይቆምም፤ ሀብትም ያለጥበብ አይቆይም!!! ተረት ታሪክን አያሸንፍም!!! በኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰብ ተረት ተረት ደዌ በሽታ የተነሳ ነፃነት በባርነት፣ የባሪና ጌታ እኩልነት፣ ዜግንት በተንሸዋረረ ዘውጌነት፣ወዘተ ተቀይሮ የተማሩ ጋንግስተሮች መንጋቸውን እየነዱ በዘር ያጨፋጭፉታል፡፡ የኔ ዘር ካንተ ዘር ይበልጣል!!! የማ ዘር ጎመን ዘር!!! እየተባባሉ አህዛቡን ያተራርዱታል፣ ያጨፋጨፉታል፣ ያፈናቅሉታል፡፡ በአንድ ጥናት በኢትዮጵያ ውስጥ አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን ህዝብ የሥነ አዕምሮ ችግር እንዳለብን ጠቁመዋል፡፡ ከልጅነት ዘመን አቀንጭራ፣ ያልተመጣጠነ ሥርዓተ ምግብ፣ የጫት ሱስ፣ የአረቄና ጠጅ ሱስኝነት ጋር ተደምሮ ከውጭ በምፅዋት የምንመገበው በጄኔቲክ የተሸሻለ ምግብ (Genetically Modified Food)  የህሊና ውስጠኔአችንን አረመኔያዊ ድርጊት እንዲፈጽም አድርጎናል፡፡   በቁሳዊ ልማት የት ቢደርሱ፣ እልፍ አእላፍ ሠማይ ጠቀስ ፎቆች ቢገነቡ፣ ሽህ ሳተላይት ቢያመጥቁ፣ የኒዩክለር ማብላያ ቢያስገነቡ፣ ፓርኮች፣ ፋውንቴኖች፣ ስው ሰራስ ሐይቆችና ግድቦች፣ ቤተመንግሥት፣ ወንዞችና የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት፣ ስማርት ሲቲ የጫካ ፕሮጀክት ቢገነቡ አረመኔዎቹ ጋንግስተሮች ያወድሙታልና ስለምን ይደክሙብናል፡፡

ሰነፎች የሰበሰቡትን ጠቢቦች ይበሉበታል፤ በበደለኞቹ ክፋት ቅኖች ይመሰገናሉ፤ በሰነፎች ስሕተት ጠቢቦች ይወደዳሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እነዚህ አረመኔ ጋንግስተሮች ከአዲስ አበባ ከተማን ዙሪያ ገባ ከበው ወደ አዲስ አበባ ከተማ ለመግባት በማጎብኮብ ላይ እንዳሉ ናዝሬት- አዳማ፣ ደብረዘይት ብሸፍቱ እጣ ፈንታ እንደ ሻሸመኔና አጣዬ መሆኑን እኛም እርሷም ያውቃሉና ምን አደከመዎት!!! አረመኔ ጋንግስተሮቹ ባንክ ይዘርፋሉ መንግስትዎ ዝም፣ የጦር ግምጃ ቤት ይዘርፋሉ መንግሥትዎ ዝም፣ ሴት ይደፍራሉ መንግሥትዎ ዝም ይላል፡፡መንግሥት ያለጥበብ አይቆምም፤ ሀብትም ያለጥበብ አይቆይም!!! ተረት ታሪክን አያሸንፍም!!!ኢትዮጵያ የአረመኔዎች እስር ቤት ሆናለች!!! ግን በመጨረሻው በአረመኔዎቹ መቃብር ላይ ኢትዮጵያ ትነሳለች፣ አንድ መርጫ ብቻ ከትንሳዔዋ ጋር መቆም አሊያም ከአረመኔዎቹጋር መውደም!!!

ተጨማሪ ያንብቡ:  በትዞራለች ...ትዞራለች ...ሲደክማት ታርፈና አሁንም ትዞራለች !

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፤ ይልቅ ሃያ አንድ ሚሊዮን ህዝብ አስቸኮይ እርዳታ ይሻልና ይድረሱለት፣ አስራ ስድስት ሚሊዮን ህዝብ በድርቅ ተጎድቷልና ይድረሱለት፣ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ከቀየው ተፈናቅሏልና ይድረሱለት፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ያገኙትን የአንድ ትሪሊየን ብር የጫካው ፕሮጀክት ገንዘብ ነፍስ ያድኑ ይድረሱላቸው እንላለን፡፡

ምንጭ፡-

(1) ከንግሥት ሳባ ንግግር የተወሰደ/ መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ/ መስፍን ወልደማርያም 200ዓ/ም ገጽ 69-70

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.