አልቃሽ እና አወዳሽ  -ህዳር ፳፱  

ጉልቻ ቢለወጥ……ወጥ ላይወጠወጥ  ቢወጠወጥ ላይጣፍጥ…..ቃል በቃል ቢተካ ከጋጋታ ያለፈ ጠብታ እርካታ የለም ፡፡

ከግማሽ ክ/ዘመን በፊት ታላቁ ኢትዮጵያዊ የስነፅሁፍ ሠዉ ደራሲ ፣ዶ/ር ከበደ ሚካኤል “ የኢትዮጵያ ህዝብ እብደገብስ ዛላ ነፋስ የሚከተል  ”ብለዋል የሚል አንድ መልዕክት ከዓመታት በፊት ተመልክቸ ስለነበር ዞትር ስለ እኔ እና ስለእኛ ሳስብ  ነገሩ ዕዉነት ስለመሆኑ አስከዛሬ ድረስ ዕዉነትነቱን ለአፍታ አልጠራጠርም ፡፡

ከዚህም በላይ የታላቋ ኢትዮጵያ አስካሁን  የመጨረሻዉ መሪ  ኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም  “ህዝቤ ወርቅ ሲሉት….ጠጠር ” ይላል  እንዳሉ እንሰማለን፡፡

እዚህ ጋ ከላይ የመጨረሻዉ መሪ ያልኳቸዉ መንግሰቱ ኃ/ማርያም ለኢትዮጵያ አንድነት እና ለዜጎች ዕኩልነት በዕዉነት ፣ በነፃነት እና በፍትኃዊነት ….ለመስራት እናለመምራት በሙሉ ልበ ቅንነት ፣ ብቃት እና ኢትዮጵያዊነት ማንነት መስራታቸዉን በተግባር ስለምናይ እና ነገ ታሪክ እና ትዉልድ እንደ አርሳቸዉ ለአገር እና ለህዝብ ክብር እና ዳር ድንበር የሚኖር መሪ እንዲኖር በትብብር እንደሚሰሩ (ታሪክ እና ትዉልድ) ስለምገምት ነዉ ፡፡ ኢትዮጵያን ከተሟላ ሉዓላዊ ዳር ድንበር ፣የባህር በር ባለቤትነት ፣በኢትዮጵያ ህዝብ በማንኛዉም መልኩ የማይደራደሩ መሪ መሆናቸዉን እኛ ብንክድ የኢትዮጵያ ጠላቶች እና ዓለም ያዉቁታል፤ይመሰክሩታል፡፡

እኛ ኢትዮጵያዉያን በዕዉነት ፣በአገራችን የጋራ ጉዳይ እና በልዩነት ላይ ሳንግባባ በሀሰት ላይ እንዴት እንደምንግባባ ባይገባኝም ሳንግባባ እንደተግባባን ማስተጋባታችን ደግሞ የመጨረሻዉ የመዉረዳችን ምልክት እና ሳንሰማ እንደሰማን፤ ሳይገባን እንደገባን ….ማጨብጨብ የምናቆመዉ መቸ ነዉ ፡፡

የማይገባንን እስኪገባን ዝም ማለት እና መረዳትን ለምን ችላ እንላለን ፡፡ በሰሞነኛ ነገር እየሰከርን እንዴት እና አስከመቸ በሞት እሳት ቆመን እንረማመዳለን….እናጨበጭባለን፡፡ በራስ ጥፋት እና ሞት መደሰት  ዕዉነተኛ ደስታ የሚሆነዉ እንዴት እንደሆነ ባይገባንም ለአመታት አየነዉ ከሞት ወደ ህይወት ፣ ከዉድቀት ወደ ዕድገት እንጂ እንዴት  ጨርቅ እና ወርቅ እንድ ሲሉን ሁለት እያልን ወደ ሲኦል እንነዳለን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰው የዳቢሎስ ጠበቃ ከሆነ ነገር ዓለሙ ሁሉ መበላሸቱ አይቀርም - መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ 

ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዉን የኢህአዴግ ህገ-ደንብ ሥራ ላይ የዋለበት ህዳር ፳፱ ቀን ሲታወስ አገሪቷ ላይ ይህ ህገ-ኢህአዴግ ስራ ላይ እንዲዉል እና ኢትዮጵያ እና ህዝቧ የክህደት እና ሞት ቋጥኝ ከተደፋባቸዉ ጊዜ አንስቶ ምን አገኘን ምን አጣን ሳንል እና በቁስል ስቃይ እና በገደል አፋፋ ሆነን በየሰሞኑ ሰሞነኛ መሆናችን ከህይወት እንደተቆረጠ ቅጠል ለራሳችን መጥፊያ እሳት ማቀጣጠያ መሆናችን ከገብስ፣ ጠጠር እና ጨርቅ ወርደን አጥፊ እና ጠፊ መሆናችንን ያሳያል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ እና በተለይም ኢትዮጵያ እና በህገ-ኢህአዴግ የተረሱት ፣የተገለሉት ብዙኃን ኢትዮጵያዉያን ላለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት የደረሰባቸዉ እና እየደረሰባቸዉ ስቃይ እና ተጭኗቸዉ ያለዉ የመከራ ቀንበር አስኪሰበር ህዳር ሀያ ዘጠኝ አልቃሽ እና አወዳሽ ሆና ማስተናገዷ አስከመች ይሆን ፡፡

ለኢትዮጵያ አንድነት እና ዘላቂ ዕድገት ሁሉንም ኢትዮጵያዉያን እና የኢትዮጵያን ግዛቶች የሚገልፅ ህገ-ህዝብ(ኢትዮጵያ) አስካልሰፈነ ጊዜ ድረስ ህዳር ፳፱  ከግንቦት ፳ ቀን መወለዱን ሳንረሳ እየተወሳ እነኝህ ሁለት ዕለታት “ መረሳትም፤ መወሳትም ” ለኢትዮጵያ እና ብዙኃን ኢትዮጵያዉያን ያስገኘዉ መት ወይስ ትሩፋት ብሎ መረዳት ቢመሽም  ጭለማዉ በርትቶ ባለመንጋቱ ይታሰብበት የምን መዘናጋት ፤ የምን ዳግም ጥፋት ለምንድነዉ መርሳት   ፡፡

 

አንድነት ኃይል ነዉ ፡፡

Allen Amber

 

 

 

1 Comment

  1. እንግዲህ ወዳጄ ችግሩን አብረን አይተናል ይህ እንዲሆን በትግሬዎችና በኢትዮጵያ ጠላቶች በጥንቃቄ ተነድፎ በተግባር ላይ ውሏል። እንዳየኸው አሁን የሚዘርፈው ካድሬና የጎሳ ሹመኛ ብቻ ሳይሆን ወደፊት ለዘረፋ ቦታውን ላገኝ እችላለሁ በሚል ተስፋ ጌቶቹን ለማስደሰት ሌት ተቀን የሚደክም ባንዳ ቁጥሩ ቀላል አይደለም። ኢትዮጵያዊነት የሚለው ሀሳብ እንዳይመለስ ስብሀት ነጋና አረጋዊ በርሄ በብረት አትመውበታል ክልሎች የተሰጣቸውን ጨርቅ እየተሸከሙ ላይ ታች የሚሉ በእውቀት ያልጠነከሩ እንኩቶዎች የበዙበት አገር ሁኗል ይህም የረጅም እቅዱ አንድ አካል ነው። ከሰው ይህን ይመስላል የአምላክን እንጠብቃለን። ያን ሁሉ ግፍ የሰራ የትግሬ ቡድን ዛሬ በኢትዮጵያ መገናኛና ተከፋይ ዩ ቱዩበርስ(ቱቦዎች) ጌታቸው ረዳ፣ታደሰ ወረደ፣ጻድቃን ምናምን ሊመሰገኑ ይገባል እያሉ ውዳሴ ማውረድ ይዘዋል። ይህ ነው ትውልዱ ይህ ነው አመራሩ። ለማንኛውም ይህን ሰቆቃ የበዛበትን ህዝብ አምላክ ይጎብኘው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.