Comments on: የአማራ ሸኔ ይፈጠር እና የአማራ ሸኔ አለ፤ ለየቅል ነው፡፡ ሂሳብን በዚህ ዓነት መልኩ ኃላፊነት የሚሰማው መንግስት አያወራርድም https://amharic-zehabesha.com/archives/178408 ዘ-ሐበሻ | Ethiopian News | የዕለቱ ዜና | ሰበር ዜና, ትኩስ የዕለቱ ዜና በአማርኛ, የኢትዮጵያ ዜና | ዜና ፖለቲካ ፣ አይቲ ዘ-ሐበሻ ሰበር ዜና ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ ሌሎች ብዙ አዳዲስ ዜናዎች| Fri, 13 Jan 2023 14:10:23 +0000 hourly 1 https://wordpress.org/?v=6.1.1 By: Getnet A. https://amharic-zehabesha.com/archives/178408#comment-202849 Mon, 26 Dec 2022 08:49:24 +0000 http://amharic-zehabesha.com/?p=178408#comment-202849 ለሃገርና ለሰፊው ህዝብ ጥቅም በቅንነትና በአንድ ልብ እስካልተቆመ ድረስ ሃገሪቱ እንዲህ ባሉ እውቀትም፤ ቅንነትም፤ ሰውነትም በጎደላቸው ሃይሎች ህልውናዋ አደጋ ውስጥ መግባቱ እማይቀር ነው፡፡
የሰውን ስብእና በውጫዊ ተክለሰውነትና በአፍ ሽንገላ መዝኖ የሚቀበል ህዝብ ከዚህ መማር ካልቻለ ነገም ሌላ አፈ-ቀላጤ የመንግስትን ቦታ ተቆጣጥሮ ሃገርንና ህዝብን መጫዎቻ የማያደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርም፡፡

]]>
By: Tesfa https://amharic-zehabesha.com/archives/178408#comment-202845 Sun, 25 Dec 2022 14:11:12 +0000 http://amharic-zehabesha.com/?p=178408#comment-202845 ጠ/ሚሩ ተናግሮ የማይጠግብ፤ ሁሉን አውቃለሁ የሚል፤ በስማ በለው እንጂ በመረጃ የማይመራ ለመሆኑ በየጊዜው ከሚደሰኩራቸው ንግግሮች መረዳት ይቻላል። የሚገርመው አፉን በከፈተ ቁጥር እያዋዛ ጣል የሚያደርጋቸው ከፋፋይና ከንቱ ውዳሴዎች አንድን ደስ አሰኝቶ ሌላውን ለማስከፋት በእቅድ የሚሰራበት ይመስላል። በምድሪቱ ሙሰኝነትን መዋጋት በብልጽግና (በድህነት) ፓርቲ አልተጀመረም። ደርግም ከበሮ መቶበታል፤ ወያኔ ከአዲስ አበባ መሃል ከተማ ብዙ ሺህ ኩንታል ቡና ሲሰረቅ እጅ እንቆርጣለን ብሎ ዝቶ ነበር። ያለፈውም ሆነ የአሁኑ የውስልትና ዛቻ ነው። የተደረገ የሚደረግም ነገር የለም። ጉቦውና ስርቆቱ ይቀጥላል። የሚያሳዝነው ጠ/ሚሩ የሰረቃችሁም በዛው ሃብት ዳቦ ቤት ክፈቱልን ማለቱ ነው። ይህችን ይወዳል። ለየትኞቹ ሌቦች ነው ይህ ሰርቆ በዳቦ ቤት ምህረት ማግኘት? ለወያኔ ዘራፊዎች ወይስ አሁን በኦሮሞ ህዝብ ስም በየስፍራው ተሰግስገው ህዝብን የሚግጡትን የቀን ጅቦች? ግን ሰውየው ተማቶበታል። መካሪ ቢኖረው ባይናገር ይመረጣል። በምን ሂሳብ ነው የአንዲት ሃገር መሪ እንዲህ ያለ ቃል የሚናገረው?
ቀጥሎም በንግግሩ ነገር ሲያደፈርስ የአማራና የኦነግ ሸኔ። እነማን ይሆኑ? መቼ ነው ይህ ጥምረትም ሆን ስም ለአማራው የተሰጠው? ግን አበው እንደሚሉት አህያውን ፈርተው ዳውላውን እንዲሉ ነውና ከኦነጎች ጋር ላለመላተም ተለጣፊ ስም መፈለግ አስፈላጊ ስለሆነ ነው እንዲህ ነገር የሚያምታታው። እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም። አንገታችን ይቆረጣል እንጂ እያለ እንዳልደነፋ አሁን ደግሞ ይህች ሃገር እንዳትፍረከረክ እሰጋለሁ ይለናል። ትፍረክረካ፡ ኑሯም አላማረባትም። ግን አትራፊ አይኖርም። መጫረስ፤ መገዳደል፤ መወነጃጀል፤ ረሃብና ሰቆቃ ነው የምናተርፈው። እንዲህ በተሳከረ የፓለቲካ አስረሽ ምቺው እሰጣ ገባ እንዴት ነው ሃገር ገንብቶ ተተኪ ትውልድ ማፍራት የሚቻለው? ጠ/ሚሩ ያው ወያኔ ወልዶ ያሳደገው በወያኔ የተንኮል ፓለቲካ የተቃመሰ በመሆኑ የፓለቲካ ሸሩን ተክኖበታል። ግን ለምን ይሆን ከዘመን ዘመን ምድሪቱ የክፋት ጥግ የወጡ መሪዎች ብቻ የሚያተራምሷት? ፊውዳሉ ሲሄድ፤ አውሬው ደርግ ተተካ፤ ኦ ይህም አለፈ ሲባል በዘርና በቋንቋ የተደራጀው የወያኔ ግፍ ምድሪቱን አስረገዳት፤ እስቲ አሁን በቃ በለን ስንል ቋንጭራ ይዞ ነፍሰ ጡር ሴትን ሆዷን የሚዘነጥል፤ ከሃገሬ ውጡልኝ የሚል የኦሮሞ ስብስብን ላከብን። አሁን በእውነት ፈጣሪ አለ? ወይስ ከላይ ሆኖ እያየ ይስቃል በጅልነታችን? አላውቅም። እንደ ሃበሻ ምድር ያለ ከጊዜ ወደ ጊዜ የማይሻለው ህዝብና ምድር የትም የለም።
እውቁ ደራሲ አቤ ጉበኛ – አቤ ሰፊ ህዝብ ማለት ምን ማለት ነው ተብሎ ሲጠየቅ “ሞቶ የማያልቅ ማለት ነው” ነበር ያለው። ጠ/ሚሩ ሃገር ያቆመ እየመሰለው በየጊዜው የሚናገራቸው ንግግሮች ከፋፋይና ግርግር ፈጣሪዎች እየሆኑ ነው። ለምሳሌ ያህል “አዲስ አበባ ውስጥ ኦሮሞ ጠሎች አሉ” ሰውን እንዲጠላ የሚያደርገው ተግባሩ እንጂ ዘሩ አይደለም። ወያኔን እንዲጠላ ያደረገው ድርቡሻዊ ሥራው ነው። ደርግን እንዲጠላ ያደረገው ገድሎ መሰንበት መሻቱ ነው። የፊዳሉን መንግስትም መንኮታኮት እልፎች እየተራቡ ጥቂቶች የሚፈነጩባት ምድር በመሆኗ ነው። ጥያቄው የዛሬው ካለፈው የሚለየው የቱ ላይ ነው? የኦሮሞን ባንዲራና መዝሙር በግድ ዘምር መባሉ ከጣሊያን ወረራና በግድ ጣሊያንኛ ልመድ ወይም የጣሊያን ሰንደቅ መዝሙር ዘምር ከሚለው ምን ለየው? ፓለቲከኞች ልበ ቢሶች ናቸው። ይህ የእኛው ሃገር የዘር ፓለቲካ ቢይዙት የማይጨበጥ ንፋስ ነው። ለጊዜው ሰውን አፋጅቶና የሌለ ተስፋ አስታቅፎ በምትኩ ደግሞ ሌላ ገፊና ገፍታሪ ይመጣል። በታሪክ ያየነው ይህን ነው። ጠ/ሚሩ ቃሉ አጭር፤ የሚናገረውን በጽሁፍ አዘጋጅቶ ቢደሰኩር ይሻላል። ዝም ብሎ አፍ እንዳመጣ መለፍለፍ ከአፍ የወጣ አፋፍ ነውና ጥንቃቄ ያስፈልጋል። የአማራ ሸኔ የለም። የኦሮሞ እንጂ! እያማቱ መኖር ይቅር።
በመጨረሻም ዮሃንስ ፍሥሃ – ናፋቂ ዜማዎች ላይ ካሳተመው አንድ ግጥም አልፍ አለፍ ብዬ ጥቂት ስንኞች ልዋስና ነገሬን ልቋጭ።
ህልም አይቼ ነበር መሃል አዲሳባ
የጎመን ድስት ወቶ የገንፎ ሲገባ
ለጎመን ድስት ቀብር አፈር እየማስኩኝ
ቀበርኩት ስል ከሥር ወጣሁኝ ስል ከላይ
እኚህን ጅምር ህልሞች በቅዥት ለውሶ
ከማረፊያው ጣለኝ ከህልሜ ቀስቅሶ
የሃበሻው የፓለቲካ ተንኮል ይገታ ይሆን? ወይስ ዝንተ ዓለም አንድ በአንድ ሌላው በሌላው እያሳበበ ትውልድ እያስጨረስን፤ ያለፈውን እየደገምን፤ ካለፈውም የከፋና የከረፋ ነገር እየፈጸምን በደምበር ገተር ፓለቲካ ውስጥ ተዘፍቀን እንኖር ይሆን? በቃኝ!

]]>
By: TG https://amharic-zehabesha.com/archives/178408#comment-202844 Sun, 25 Dec 2022 12:45:27 +0000 http://amharic-zehabesha.com/?p=178408#comment-202844 Most of your points of view and points of argument tell the very hard reality on the ground ! Good !

But the way you tried to describe and characterize the prime minister makes the whole of your points of argument very weak if not badly paradoxical ! To describe a guy whose political personality is full of deception, dishonesty , hypocrisy, conspiracy , lie , arrogance, narcissism, immorality , and of course cruelty, … as someone who does wrong things knowingly or unknowingly and also because of his bad advisors is terribly misleading if not politically nonsensical!!!

]]>