ከጠ/ምኒስትር ከዐብይ አህመድ: ለሌቦቻቸው የቀረበ ጥሪ !! (አሥራደው ከፈረንሳይ)

ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ፤ ይቅርታ ፓስተር ዐብይ አህመድ፤ ማለቱ ሳይሻል አይቀርም፤ ሰሞኑን በወላይታ ፤ የዳቦ መጋገርያ ፋብሪካ ለመመረቅ፤ ወደ ወላይታ ሄዶ ባደረገው ንግግር ፤ በኢትዮጵያ የህወሃትና  የብልጽግና፤ (ኦህዴድ/ኦነግ/ብአዴን) ሥርዓት የፈጠሯቸው ሌቦቻቸውን፤ የኢትጵያን ሕዝብ ሃብት በመዝረፍ በህግ ፊት እንዳይጠየቁ፤ ፤ ዳቦ ቤት፤ ትምህርት ቤትና ሆስፒታሎች….ወዘተ. እንዲከፍቱለት ተማጥኗል ::

ከአንድ አገር መሪ በማይጠበቅና፤ እጅግ በዘቀጠ መልኩ፤ እመራታለሁ በሚላት አገርና፤ በሚመራው ሕዝብ ፊት ቀርቦ፤ በኢትዮጵያ የህግ የበላይነት ባለመኖሩ፤ ፍትህን ማግኘት እንደማይቻል፤ በገዛ አንደበቱ ለህዝብ አረጋግጧል ::

አጠያፊ ሌቦችን በመጠየፍ፤ በህግ የበላይነት፤ ለፍርድ በማቅረብ፤ እንዲጠየቁ በማድረግ ፈንታ፤  የአገር ሃብት በመዝረፍ፤ በንቅዘት (በሙስና)  የበሰበሱትን ሌቦች፤ ዳቦ ቤት ክፈቱልን፤ ት/ ቤት፤ ሆስፒታሎችን ሥሩልን  …. ወዘተ ብሎ ሲማጠን መስማቱ፤ የኢትዮጵያን ትንሳኤ  ለምንናፍቅ ዜጎች ፤ በእጅጉ የሚዘገንንና  የሚያበሳጭ  ሆኖ አግኝቸዋለሁ ::

ከዚህ በፊት « ከሠርቶ አደር: ወደ ሰርቆ አደር  ነገስ ?! » በሚል ርዕስ ባቀረብኩት መጣጥፌ : ሌብነትና ሌቦችን በመጠየፍ ለፍርድ ማቅረብ እንደሚገባ አመላክቼ እንደነበር ፤ አንባቢዎቼ በዚህ ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ሊቃኙ ይችላሉ ::

https://www.goolgule.com/challenges-for-change-in-ethiopia/

« ዋልታ ረገጥ ! ጽንፍ የረገጠ !  የአማራው ሸኔ ! የኦነግ ሸኔ !  ……. ወዘተ. ለሚሉት  አባባሎቹ             ሰሞኑን ከአማራ ቆዳ በተሠራ  ከበሮ: ጭፋሮ !!  በሚለው የሁለተኛው ክፍል መጣጥፌ ስለምመለስበት  ለጊዜው ትቼዋለሁ ::

ወገኖቼ እስቲ እግዜር ያሳያችሁ ! በድሃው ሕዝባችን ስም፤ በብድርና በልመና ከውጪ አገራትና ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች፤ የተገኘን ገንዘብ በመዝረፍ፤ ዓሣ ዓሣ የሚሸቱ ሌቦችን፤ ዳቦ ቤት ክፈቱልን፤                      ት/ ቤትና፤ ሆስፒታሎችን ሥሩልን  ብሎ ከመማጠን በላይ፤ ምን ዓይነት የፖለቲካ ክስረት ይኖራል ?!

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአርቲስት ሻምበል በላይነህ አገራዊ ስራዎች አርአያነት - “ወጣቱ አንበሳ ላገርህ ተነሳ...” (ከሉሉ ከበደ)

እርግጠኛ ነኝ፤ ለህሊናው የሚኖር ኢትዮጵያዊ፤ ሌቦች ከከፈቱት ዳቦ ቤት፤ ገዝቶ ለመብላት ቀርቶ፤ በበሩ ደጃፍ ሲያልፍ እንዳይሸተው አፍንጫውንና አፉን በጭንብል ሸፍኖ፤ እንደሚያልፍ አልጠራጠርም ::

ደግሞስ፤ ቱባ ቱባ የሆኑ ሌቦች፤ ባሠሩት ት/ ቤት ውስጥ፤ የሌብነትን ሞያ ተምረው የሚመረቁት፤ አዳዲስ ወጣት ሌቦች፤ የሚሰማሩበት የሥራ ቦታ፤ ገንዘብ ሚኒስቴር ፤ ማዕድን ሚኒስቴር፤ ብሔራዊ ባንክ፤ ንግድ ባንክ፤ የመሬት ይዞታና ማዘጋጃ ቤት ሳይሆን ይቀራል ?!

ሌቦች በሚያሠሩት ሆስፒታል ውስጥ ገብቶ የሚታከም ዜጋ፤ አንድም እንደነሱው ሌባ የሆነ፤ ወይም የለየለት ጨርቁን ጥሎ ያበደ፤ አለያም ኑሮ አስከፍቶት እድሜዬን ላሳጥር ብሎ ፤ የሚገባ ካልሆነ በቀር፤ የሌቦች ሆስፒታል ውስጥ ገብቶ፤ ማንስ ታክሞ ድኖ ሊወጣ ?!

ይህ ጥሪ የቀረበው፤ ዐብይ አህመድ በቅርብ ለሚያውቃቸው ሌቦቹ፤ የቀረበ ጥሪ ቢሆንም፤ የትኞቹ ሌቦች ጥሪውን ተቀብለው፤ በሕዝብ ፊት ሌብነታቸውን ለማስተዋወቅ ብቅ እንደሚሉ ስናስብ፤ አስቂኝም፤ አሳዛኝም፤ ባዶ ኳኳታ መሆኑን እንረዳለን ::

 

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

ነፃነት፤ እኩልነትና ወንድማማችነት ይለምልም !!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ !!

ታኅሣሥ 16 ቀን 2015 ዓ.ም (25/12/2022) እኤአ

2 Comments

  1. መልካም ብለሀል ሰውየው ይህንን ነገር እንዳንተ አካብደው አያዩትም እድገታቸው ምርጥ ምርጥ በሆኑ ሌቦች ስር ነው እንደሚባለው እሳቸው ያገለገሉት ስርአት ከ27-45 ቢሊዮን ብር ሰርቋል ነው የተባለው ።እንደ ዛሬው ሁሉ ቀደም ሲል ክቡራን ሌቦችን ሰብስበው የሰረቃችሁትን ገንዘብ መልሱ ነበር ያሉት ውስጠ ወይራው ግን አሽሹት ማለታቸው ነበር። እነዛ ምርጥ ሌቦች የሳቸው አለቆች በሰረቁት ገንዘብ እረፍት ነስተዋቹው ዛሬ ላይ ያለ እንቅልፍ ያድራሉ። ድንቁ ደያስ ከጁዋር ጋር አብሮ ባይሸሽ ሌላው ተሸላሚ ነበር። 3000ኦሮሞ ቢሊየነር እፈጥራለሁ ብሎ ማለት 3000 አባዱላና ድንቁ ደያስን እፈጥራለሁ ማለት ነው። ሰውዬው የሙስና ወዳጅ ናቸው እንደዛ ባይሆን ከ130 ሚሊዮን ህዝብ ታከለ ኡማ አዳነች አቤቤን የመሳሰሉ ዘራፊዎችን የመንግስትን ሽራፊ ባልሰጠህ ነበር። የትግሬ ሌቦች አንተንም መንግስትህንም ከማፍረሳቸው በፊት ባስቸኳይ በቁጥጥር ውስጥ አስገባ ሲባል እሱ ግን መሾሙን ቀጠለ ዛሬም አይኑ ውስጥ የገቡት የህወአት ወዳጆቹን ከየቦታው እየመለሰ ነው። ዛሬ እስራኤል ዳንሳ፣እዩ ጩፋ፣ዮናታን አክሊሉን የተባሉት ተራ ሌቦችስ ሌብነት የሚጠላ መንግስት ቢኖር ልዩ ጥበቃ ይደረግላቸዋል? ይሄ እንግዲህ በክብር የተሸኘውን ተወልደ ገማርያምን፣አባዱላ ገመዳን ሳይጨምር ነው። ሰውዬው ቅር ቃር ውስጥ የገባው ሲጀመር አባዱላን ለማዳን ነበር ምርመራ ሌሎች ላይ ከተጀመረ እሱን ሊነካበት ሆነ አስሮ ሊፈታው ሲችል እራሱ ላይ ቋጠሮውን አጠበቀው። የማይሆን አርእስት አንስተህ አስወተወትከን ።

  2. ዶር አብይ ቅር ቃር ውስጥ ገብቷል መርህ ስለሌለው ሲወጠር ክብሩን አውርዶ የማይሆን ነገር ውስጥ ይገባል። ጁዋር ዜጎችን ዘቅዝቆ ሲያሰቅል የዛን ጊዜ የሆነውን መርበትበት ማስታወስ ይገባል። ትግሬዎች የኢትዮጵያን መከላከያ በተኛበት ሲያርዱ የኢሳያስን ጉልበት ሲስም የነበረበትን ሁኔታ ማስታወስ መልካም ነው ዛሬ ላይ ፈረንጆች ይሄን አድርግ ያን አድርግ ሲሉት ነብሱን በታደጉት ፋኖ ላይና ኤርትራ ላይ ሊዘምት እያኮበኮበ ነውና ሰውዬው በመርህ ስለማይኖር ነብሱን እያስጨነቀ ይኖራል አሜሪካኖች የሚፈልጉትን ሳያሟላ ሽራፊ ዶላር አያገኝም የሚቀጥለው ግብረ ሰዶማዊነትን ህጋዊ ካላደረግህ አናውቅም ነው የሚሉት እዛ እስኪደርስ ብዙ ወንጀል ይሰራል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.