ለዐማራ ሕዝብ፣ ለዐማራ ክልላዊ መንግሥትና፣ ለዐማራ ብልፅግና ፓርቲ የቀረበ የፍትሕ ጥሪ!

(ለሕዝብና የታሪክ ፍርድ የሚቀመጥ)
                                            ታህሳስ 23/2015 ዓ.ም.
                                                    January 1, 2023
©ልሳነ ግፉዓን ድርጅት
የፍትሕ ጥሪ ለብልፅግና ፓርቲ/በተለይም ለዐማራ ብልፅግና
❶. የፌዴራል መንግሥቱ የወልቃይት ሕዝብ ዐማራዊ ማንነት በይፋ እውቅና መስጠትና ማክበር ይገባዋል!
❷. ፋሽስቱና ወንጀለኛው ትሕነግ በመፋትሔነት ያቀረባቸው “ሕዝበ ውሳኔ” ወይም “በፌደራል ስር/የራስ ገዝ አስተዳደር” የሚሉ ሐሳቦች በሕዝባችን ዘንድ ፍፁም ተቀባይነት የላቸውም! ወልቃይት፣ ጠገዴና፣ ጠለምት ከ1983 ዓ.ም በፊት ወደ ነበሩበት የጎንደር/ዐማራ ክልል በይፋ እንዲካለሉ!
❸. የወልቃይት ሕዝብ የዐማራ ማንነት ጥያቄ ፍትሃዊ ምላሽ መነፈግ ምክንያት የዐማራ ሕዝብ አንድነትና የክልሉ መንግሥት ህልውና አደጋ ውስጥ እንዳይወድቅ አስቀድመን እናሳስባልን!
የዐማራ ክልል ወሰን ወልቃይት፣ ጠገዴና፣ ጠለምትን ባካተተ ሁኔታ እንዲያሻሽል፣ በዚህም መሰረት የክልሉን ሕገ-መንግሥት ማሻሻያ በማድረግ እንዲያፀና አጥብቀን እንጠይቃለን!
“ወልቃይት የማንሻገረው ቀይ መስመራችን” ነው! በማለት ለዐማራና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የገባችሁትን ቃል በተግባር ታረጋግጡ ዘንድ እንጠይቃልን!
❹. በወልቃይት ህዝብ ላይ የተፈፀሙትን ዘርፈ ብዙ ወንጀሎች የሚመረምር ልዩ አቃቢ ህግ በአስቸኳይ እንዲቋቋም በአንክሮ እንጠይቃለን!
የፍትህ ጥሪ ለመላው የዐማራ ሕዝብ
❺. መላው የዐማራ ሕዝብ በልጆቹ ክቡር መስዋዕትነት ከትግሬ ወራሪ ኃይል ያስመለሳቸውን የዐማራ ታሪካዊ መሬቶችህጋዊ ለማድረግና ለማፅናት በቀጣይነት ለምናደርገው ትግል እንደትላንቱ ሁሉ ዛሬም በፅናትና በቁርጠኝነት ከጎናችን እንዲሰልፍና የምናስተላለፋቸውን የትግል ጥሪዎች በአንከሮ እንዲከታተል እናሳስባለን።
❻. የወልቃይትን ሕዝብ የዐማራ ማንነት ጥያቄ የማያዳግም ምላሽ እንዲያገኝ ትግሉ በሚጠይቀው ቁርጠኝነትና ፅናት ልክ የዐማራ ብልፅግና ፓርቲም ሆነ የክልሉ መንግሥት በግልፅ እንዲታገሉና ውጤቱንም ለህዝብ በይፋ እንዲያሳውቁ የዐማራ ሕዝብ በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ ግድ ይላቸው ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን።
“የዘገዬ ፍትሕ እንደ ተከለከለ ይቆጠራል” እንዲሉ የወልቃይት ሕዝብ የዐማራ ማንነትና ፍትሐዊ ጥያቄ ዛሬም ምላሽአላገኘም። ዛሬ ትግሉም መንግሥት ከሆነው የብልፅግና ፓርቲ ጋር ሲሆን፤ የዐማራ ክልልን እያስተዳደረ የሚገኘውየዐማራ ብልፅግና ፓርቲ የፌደራሉ መንግሥት አካልና ባለሙሉ ሥልጣን ነው።
“ጠዋት ከቤትህ ስትወጣ የመታህ እንቅፋት፥ ማታ ወደ ቤትህ ስትገባ ከደገመህ ድንጋዩ አንተ ነህ” ትላንት ከትሕነግ/ኢሕአዴግ ጋር ሆኖ የወልቃይት ዐማራ ሕዝብ ሰቆቃ ያላስቆጣው ብአዴን፣ ዛሬ ከብልፅግና ጋር ሆኖ የወልቃይትን ሕዝብየዐማራ ማንነት ማረጋገጥ የሚሳነው ከሆነና በዐማራ ሕዝብ ስም ያገኘውን ሥልጣን አደላድሎ የሚቀመጥ ከሆነ ጥፋተኛው የዐማራ ሕዝብ እንጂ የዐማራ ብልፅግና አመራሮች ሊሆኑ አይችሉም።
“ስልቻ ቀልቀሎ፣ ቀልቀሎ ስልቻ” እንዲሉ የዐማራ ብልፅግና ለዐማራ ሕዝብ ያለውን ተአማኒነትና ወገንተኝነት በተግባር የማያረጋግጥና የዐማራ ሕዝብ ፍትሐዊ ጥያቄዎችን ቆጥሮና ሰፍሮ ምላሽ የማያሰጥ ከሆነ መላው የዐማራ ሕዝብ በዐማራ ብልፅግና ፓርቲና በዐማራ ክልላዊ መንግሥት ላይ ግልፅ አቋም ሊወስድና ተገቢውን ጫና ሊፈጥር ይገባል።
❼. በመጨረሻም፣ የወልቃይት ሕዝብ የዐማራ ማንነቱን ለማስከበር፣ ጠላት የሆነው የትግራይ ወራሪ ኃይል ዳግም የህልውናችንና የማንነታችን ስጋት ወደ ማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ፣ በብልፅግና ፓርቲና በኢትዮጵያ መንግሥት የተነፈግነውን ፍትሕ ለማረጋገጥ በምናደርገው ትግል መላው የዐማራ ሕዝብ ከጎናችን እንዲሰለፍ ጥሪያችንንእናስተላልፋለን።
ሕጋዊና ፍትሐዊ የማንነት ትግላችን አሸናፊ ነው!
የወልቃይት የዐማራ ማንነትና የወሰን ጥያቄ በድል ይቋጫል!!
ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!!!
ድል ለሕዝባችን!
ሙሉውን ለማንበብ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይዳብሱ👇
ተጨማሪ ያንብቡ:  በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ላለው የዘር ማጥፋት ወንጀል (Genocide) መንግስት ሙሉ ኃላፊነቱን ሊወስድ ይገባል!!! (መኢአድ)

2 Comments

  1. ክቡር አቶ ተታዲዮስ ታንቱ መስከረም አበራ መሳፍንት ጥጋቡንና 13,000 ፋኖዎች ይፈቱ ስብሀት ነጋና የወንጀል ስብስቡን የፈታ እነዚህን ለማሰር የሞራል ብቃት የለውም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.