ሙዋች ሰው ሌላውን ሙዋች በራሱ ስልጣን በጭካኔ ሲገል አንድ ቀን የዘራውን እንደ ሚያጭድ ትዝ አይለውም! – ሙናች ሙሉዓለም ከባይ ማዶ

ሁ ላ ች ን ም   ከ ዚ ህ    እ ን ማ ር ?

ትልቅ የድንቁርና ጥግና ከረባት አጥልቆና የእንግሊዝ ሱፍ ለብሶ በሁለት እግሮቹ የሚንቀሳቀስ ” “ሰው” ሁሉ ሰው አለመሆኑ እንዲህ ስለሚገለጥ ነው ዳዊት ሊሞት ሲል በጥበብ የተሞላውን ልጁን ዳዊትን ሰው ሁን (ከቃሉ ዝንፍ እንዳትል) የሚል ጽኑ የሆነ የአባት ምክር የሰጠው!
(1 ነገ 2:1-3)

*** ይህን ሊንክ ክሊክ ያድርጉና ይመልከቱ:-

https://images.app.goo.gl/sXR4EEtrTAJvak3e8

ዛሬ የዚህን ጨካኝ ሰው ሞት በሔግ የእድሜ ልክ ተፈርዶበት የነበረን የ82 ወንድሞቼን ገዳይ ሞት ስሰማ ደስታ ሳይሆን የተሰማኝ የትቤተኞችና የክፉ ሰዎች መጨረሻ እየባሰ እንደሚሄድ ተረድተን ከወያኔ የቀበሮ ጉድጉዋድና (ሕዝብን ማስጨረስ) ዛሬ ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት ምን ዓይነት ትምህርት ይማር ይሆን? የሚለውን ጥያቄ በማንሳት ልሞግተው ፈልጌ ነውና የደረሳችሁ ለሚመለከተው ሁሉ እንድታዳርሱት የተመረጠት ሴት በሆነችው በማርያም የምትምሉ (መማል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባይሆንም) በእስዋ ስም ይዣችሁአለሁ አዳርሱት
በክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ አምናችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ነን የምትሉ ደግሞ በእርሱ ስም አሳስባችሁአለሁ አዳርሱት????

ለሁላችን ለሃይማኖተኛነት ሳይሆን ለሕይወት ሰው ሆኖ ወደዚች ወደ ተበላሸች ምድር መጥቶ የሞተውና የተነሳው (የትንሳኤው ኃይል) የሆነው ጌታ አምላክ ማስተዋልን ይስጠን!
አሜን::

         አስተዋይ ሰው ከዚህ ይማራል!

መቶ አለቃ እሸቱ ዓለሙ በደብረ ማርቆስ ወህኒ ቤት በአንድ ምሽት ከጨፈጨፋቸው  ከ80 በላይ የጎጃም ወጣቶች መካከል ይህ እህቱ እንባዋን እያፈሰሰሽ ፎቶውን በእጅዋ የያዘችውና የንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ (ድብዛ) ትምህርት ቤት ወጣት ዳይሬክተር የነበረው አቶ በላቸው አደመ ነበር፣!

ተጨማሪ ያንብቡ:  መንገድ ወድቆ አየሁት - ከክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)

አገሪቱ መቶ ዓመት ብታምጥ ደግማ ልትወልዳቸው ወይም ልታገኛቸው የማትችላቸውን በሳል ወጣት ምሁራን እነዚህ ጡንቻ ብቻ እንጂ ማስተዋል ያልፈጠረባቸው የደርግ ስብስብ ጨካኞች ለማይቆዩበትና በውርደት ለተፈረካከሱበት ጊዜያዊና ቀሪ ስልጣን ሲሉ አገሪቱን በአንድ ምሽት የወጣት ድሃ ማድረጋቸው ሳያንስ አገሪቱን ወያኔ ለተባለ ለሌላ ለባሰ የዘር ነቀርሳ በሽታ  ዋና አስፋፊ ጨካኝና አረመኔ ቡድን አሳልፈው ሰጡአት!

*** በወጣንቱ የከፍተኝ ት/ቤት**”

        *ዳይሬክተር የነበረው በላቸው፣ዋ*

https://images.app.goo.gl/4t3E6NcJDpyqkHeF7

ዛሬ ላይ ከሕዝብ ብሶት ከተነሳ ጮኸትና ምሬት የተነሳ ድጋፍ አግኝቶ መንግሥታዊ ስልጣን ከወያኔ የተረከበው የብልጽግና ፓርቲ መንግሥት ምን ትምህርት ይማር ይሆን? ነው ወይስ ሰው ሁሉ ቤተ መንግሥት ካለው ወንበር ላይ ሲቀመጥ መማር የማያስችልና ይባስ ብሎ ያፍዝ ያደንዝዝ መርፌ በስውር የሚወጋ ስውር “የኢትዮጵያ መንግሥት አለቃ” የሚባል መንፈስ አለ???

የኢትዮጵያ መንግሥት ሆይ!
ጆሮ ያለው የእግዚአብሔር መንፈስ የሚለውን በማስተዋል ይስማ!

ከታላቅ አክብሮት ጋር
ሙናች ሙሉዓለም
    ከባይ ማዶ

Leave a Reply

Your email address will not be published.