ጥር 6 ቀን – የመይሳው ካሳ የልዴት ቀንና የአሁኗ ኢትዮጵያ በአንክሮ (እውነቱ ቢሆን)

ዛሬ ጥር 6 ቀን መንጋ የብልጽግና ሆድ አደሮች፣ ተረኞችና  የወያኔ ውርጋጦች  የሚያላግጡባትን ታላቋን ኢትዮጵያ ከገነገነ የመሳፍንት አገዛዝ አውጥተው አንዲነቷ የተጠበቀ ዘመናዊት ኢትዮጵያን እውን ያደረጉት ታላቁ ንጉስ አጼ ቴዎድሮስ የተወለዱበት ቀን ነው፡፡ በጀግንነት ስማቸው “መይሳው ካሳ” ተብለው የሚታወቁት አጼ ቴወድሮስ የተወለዱት ጥር 6 ቀን 1811 ዓም ነበር፡፡ የመሳፍንት አገዛዝን አፍርሰው አገሪቱን አንድ ካደረጉ በኋላ በዚያ ዘመን በጠላቶቿ እጅ ወድቃ የነበረችውን እስራኤልን ከጠላቶቿ ለማስለቀቅ መርከብ ለማሰራት አቅደው የነበሩት ታላቁ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ንጉስ አጼ ቴወድሮስ ለዚህ ውጥናቸው ህዝቡ እንዲህ ሲል ግጥም ገጥሞላቸዋል፡፡

ታጠቅ ብሎ ፈረስ ካሳ ብሎ ስም
ዓርብ ዓርብ ይሸበራል እየሩሳሌም

የአሁኑ ዘመን ወጣቶች የንጉሱን ታሪክ ለመመርመር ይረዳቸው ዘንድ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ቴወድሮስ አደባባይ ያለውን መታስቢያቸውንና ሊያሰሩትም አስበው የነበረውን “መድፍ ” አይቶና መርምሮ ለአገራቸውየነበራቸውን ህልምና የስልጣኔ አሻራቸውን ምን ያህል ከፍተኛ እንደነበረ መረዳት ይችላል፡፡

ስለ ንጉሱ ታሪክ፣ ስለእንግሊዞች ወረራ፣ እንግሊዞችን እስከመቅደላ ድረስ ማን መርቶ እንዳመጣቸው፣ ለባንዳወቹ በዉለታ  እንግሊዞቹ የሰጧቸው ምን እንደነበረ፣ ንጉሱ ለአገራቸው ክብር ሲሉ እጃቸውን ለእንግሊዞች ሳይሰጡ ሽጉጣቸውን ጠጥተው እንደሞቱ፣ ስለምርኮኛው የንጉሱ ልጅ ስለ ልዑል አለማየሁ ቴወድሮስ፣ ምርኮኛው ልዑል በያኔዋ የእንግሊዟ ንግስት እንዴት እንዲያዙ እንደተደረገ፣ መቅደላ ላይ ከንጉሱ ጸጉር ተቆርጦ ወደ እንግሊዝ ተወስዶ ስለነበረው ቆንዳላቸው ……ወዘተ ብዙ ታሪካዊ እውነቶችን ማወቅ ይችላሉ፡፡

አጼ ቴወድሮስ መቅደላ ላይ በነበረው ዉጊያ  የቀኝ እጃቸው የነበረው ገብርዬ እንደወደቀ ሲያዩ አልሸሽም ብለውና እጃቸውንም ለእንግሊዝ ጦር ሰጥቼ አልማረክም ብለው በጀግንነት ሽጉጣቸውን ጠጥተው በኩራትና በክብር ለአገራቸው ሞተዋል፡፡ ንጉሱን ለመያዝ በባንዳወች እየተመራ መቅደላ ድረስ የመጣው የእንግሊዝ ጦር መሪ ንጉሱን በህይወት ሳይማርካቸው በመቅረቱና ይልቁንም ራሳቸው ሽጉጣቸውን ጠጥተው እንደወደቁ በተመለከተ ጊዜ በህይወት ሳይማርካቸው በመቅረቱ ቢያዝንም በንጉስ ደረጃ ሆነው ሽጉጣቸውን ጠጥተው ክብራቸውን ለአገራቸው በመስጠታቸው በድርጊታቸው እጅጉን ተድንቋል፡፡ ይህም በስፋት በውጭ አገራት ተዘግቧል፡፡ ለዚሁ በንጉስ ደረጃ ተሁኖ ለተወሰደ ወደርየለሽ  ጀግንነት አዝማሪ እንዲህ ሲል ግጥም ገጥሞላቸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  "አጐቶቼ ሙስሊሞች ናቸው" - ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም

መቅደላ አፋፉ ላይ ጩሀት በረከተ
የሴቱን አላውቅም ወንድ አድንድ ሰው ሞተ

የንግስና የዘር ግንድ የሌላቸውና የኮሶ ሳጭ ልጅ ስለነበሩት ስለቋራው ካሳ ማለትም አጼ ቴወድሮስ ታሪክ የውስጥም ሆነ የውጭ አገራት የታሪክ ድርሳናት ይህንኑ እውነታ በሰፊው መዝግበው ይዘውታል፡፡ ይህንን የመሠሉ አያሌ መስዋእትነት ተከፍሎባት የጸናችን አገር በማፈራረስ ላይ ያሉት የአሁኖቹ ወፍዘራሾችና ተረኞች ያኔ የት እንደነበሩ ማስረጃችውን ማቅረብ ግድ ይላቸዋል፡፡

የአሁኑ ትውልድ መላው ጠፍቶታል፡፡ ሌላ አገር እንዳለው ሁሉ በመናኛ የገዥወች ጥቅሞች እየተታለለ አገሩን እያጠፋ ያለ ትውልድ ሆኗል፡፡ አገር ከጠፋች አትመለስም፡፡ አገሮች ፈርሰው ህዝቦች ማንነታቸውን አጥተው አይተናል፡፡ አገርየለሽ መሆናቸውንም ሰምተናል፡፡ በእኛም አገር የዚሁ ጅማሮ የሆነውን የአገርየለሽነቱን ሂደት ከአሁኑ ምን ያህል የመረረ እንደሆነ እያየነው ነው፡፡

በሰላምና በእኩልነት ተስማምቶ መኖር የሚቻልባትን አገራችንን ኢትዮጵያን እየበታተንናት ነው፡፤ ሁኔታወች አሁን በሚታየው ሂደት ከቀጠሉ 100% እርግጥ ሆኖ መናገር የሚቻለው በኢትዮጵያዊነትን መቃብር ላይ ኦሮማዊነትን መትከል እንደማይቻል ነው፡፡

እቅጩን እናፍርጠው፡፡ ይህ የተረኞቹ ህልምና ቅዠት ሆኖ ይቀራል እንጅ ኦሮሙማ የበላይ ቀሪውወይንም የተወሰነው  ኢትዮጵያዊ የበታች ተሁኖ የሚኖርባት ኢትዮጵያ አትፈጠርም፡፡ የፈለጉትን ውሸት ቢዋሹ፣ የፈለጉትን ማስመሰያ ቢጠቀሙ ያሻቸውን ‘’CONVINCE and/or CONFUSE’’  ዘዴያቸውን  ቢጠቀሙ (ፖለቲከኞችን ላኩም) ህዝቡን ማታለልና ማጭበርበር  አይሳካላቸውም፡፡ ህዝቡ ስለሁኔታወቹ በሙሉና በነቂስ  ከሚገምቱት በላይ ያውቃል፡፤ ከሚገምቱት በላይ ግፍ አንገሽግሾታል፡፤ ከሚገምቱት በላይ ድሉን በእጁ ለማስገባት ቆርጧል፡፡

በአብይ አህመድ በሚዘወር ያልበሰለና የጨነቀረ የተረኝነት ስሌትና የተበላ ቁማር ሁሉም ግልብጥብጥ ብሎ ብትንትኑ ይወጣል እንጅ አገር አትጸናም፤፡ በአጭሩ ካልታረሙ አገሪቱ ፈራርሳ ለማንም ሳትሆን ትቀራለች፡፤ እንዲያውም ይህ ከሆነ ችግሩ ይብሱኑ የሚበረታው እኔ የበላይ ልሁን በሚለው የጅሎቹ “ኬኛወች” መንደር ይሆናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የሕወሓት አገዛዝ በፈጸመባቸው ግፍ ህይወታቸው ያለፈውን የፕ/ር አስራት ወልደዬስን 23ተኛ ዓመት መታሰቢያ ዘክሯል

ያኔ ዳግማዊ አጼ ቴወድሮስ ይፈጠሩ ይሆናል፡፡  በአሁኑ”እኛ ኬኛወች ብቻ” ወይንም “እኛ የታላቂቱ ትግራይ ህልመኞች” ብቻ  አሸናፊ ሆነን እንወጣለን የሚለው ሀሳብ አንዲት ኢንች አያራምድም፡፡ ሀሳብ ብቻ ሳይሆን ቅዠት ሆኖ መክኖ ይቀራል፡፡

 

 

1 Comment

 1. በእርግጥም አገር አልባ እያደረግን ያለው ኢትዮጵያ ጠንካራ አገር እንዳትሆን አጥብቀው በሚሰሩ የውጭ አገራት ስር የተንበረከከው የአብይ አህመድ ኦሮሙማና የታሪክ አተላው የወያኔ ጥምረት ብቻ አደለም፡፤ ክህዝቡ ውስጥ ወጥተው ህዝቡን የወገኑ መስለው የገዥው ፓርቲ ተቀናቃኞች ፖለቲከኞች ነን ብለው ለየግላቸው ጥቅማጥቅሞች ተገዥ የሆኑት አድር ባይ ፖለቲከኞችም ሚና ቀላል አይደለም፡፡

  የህዝቡን ስቃይ አራዝሞታል፡፡የህዝቡን የትግል ጉዞም አሰናክሎታል፡፡ ብዙወቹ የሚያምታቱት ለሆዳቸው ነው፡፡ ሆዳቸውን እንጅ የህዝቡን ስቃይ አይመለከቱም፡፤ ስቃዩን ቢመለከቱም የስቃዩ፣ የጉዳቱ፣ የግፉ ሁኔታ አይሰማቸውም፡፤ በማታለል፣ በውሸትና በማጭበርበር፣ በመከፋፈልና በጥቅም በመደለል የተካነው አብይ አህመድ አሊ ሁሉንም ሆዳሞች ሸቀጡ፣ አሽከሩና የሚያዝባቸው እቃወቹ አድርጓቸዋል፡፡
  በመሰረቱ ወያኔና ኦሮሙማ የእምየ ኢትዮጵያ አረሞች ናቸው፡፡የሚሰሩት እፍኝ ለማይሞሉ ጥቂት ተከታዮቻቸው እንጅ ለህዝቦቻቸው ያመጡት ጥቅም የለም፡፤
  ወያኔ ሲጀመር አንስቶ ታላቋ ትግራይን እመሰርታለሁ ብሎ ባደረሰው እስካሁን ባልተሳካለት የብዙ አመታት የጥፋት ጉዞው ስንት መቶ ሽህ የትግራይ ወጣቶች (ምናልባትም ከሚሊዮን በላይ) እንዳለቁ ቁጥሩን ሌላ ማንም ሳይሆን የትግራይ እናቶች እነርሱው ይቁጠሩት፡፡ የአብይ አህመድ ኦሮሙማም የሚሰራው የኦሮሞ የበላይነትን በኢትዮጵያዊነት መቃብር ላይ ለመመስረት በሚል ከንቱ ተስፋ በተረኝነት ሲባዝን ይታያል፡፡ የሚያበለጽገው የተወሰኑ የኦህዴድ ጅቦችን እንጅ ሰፊውን የኦሮሞ ህዝብ አይደለም፡፡ ለሰፊው ህዝብ ያስገኘው ልዩ ተጠቃሚነት የለም፡፡ ኦሮሚያ በሚሉት ክልል ውስጥ የሚኖረውን 15 ሚሊዮን የአማራ ህዝብ ቁጥር እየመረጠ በመግደል፣ በመጨፍጨፍ በማሰደድና ቁም ስቅሉን በማሳጣት ቁጥሩን እንዲቀንስ እያደረገ ሄዶ ኦሮሚያን ከአማራ ነጻ አድርጋለሁ ብሎ በተለያዩ የአደረጃጀት ስሞች አበክሮ እየሰራ ነው፡፡ ይህ መሬት ላይ ሀቅ ነው፡፡ የተመዘገብና የተሰደረ ማስረጃና መረጃ ያለው ድርጊት ነው፡፡ ያልትጋነነ ሙሉ እውነት ነው፡፤ ህዝቡም ይህንኑ በሚገባ ያውቀዋል፡፡
  ሲጀመር ይህ ሊሆን የሚችል ጉዳይ አይደለም፡፡ ሌላውን ህዝብ አፍነህ አንተ ተንፍስ፣ ሌላውን ህዝብ አስርበህ አንተ ብላ፣ ሌላውን ህዝብ ገድለህና ጨፍጭፈህ አንተ በሰላም ኑር የትምና መቼም አይሰራም፡፡
  ኢትዮጵያ ውስጥ ከህዝቡ ታሪክ ከህዝቡ የማንነት ባህልና ስሪት አንጻር ማንም የማንም የበላይ ሆኖ ወይንም የበታች ሆኖ የሚኖርበት ሁኔታ ዘሮ ነው፡፤ የለም፡፡
  ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ለጊኡዜውም ቢሆን የእነዚህን የአገር እርግማኖች እድሜ እያረዘሙ ያሉት ህዝቡ መሀል የተሰግስጉት አሽከሮቻቸውና ተቀጣሪወቻቸው ስለሆኑ ህዝቡ እነዚሁኑ ልብ እንዲገዙ ማድረግ አለበት፡፡ ሆዳሞች ከህዝቡ ውስጥ ተለይተው ወጥተው ህዝቡ ራሱ እርምጃ ካልወሰደባቸው ሁሉም ነገር እየባሰበት ይሄዳል፡፡ አሸናፊም ሆነ ልዩ ተጠቃሚ ግን ፈጽሞ አይኖርም፡፡
  ህዝቤ ሆይ፦ የመይሳው ካስን መሰል ጀግናን ከውስጥህ ፍጠርና አገርህን አድን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.