ህገ-ፓርቲ/ ኢህአዴግ  ህገ-ህዝብ አይደለም

በኢትዮጵያ ለነበሩት እና ስር ለሰደዱት ሁለንተናዊ ዉስብስብ ችግሮች ምንጭ እና አማጭ ህገ -ኢህአዴግ  ህገ-መንግስት እየተባለ የሁሉም ነገር አልፋና አሜጋ ሆኖ መታየቱ አስከመች መሆኑን ባይታወቅም መፍትሄ ግን ሊሆን አይችልም ፡፡

ኢትዮጵያ ለየትኛዉም ዓለም አቀፍ ሆነ በሄራዊ ህገ -መሰረት ሆና ስትታወቅ እንጂ በየጊዜዉ በሚለዋወጥ የድርጂት ወይም ፓርቲ ፍላጎት እና ጥቅም የመታንስ እና የምትቀነስ መሆን አልነበረባትም ፤የለባትም፡፡

ሆኖም የታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋ ፣ ጥበብ ፣ ስነፅሁፍ እና ህግ ጥንተ ፍጥረት ባለቤት ሆና ሳለ በህገ-ፓርቲ ዛሬ እንደተፈጠረች ለሚያስቡ እና ስለሚያሳብቡ ሁሉ ዕዉነት ስለ አገር አንድነት እና ደህንነት ማሰባቸዉ የሚያጠራጥር ብቻ ሳይሆን በዕዉነት ሊጠረጠር ይገባል፡፡

ከሩብ ክ/ዘመን ቀድሞ ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታጣ፣ የቀደመ ማንቷ እንዲደበዝዝ፣ ዜጎችን ጠላት እና ወዳጂ የሚለይ ሆኖ በማንነት ላይ ያነፃፀረ የዓመታት ፍጂት፣ ስደት እና ድህነት  መነሰራፋት እንዲሁም ነባር የኢትዮጵያ ግዛቶች አካል የሆኑትን አካባቢዎች ለግጭት እና ሞት ብሎም ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ አንድነት መላላት በር ከፍች የሆነ የክልል አወቃቀር መሰረቱ ይህ ህገ-ፓርቲ(ኢህአዴግ) መሆኑ የሚክድ የለም፡፡

በኢትዮጵያ ህዝብ እና በኤርትራ ከረጂም ዓመታት በፊት እንዲሁም ከሁለት ዓመት በፊት የጀመረዉ እና መጨረሻዉ የማይታወቀዉ የትህነግ የግዛት (መሬት) ይዞታ ይገባኛል የጦርነት ጅምር እና ድምር ይህ ህገ-ኢህአዴግ ከዉልደቱ አስከ ሞቱ ይዞት የሚዞረዉ ኢትዮጵያን ሳይሆን ድርጂትን በአገር እና ህዝብ ጫንቃ የሚጥል ለኢትዮጵያዉን አብሮነት እና ለብሄራዊ ደህንትም ሆነ አንድነት ከሉዓላዊነት ሚዛን ሲቃኝ ስጋት ሆኖ እንደኖረ ዛሬም ቀጥሏል፡፡

የመከራ እና የዕልቂት አዙሪት የሚጀምርበት የጥፋት መድብል መሆኑ ተዘንግቶ ለዕርምት እና ማስተካከያ ዕዉነተኛ እና ዘላቂ ብሄራዊ ሠላም ለማስፈን በኢትዮጵያ አንድነት ላይ መሰረት ለመጣል ሊሰራበት ሲገባ ከዚህ በተቃራኒ መፍትሄ ማድረግ ከንቱ ድከም እንዳይሆን ሊተኮርበት ይገባል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  [የዓለማየሁ አቶምሳ ቀብር ጉዳይ] እነዚህ ሰዎች የሚናገሩትንም አያውቁም

የኢትዮጵያ አንድነት እና የግዛት ወሰኖቿ በነበረዉ ሕገ- ኢህአዴግ ምክነያት ችግር ዉስጥ መግባታቸዉ አስከታወቀ ድረስ ለዚህ  ፍቱን መድኃኒቱ ዕንቅፋቱን ማንሳት እንጂ ማደላደል ለአንድነት እና ለዘላቂ ብሄራዊ ችግር መቅረፍ  ሳይሆን ዳግም ማደናቀፍ ይሆናል፡፡

ከቅርብ ዘመናት ስንነሳ በ12ኛዉ መቶ ክ/ዘመን አንስቶ የኢትዮጵያ ግዛት የት ጀምሮ የት እንደሚቆም ታሪክ እና ትዉልድ የሚያዉቀዉን፤ ተፈጥሮ የሚመሰክረዉን ዕዉነት ገሸሽ በማድረግ ለአገራችን ሠላም ዕጦትም ሆነ ክስተት የኢትዮጵያን ነባር ሁኔታ በመቀያየር እንደሆነ አድርጎ ማስተጋባት ልክ ሊሆን አይችልም፡፡

ለአስረጂነት በሰሜን ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ግዛት የጎንደር  ክ/አሀገር ከተከዜ ምላሽ መሆኑ ፤ እንዲሁም የትግራይ ከተከዜ አስከ ኤርትራ (በህረ ነጋሽ) የሚጋራ የግዛት ወሰን እንደሚጋሩ ከ12ኛዉ ክ/ዘመን መባቻ ከኢትዮጵያ /አቢሲንያ ግዛት ታሪክ ባሻገር የዉጭ አገር ፀኻፍት ሳይቀሩ የሚመሰክሩትን ዕዉነት የዚህ ዘመን ትዉልድ ኃላፊነት ነዉ ፡፡

የኢትዮጵያ ችግር የሚገኘዉ መሬት ላይ ባለዉ ሳይሆን በኢትዮጵያ አንድነት እና መሰረት ላይ በሚታይ የጥላቻ አመለካከት እና በወረቀት በሚገኝ ህገ- ፓርቲ ፍላጎት በመሆኑ በኢትዮጵያ አንድነት እና ሉዓላዊነት ላይ መስራት ግድ የሚል አስከሆነ በጥላቻ አመለካከት እና በወረቀት ላይ በሚንሳፈፍ የችግር ምንጭ በሆነ የችግር እና የመከራ ጎርፍ ከሚነሳበት ህገ- ኢህአዴግ  ህገ- ህዝብ ባልሆነበት ለወለደዉ መከራ መፍትሄ ይሆናል ማለት ግማሽ ዕዉነት ወይም ከፊል ሠላም  በሌላዉ ሞት ህይወት እንደመመኘት ነዉ  ፡፡

 

አንድነት ኃይል ነዉ !

Allen Amber!

ህወሀት ኢትዮጵያን እንዲዘረፍ መንገድ የከፈተው ህገ መንግስት! – በሰዋለ በለው

 

የኢህአዴግ መንግስት በሚቃወሙትና በሚተቹት ላይ እየወሰደ ያለውን አፈና እና እስር የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲታገለው ጥሪ እናቀርባለን!!!

 

ሦስቱን መንግስታት በንጽጽር (ንጉሱ- ደርግ-ኢህአዴግ)

 

አገዛዙ አለኝ የሚለውን ህገ መንግስት በተግባር ቀዶ ጥሎታል!

 

የኢህአዴግ መንግስት ጨካኝ ወይስ ጨቋኝ?

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  ክልል ሲሉ ክልል ስንል! - አገሬ አዲስ

Leave a Reply

Your email address will not be published.